አዲስ አበባ፦ ኢትዮጵያ በ2011 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት ከበይነ መንግስታት(መልቲላተራል) እና ከመንግስታት ትብብር (ባይላተራል) 85 ነጥብ 629 ቢሊዮን ብር ብድርና እርዳታ መገኘቱ ተገለጸ፡፡ 57 ነጥብ 55 ቢሊዮን ብር ለፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ በፍሰት ተመዝግቧል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በያዝነው የበጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት ከለጋሽ መንግስታዊ ተቋማት ቃል በተገባው(ግኝት) መሰረት በብድር 23ነጥብ201 ቢሊዮን ብርና በእርዳታ 32ነጥብ22 ቢሊዮን በድምሩ 55ነጥብ421 ቢሊዮን ብድርና እርዳታ ተገኝቷል፡፡
እንደ አቶ ሃጂ ገለጻ፣ በመንግስታት ትብብር በብድር 8ነጥብ632 ቢሊዮን ብር እና በእርዳታ 21ነጥብ576 ቢሊዮን ብር በድምሩ 30ነጥብ208 ቢሊዮን ብር ብድርና እርዳታ የተገኝ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ከሁለቱም ምንጮች በግማሽ አመቱ 85ነጥብ629 ቢሊዮን ብር የውጭ ብድርና እርዳታ አግኝታለች።
ለፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ በፍሰት ከበይነ መንግስታት በብድር 21ሺ471 ቢሊዮን ብር፣ በእርዳታ 19ነጥብ1 ቢሊዮን ብር በድምሩ 40ነጥብ566 ቢሊዮን ብር የውጭ ሀብት ፍሰት መገኘቱን፤ ይህ ፍሰት ከባለፈው 2010ዓ.ም የመጀመሪያ በጀት አመት ፍሰት ብር 20ነጥብ967 ቢሊዮን ጋር ሲነፃጸር በ19ነጥብ599 ቢሊዮን ብር ወይም በ93ነጥብ47 በመቶ እድገት ማሳየቱን ጠቁመዋል።
ዳይሬክተሩ በመንግስታት ትብብር በብድር 4ነጥብ592 ቢሊዮን ብር እና በእርዳታ 21ነጥብ576 ቢሊዮን ብር በድምሩ 30ነጥብ208 ቢሊዮን ብድርና እርዳታ የተገኘ ሲሆን፤ ይህ ፍሰት ከባለፈው 2010 ዓ.ም የመጀመሪያ በጀት አመት ፍሰት 29ነጥብ476 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃጸር በ12ነጥብ497 ቢሊዮን ብር ወይም በ42ነጥብ4 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱንም ጠቅሰው፤ በድምሩ 57ነጥብ55 ቢሊዮን ብር ፍሰት የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከባለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው የብድርና እርዳታ ፍሰት 50ነጥብ443 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃጸር በ7ነጥብ1 ቢሊዮን ብር ወይም በ14 በመቶ ከፍ እንዳለ ገልጸዋል።
አዲስ ዘመን የካቲት 2/2011
ሶሎሞን በየነ