
በኢትዮጵያ 108 ፓርቲዎች መኖራቸው ይገለፃል፡፡ 66ቱ የብሄር ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ለምን ብሔርን ነፃ እናወጣለን የሚሉ ፓርቲዎች በዙ? የብሔር ፖለቲካ ቀጣይነት እስከ መቼ መዝለቅ አለበት በሚሉት ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ቀድሞ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩት እና አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም እና ደህንነት የሦስተኛ ዲግሪያቸውን እየሰሩ ያሉት አቶ ሞላ ረዳ፤ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የብሔር ፓርቲዎች የመደብ ጭቆና አለ የሚል እምነት ስለነበራቸው ራሳቸውን ከጭቆናው ነፃ ለማውጣት በብሔር ተደራጅተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብዙ ብሔሮች በመኖራቸውም የተለያዩ የብሔር ፓርቲዎቹ የዛው ነፀብራቅ ሆነው መዋቀራቸው ችግር የለውም ይላሉ፡፡ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ዓለሙ ዋጋሬም የአቶ ሞላን ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ አቶ ሞላም እንደሚናገሩት፤ የብሔር ፓርቲ ኖሮ ለብሔረሰቡ ያለውን ጥያቄ አንስቶ ችግሮቹ እንዲፈቱ ማስቻሉ፤ ስለብሔሩ መታገሉ ተገቢ እና አስፈላጊ ነው፡፡ የራሱን ችግር ከፈታ በኋላ የሌሎችን ችግር ይፈታል፤ ለሌሎችም ይታገላል፡፡
ሰው ራሱ በሽተኛ ሆኖ ሌላውን ማሳከም አይችልም፡፡ ስለዚህ የብሔር ፓርቲ መኖሩም ተገቢ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በቅርስ ጥናት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የታሪክ ተመራማሪው አየለ በከሬ እንደሚናገሩት፤ የመንግሥት ሥርዓት ንጉሰ ነገስታዊ ሥርዓት ስለነበር፤ ንጉሱም ፈላጭ ቆራጭ በመሆናቸው ከዛም ጋር ተያይዞ የንጉሱ ቋንቋ እና ባህል ያይላል፤ ጦሩም ያንኑ ቋንቋ ይናገራል፡፡
ይህ በኢትዮጵያ ሆኗል፡፡ ነገር ግን ችግሩ አማርኛ በብዛት መነገሩ ሳይሆን ያንን ቋንቋ በመጠቀም ሂደት ውስጥ የሌሎችን ቋንቋ በማንቋሸሽ ይህን ቋንቋ ካልተናገሩ በስተቀር የእኩልነት ዜግነታቸው መብታቸው የማይጠበቅበት ሁኔታ ስለነበር የዛ ብሶት እና ንዴት የብሔር ፓርቲን ፈጥሯል ባይ ናቸው፡፡
ነገር ግን ፖለቲካ ፓርቲዎች መደራጀት ያለባቸው በሃሳብ ሊሆን ይገባል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ የብሔር ፖለቲካ ከፋፋይ ነው፡ ፡ ወደ ግጭት እንዲያመሩ ይገፋፋል በማለት ከላይኞቹ የተለየ ሃሳብ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ዶክተር ዓለሙ አንዱ ስልጣን ላይ ወጥቶ ሌላውን ይጎዳል የሚል እምነት እንደሌላቸው አስታውቀው፤ የፓርቲዎች በብሔር መደራጀት ስጋት መሆን የለበትም የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ሞላም የብሔር ፓርቲ ብሔሮች እኩል መብት እስከ ሚኖራቸው ድረስ መኖራቸው ችግር የለውም፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በተግባር ብሔራዊነት እያለ ስለብሔር ሲነሳ እንደ ስህተት የሚቆጥሩ አሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ትክክል አይደለም ካሉ በኋላ፤ አሁንም እንደ አናሳ እንታያለን የሚሉ ብሔረሰቦች እንጨፈለቃለን የሚል ስጋት ስለሚኖራቸው የራሳቸውን ጠንካራ ድርጅት በመፍጠር ይንቀሳቀሳሉ፡፡
ስለዚህ አሁን ላይ የብሔር ፓርቲ በዚህ ጊዜ ማስቀረት አይቻልም፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነታ ይህ ነው፡፡ ህገመንግስት ካልተከበረ፤ ሁሉም ቋንቋ፣ ሁሉም ባህል፣ ሁሉም ሃይማኖት እኩል መሆኑ ካልተረጋገጠ በግድ ወደ አንድ ማምጣት አይቻልም፡፡ እንደ አቶ ሞላ ገለፃ፤ አንዳንዱ በኢኮኖሚ እኔ
ምህረት ሞገስ