የራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ከቀናት በፊት በሞስኮ የተገናኙ ሲሆን፤ ሁለቱ መሪዎች ቀደም ብለው በተደጋጋሚ ስለ ሶሪያ ጉዳይ ሲወያዩ ነበር። አሁን ላይ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በሁለቱ መሪዎች መካከል ያለው ውይይት በምርጫው ጉዳይ ላይ እንዲሆን አድርጓል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከአምስት ቀን ቀደም ብሎ በእስራኤል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ማክሰኞ እለት በሞስኮ ከራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ስለ ምርጫው ለመምከር አብረው ነበሩ ፤ ምርጫውም እንደሚያሳየው የአብዛኛውን ህዝብ ውሳኔ ኔታነያሁ እንደተመረጡ ያሳያል።
ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ባላቸው የውጭ ግንኙነት ልዩ ችሎታና በዓለም ዙሪያ ካሉ መሪዎች በሚፈጥሩት መልካም ግንኙነት አማካኝነት ነው። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሞስኮ ያደረጉትን ጉዞ ተከትሎ ኔታንያሁ ከሳምንት በኋላ በዋሽንግተን ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን፤ ይህም ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የመገናኘት ዕድል ፈጥሮላቸዋል። በዚህም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በምርጫው ዋነኛ ተቀናቃኝ ሆነው ከቀረቡት የድሮው የሀገሪቱ የጦር አዛዥ ከፍተኛ ፈተና ገጥሟቸው ነበር ፤ ከተቀናቃኛቸውም ሲቀርቡ ለነበሩ ተጨባጭ መረጃ ለሌላቸው ሀሰተኛ ውንጀላዎች ቦታ ሳይሰጡ በውጭ ግንኙነት ያስመዘገቡትን ውጤትና ከልእለ ሀያልዋ አሜሪካ መሪ ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደ ጠንካራ ጎን በመውሰድ ምርጫውን ለማሸነፍ ችለዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ለአምስተኛ ጊዜ ለመመረጥ በማሰብ ከዚህ ሳምንት ቀደም ብለው በቀጣዩ ማክሰኞ የሚካሄደውን ምርጫ እንዲታዘቡየብራዚሉን ፕሬዚዳንት ጃይር ቦልሶናሮ ወደ እየሩሳሌም ቢጋብዟቸውም መጀመሪያ ከፑቲን ጋር በሶሪያ ጉዳይ ሊወያዩ እንደሚገባ አሳውቀዋል። ክሪሚሊን ከዚህ ሳምንት በፊት እንደተናገሩት ሁለቱ መሪዎች ለውይይት ከመቅረባቸው በፊት የሚወያዩባቸውን አጀንዳዎች ላይ ሊመክሩ ይገባል።
ምክንያቱም ሁለቱ መሪዎች ባለፉት ጊዜያት ይህን ባለማድረጋቸው ሳይግባቡ ብዙ ደክመዋል እስራኤልና ራሺያ በተጠናከረ የአየር ኃይል በሶሪያ ላይ በፈፀሙት ጥቃት በሀገሪቱ ለዘጠኝ ዓመታት የቀጠለ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንድትገባ አድርገዋል። ሁለቱ መሪዎች ከመገናኘታቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ የእስራኤል ጦር ሠራዊት እንዳሳወቀው አገሪቱ ሶሪያን በወረረችበት ጊዜ የእስራኤል ዜግነት ያላቸው የአሜሪካ ተወላጅ ወታደሮች መሞታቸው ይታወሳል አፅማቸውም እ.ኤ.አ ከ 1982 ጀምሮ በደቡብ ሊባኖስ ይገኛል።
በዚህ ወቅት ህይወታቸው ካለፉ ወታደሮች መካከል የሚገኘውና የ 21 ዓመት ወጣት የነበረው ዛቻረየ ባኡሜል ከ37 ዓመት በኋላ አጽሙ ወደ አስራኤል ለመመለስ ችሏል። ለዚህ ውጤት ደግሞ የራሺያው መሪ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ተገልጿል። የራሽያው ፕሬዚዳንት ፑቲን «አሁን ላይ የእስራኤል ጦር ሠራዊት ከሶሪያን ጓዶች ጋር አብሮ በዚህ የመቃብር ስፍራ ላይ ቆመዋል» ያሉ ሲሆን ኔታንያሁ በበኩላቸው እስራኤል የባኦሜለስን አፅም ማግኘት እንድትችል የራሽያው ፕሬዚዳንት እንዲረዳን ከሁለት ዓመት በፊት ጠይቀናቸው ነበር በአደረጉት ድጋፍ አሁን ላይ ያሰብነው ተሳክቷል፤ በዚህም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል ብለዋል። የአጽሙ መመለስ የጋራ ኃላፊነትን የሚያሳይና አንድነትን የሚያጠናክር ነው የባኦሜል አጽምም በእስራኤል በክብር ሊያርፍ ይገባል ሲሉ ለአልጀዚራ ተናግረዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2011
ሶሎሞን በየነ