ግብር ሲከፍሉ የነበሩ ግለሰብ ስማቸው ተመሳሳይ ከሆኑ የአንዱ ወደ ሌላው እንዳይሄድ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሰዎቹ ስማቸው ብቻ ሳይሆን የትውልድ ዘመናቸውና ቦታቸው ተመሳሳይ መሆኑ ያመጣው ክፍተት ነበር፤ የአንዱን ግብር ለሌላው ማኖር ፡፡
አንድ ፈረንሳዊ ጡረተኛ ለባለሥልጣናት እንዲረዱት ባቀረበው አቤቱታ ለታክስ ሲከፍል የነበረው የራሱን ታክስ ሆኖ እንዲቀርለትና ላለፉት 15 ዓመታት የከፈለው ታክስ የስም ሞክሼው እንዳልሆነ እንዲታወቅለት ጠየቀ። ዝነኛ ስም አንዳንድ ጠቀሜታዎች አሉት፤ ለማስታወስ ቀላል ነው ስምህን ስታነሳላቸውም ሰዎች ፈጽሞ አቅልለው አያዩህም፡፡ ቢሆንም ግን ሁልጊዜ መልካም ነው ማለት አይደለም፡፡የዘመኑ ተዋናይ ታሪክ በራሱ የሚናገረው ነገር አለው፡፡ ፍራንሲስ ሎፔዝ የተባሉ የሞንትፒለር ነዋሪ የ83 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ፈረንሳዊ አንድ ዓይነት (በተመሳሳይ) ስም አንድ የልደት ቀን አንድ ከተማ እና ሌላው ቀርቶ የደህንነት ቁጥሮች ከመጨረሻው ሦስት አሃዞች በስተቀር ከሌላው ሰው ጋር ይጋራሉ። በአንዳንድ ምክንያት ባለሥልጣኖች ዘወትር የስመ ሞክሼውን ታክስ እንዲሁ በተጨማሪ ይልኩለት ነበር። ሎፔዝ ባለፉት 13 ዓመታት ለአንድ ግለሰብ ታክሱን ሲከፍል ቆይቶ አዲስ የግብር ቀረጥ ሕግ ሲወጣ ብዙ ወጪ ሊያስወጣው እንደሚችል በማሰብ በስጋት ተዋጠ፡፡
‹‹ስማችን ፍራንሲስ ሎፔዝ ነው፤ የተወለድነው በአልጄሪያ ኦራን በአውሮፓውያን አቆጣጠር በኦክቶበር 6 ቀን 1938 ነው፡፡ ከመጨረሻዎቹ ሦስት አሃዞች በስተቀር የደኅንነትና የማኅበራዊ ቁጥሮቻችን ተመሳሳይ ነበሩ፡፡ እኔ ከ2006 ጀምሮ ችግሮች ያጋጥሙኝ ነበር ያሉት ሎፔዝ ‹‹የእሱን ግብር ስከፍል የኖርኩት እኔ ነኝ›› ይላሉ፡፡
እንደ ለ ፊጋሮ ዘገባ ችግሩ የተጀመረው ከ15 ዓመታት በፊት ነው ፡፡ ተጨማሪ ጡረታ ሰጪ አካል supplementary pension provider AG2R ሌላ የፍራንሲስ ሎፔዝ ገቢ ሲመዘግብ ፤ ያም ማለት የ83 ዓመቱ ሽማግሌ ግብር ሲከፍሉ ነው ፡፡ ከኩባንያው ጋር ብዙ ግዜያት ለመገናኘት ቢሞክሩም በመጨረሻ ተስፋ ቆረጡ፡፡ ችግሩን በቀላሉ ማኑዋሊ በእጅ ሊያስወግዱ እንደሚችሉ ገምተው ነበረ፡፡ የሞክሼውን ገቢ ከእሱ የግብር ሰነድ ላይ በመቀነስ ማለት ነው፡፡ ቢሆንም ግን በአዲሱ የግብር ቀረጥ ምክንያት ቸግሩን ለማስወገድ አልተቻለም፡፡
የፈረንሳይ ግብር አገልግሎት የብዙ ፈረንሳዮች ጥያቄ ቢኖርበትም እስካሁን ዕንቆቅልሽ የሚመስለውን ክስተት ለመቅረፍ አልቻለም፡፡ ለሞክሼው ሰውዬ ገቢ ታስቦ 700 ዩሮ ማለትም 830 ዶላር መክፈል አለባቸው፡፡ ይህም ምንም መደረግ ካልተቻለ ባይከፍሉ የሚቀጥሉት ዓመታት ተጠራቅመው ብዙ ሺዎች እከፍላለሁ በሚል ፍራቻ ነው፡፡
እንደ ዕድል የፍራንሲስ ሎፔዝ ታሪክ የፈረንሳይን ዋና ዋና ሚዲያዎችና የማኅበረሰብ ሚዲያዎችን ብዙ ትኩረት ስቦ ነበር ፡፡ እናም የግብር ባለሥልጣናት ችግሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንፈታዋለን ማለታቸውን ስፑኪ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ኃይለማርያም ወንድሙ
አዲስ ዘመን መስከረም 3/2014