የፌዴራል ትራስፖርት ባለስለጣን በበጀት ዓመቱ ሊያስጀምራቸው ካቀዳቸው የቃሊቲ መናኸርያ እንዲሁም የቃሊቲ ትራንስፖርት ማኔጅመንትና ትራፊክ ደህንነት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዘመናዊ መልክ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።
ለቃሊቲ መናሃርያ ግንባታ ብቻ የተያዘለት በጀት 445 ሚሊዮን ብር መሆኑ የትራንስፖርት ሚኒስተር ዲኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግኢኣበሄር ገልፀዋል። የመናኸሪያው ስፋት 37‚366 ካሬ ሜትር፣ የወለሉ ብዛት G+4 ሲሆን በውስጡም ራሱን የቻለ የስብሰባ አዳራሽ፣ ሱፐርማርኬት፣ የመንገደኞች ማረፍያ፣ የተለያዩ ቢሮዎች፣ የጠፉ እቃዎች ማሰቀመጫ መጋዘኖች፣ ባንኮች፣ በቂ የመኪና ማቆምያና መጫኛ ቦታና ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች እንደሚኖራቸው ሚኒስተረ ዲኤታዋ ገልፀዋል።
ግንባታው “FE Construction Plc” በተባለው ኮንትረታክተር የሚገነባ ሲሆን ለመጠናቀቅም አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚወስድ እንደሆነና መናኸርያው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ አሁን የሚታዩ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀርፍ ሚኒስትር ዴዔታዋ አክለው ገልፀዋል።
የቃሊቲ ትራነስፖርት ማኔጅመንትና ትራፊክ ደህንነት ማሰልጠኛ ኢንስቲዩት ግንባታው በተመለከተ 382 ሚልዮን ብር በጀት የተያዘለት ሲሆን በ 5093 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ በሶስት ህንፃዎች የተዋቀረ መሆኑ የፌደራል ትራስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ ገልፀዋል።
1ኛው ህንጻ G+3 የስልጠና ከፍሎች፣ 2ኛው B+G+5 የሰልጣኞች ማደርያ፣ 3ኛው ህንፃ ደግሞ B+G+9 የአስተዳደራዊና ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍሎች ክሊኒክ፣ ቤተ መፃህፍት፣ ቢሮዎች፣ ጂምናዝየም፣ የመኪና ማቆምያ ክፍሎችን እንደሚያጠቃልል ዳይሬክተሩ ተናገረዋል።
ግንባታው እስከ 2013 ዓ/ም ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ስራ ሲጀምር በዘርፉ በርካታ ለውጦችን እንደሚያመጣ ታመኖበት እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል።
ማዕረግ ገ/እግዚአበሔር