እስራኤል፣ ዓለምአቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት(አይሲጄ) በጋዛዋ የራፋ ከተማ የጀመረችውን ጥቃት እንድታቆም በትናንትናው እለት ያስተላለፈውን ትዕዛዝ እንደማትቀበለው ገልጻለች።
የአይሲጄ ውሳኔ እስራኤል በጋዛ እያካሄደችው ባለው ጦርነት እየደረሱባት ካሉት ተከታታይ ጫናዎች እና አለምአቀፍ መገለል ካደረሱባት ርምጃዎች የቅርብ ጊዜው ነው።
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ያነበቡት የፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት ንዋፍ ሳሌም እስራኤል በጋዛ ያሉ ሁኔታዎችን የሚያሻሽል ርምጃ እንድትወስድ ፍርድ ቤቱ ካዘዛት ወዲህ በፍልስጤም ጋዛ ያሉ ሁኔታዎች እየተባባሱ ነው ብለዋል።
“የእስራኤል መንግሥት በራፋ የሚያካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ በአስቸኳይ ማቆም እና በፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ላይ ውድመት ሊያስከትል የሚችልን ጥቃት ጨምሮ ማንኛውንም ርምጃ ከመውሰድ መቆጠብ አለባት” ብለዋል ሳሌም።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ እስራኤል በግብጽ እና በጋዛ መካከል ያለውን የራፋ ማቋረጫ በመክፈት ሠብዓዊ ርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ እንድታደርግ አዟታል።
እስራኤል መርማሪዎች ወደተከበበችው ጋዛ እንዲገቡ እንድትፈቅድ እና ሁኔታዎችን በአንድ ወር ተመልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ 15 አባላት ያሉት የዳኞች ቡድን ትዕዛዙን በሁለት ተቃውሞ በ13 ድጋፍ አጽድቆታል። ከእስራኤል እና ከኡጋንዳ የመጡ ዳኞች ትዕዛዙን ተቃውመውታል።
ውሳኔው የተላለፈው በእስራኤል ላይ የዘርማጥፋት ክስ የመሠረተችው ደቡብ አፍሪካ ከጠየቀች ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።
አይሲጄ በሁለት መንግሥት መካከል የሚኖርን አለመግባባት የሚፈታ የተመድ አካል ነው።
ፍርድ ቤቱ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የመጨረሻ እና አስገዳጅ ቢሆንም ከዚህ በፊት ችላ ሲባሉ ቆይተዋል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ተግባራዊ የሚያደርግበት አሠራር የለውም።
በጋዛ እያደረገችው ያለውን ዘመቻ ራስን የመከላከል ርምጃ ነው የምትለው እስራኤል የሚቀርብባትን የዘር ማጥፋት ክስ አትቀበለውም።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽ/ቤት እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ፈጽማለች የሚለውን የደቡብ አፍሪካ ክስ “ሀሰተኛ፣ አናዳጅ እና የሞራል ተቀባይነት የሌለው” ሲል ውድቅ አድርጎታል።
ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው “እስራኤል ዓለምአቀፍ ሕጎችን እና እሴቶቿን ባከበረ መልኩ ግዛቷን እና ዜጎቿን እየተከላከለች ነው” ብሏል።
ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) አቃቤ ሕግ በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፣ በመከላከያ ሚኒስትሩ ዩአብ ጋላንት እና በሶስት የሀማስ አመራሮች ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው ጠይቋል።
እስራኤል ጥያቄውን የጸረ-ጽዮናዊነት ማሳያ ነው በማለት በጽኑ ተቃውማዋለች።
እስራኤል፣ ሀማስ በፈጸመው ጥቃት 253 ማገቱን እና 1 ሺህ 200 ሰዎችን መግደሉን ተጠቁሞ በጋዛ እያካሄደችው ባለው ጥቃት ከ35ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ባለሥጣን ገልጸዋል።
ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን የዘር ማጥፋት ክስ ሲመለከት ፍርድ ቤቱ ሰሞኑን ባስተላለፈው አስቸኳይ ውሳኔ እስራኤል በጋዛዋ የራፋ ከተማ የጀመረችውን ጥቃት እንድታቆም ማዘዙ የሚታወስ ነው።
አይሲጄ በሁለት መንግሥት መካከል የሚኖርን አለመግባባት የሚፈታ የተመድ አካል ነው። ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ 15 አባላት ያሉት የዳኞች ቡድን ትዕዛዙን በሁለት ተቃውሞ በ13 ድጋፍ አጽድቆታል። ከእስራኤል እና ከኡጋንዳ የመጡ ዳኞች ትዕዛዙን ተቃውመውታል።
ውሳኔው የተላለፈው በእስራኤል ላይ የዘር ማጥፋት ክስ የመሠረተችው ደቡብ አፍሪካ ከጠየቀች ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።
ፍርድ ቤቱ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች የመጨረሻ እና አስገዳጅ ቢሆንም ከዚህ በፊት ችላ ሲባሉ ቆይተዋል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ተግባራዊ የሚያደርግበት አሠራር የለውም።
ከውሳኔው በኋላ ውስን ቁጥር ያላቸው የፍልስጤም ደጋፊዎች “ነጻ ፍልስጤም” እያሉ የፍልስጤምን ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።
የእስራኤል መንግሥት በቃል አቀባይዋ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት “ እስራኤልን ዜጎቿን ከመከላከል እና ሀማስን ከማጥቃት የሚያግዳት ምድራዊ ኃይል የለም” ስትል አስታውቃለች።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም