አዲስ አበባ፦ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች የእርስ በእርስ ረብሻ በማስነሳታቸው 15 ሰዎች መጎዳታቸውን የፌዴራል ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ገለጸ።
የፌዴራል ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት አስተዳዳሪ ኮማንደር ተክሉ ለታ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በአሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተነሳ የቡድን ፀብ ምክንያት በ15 የህግ ታራሚዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ጉዳት ከደረሰባቸው የህግ ታራሚዎች መካከል ስምንቱ ህክምና ተደርጎላቸው ወደማረፊያቸው ተመ ልሰዋል።
እንደ ኮማንደር ተክሉ ገለጻ፤ የቡድን ፀቡ መነሻ በእግር ኳስ ጨዋታ ምክንያት በሁለት ታራሚዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ነው። ከሁለቱም ታራሚዎች ጎን የተሰለፉ ሌሎች ታራሚዎች ጸቡን በመቀላቀላቸው የከፋ ጉዳት ሊደርስ ችሏል። በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለተለያዩ ግንባታዎች ምክንያት የተ ቀመጡ ፌሮ ብረቶች፣ ሚስማር የተቸነከረባቸው እንጨቶችን መጠቀ ማቸውን ገልጸዋል። በተጨ ማሪ በግቢው ከሚገኙ በቆርቆሮ ከተሠሩ ቤቶች ላይ የተገነጣጠሉ እንጨቶችም በመጠቀማቸው ጉዳቱን የከፋ አድርጎ ታል ብለዋል።
ግጭቱ በተከሰተበት ወቅት የማረሚያ ቤቱ ሠራተኞች ባላቸው ኃይል በሙሉ ተጠቅመው ችግሩን መቆጣጠራቸውን አስታውሰው፤ በግጭቱ ምክንያት አንድም የህግ አካል ላይ ጉዳት አለመድረሱን ጠቁመዋል። ከታራሚዎች ጋር በተደረገ ውይይት የተፈጠረው ችግር አግባብ እንዳልነበር መግባባት ላይ ተደርሷል። ታራሚው የፀቡ ዋነኛ ተዋናዮችን በማጋለጡ ጉዳዩን በህግ የማየት ሂደት ተጀምሯል። በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት የዛሬ ሳምንት በተነሳ ግጭት የአምስት ሰው ህይወት ማለፉን የከ ተማው ፖሊስ መምሪያ ማሳወቁ ይታወሳል።
በግጭቱም ሰባት የጸጥታ አካላትና ከ20 በላይ ታራሚዎች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተደረገው ፍተሻም 20 የእጅ ስልኮች፣ ከማ ንኪያና ከመመገቢያ መሳሪያዎች የተ ዘጋጁ ስለታማ መሳሪያዎች፣ አካፋና ዶማ እንዲሁም ለማቀጣጠያነት የሚያገለግሉ «ላይተሮች»፣ ሀሺሽና አሲድ መገኘቱ ይታወሳል። በከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ወይም በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ ከሁለት ሺ በላይ የህግ ታራሚዎች ይገኛሉ። ከዚህ ውስጥ አብዛኛው 10 ዓመት እና ከዚያ በላይ ተፈርዶባቸው የገቡ ናቸው።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ መጋቢት 7/2011
ጌትነት ተስፋማርያም