ዳንኤል ዘነበ
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአንድ ሀገር ውስጥ የተማረን ዜጋ ከማፍራት ባሻገር የሚፈጠሩ ልዩ ልዩ ችግሮችንና ማነቆዎችን መፍቻ የዕውቀት በሮች ቁልፍ እንደሆኑ ይታመናል። የአንድ ሀገር ጥንካሬም ሆነ ድክመት የሚመሠረተው በእነዚሁ ተቋማት ድክመትና ጥንካሬ ላይ ይወሰናል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደራጁበት፣ የሚዋቀሩበት፣ የሚቋቋሙበት፣ ወዘተ… መንገድ ዓለም አቀፋዊ ደረጃን መሠረት ማድረግ እንደሚኖርባቸው ይታመናል። ይህም በተቋማቱ የትምህርት ጥራት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይታመናል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቹ አዙሪት
የአብዛኛዎቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቻችን የተቋቋሙበትን ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ለዚህም በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብዛት ያላቸውን ተማሪዎች ለመቀበል እንዲችሉ ብቻ ካለምንም አቅምና ቅድመ ዝግጅት በየቦታው እንደሚቋቋሙ የሚደረግ መሆኑን፤ ተቋማቶቹን ለመክፈት አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ፤ አንድ የትምህርት ተቋም ማሟላት የሚገባቸውን መሠረታዊ ቁሳቁሶችና መሣሪያዎች ሳያሟሉ ወደ አገልግሎት የሚሻገሩበት ሁኔታን ታዝበናል።
በዚህ መልኩ እየተቋቋሙ በሚገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቻችን በመሠረታዊ የትምህርት ጥራት ችግር ቢታመሱ የሚገርም አይሆንም። እ.ኤ.አ በ2004 የተደረገ አንድ አገራዊ ጥናት እንዳመለከተው «ከመካከለኛ ውጤት በታች የሚያመጡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም በጅምላ የማለፍ ነገር እየተዘወተረ ነው።
በመጀመሪያ ሣይክል እየተተገበረ ያለው የሁሉም ይለፍ መርህ (automatic promotion) በጥቅሉ ሲታይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነት አነስተኛ ነው። ይህ መርህ የሚደግሙና የሚያቋርጡ ተማሪዎችን ቁጥር የቀነሰ ቢሆንም ትምህርት በጥራት የማዳረስ ፈተና እንዲጋረጥ አድርጓል» ሲል ነበር የትምህርት ጥራት ችግር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቻችን ላይ ዓይኑን አፍጥጦ የሚታይ መሆኑን ያረጋገጠው። የትምህርት ጥራት ችግሩ ተጽዕኖ ተሻጋሪ ነው።
ከኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የመጀመሪያ ዲግሪም፣ ሁለተኛ ዲግሪም ሆነ ሌሎች የትምህርት ደረጃዎች ማሥረጃዎች በዓለም አቀፍ ገበያ ዋጋ ቢስ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። በተቋማቱ የሚገኙ ሀገር በቀል ዕውቀትና የሣይንሰና ምርምር ሥራዎች ሀገር ዓቀፍና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲያጡ አድርጓቸዋል።
ቁጥር ብቻ የሆነው ጥራት አልባው ጉዞ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቹ ከሚቋቋሙበት መንገድ እስከ ትምህርት አሠጣጡ ጥራት ድረስ ያለው ሂደት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለይ ደግሞ በግል ከፍተኛ ተቋማት ላይ ችግሩ ሥር የሠደደ ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህ ረገድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱን ገመና ነጥሎ መመልከት ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመንግሥት ጋር ሲነጻፀሩ ከሁለት እጥፍ በላይ ናቸው። ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት አጀንሲ የተገኘው መረጃ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር 278 መድረሳቸውን ያመላክታል። እነዚህ ተቋማትም በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በየዓመቱ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስመርቃሉ።
በሀገራችን የግል ከፍተኛ ተቋማቱ ላለፉት 20 ዓመታት የትምህርት ኢንዱስትሪውን በመደገፍ በኩል ትልቅ ድርሻን እየተወጡ እንደሆነ ይታመናል። በሀገራችን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥራቸው እንደ አሸን እንዲፈላ ከማድረጉ ትይዩ በተለይ ደግሞ ለጥራት ክብደት አለመስጠታቸው ይገለጻል። ተቋማቱ ‹ሀገሪቱ ያጋጠሟትን ችግሮች በጥናትና በምርምር አስደግፎ ከመፍታት እና የመፍትሄ አካል መሆን አልቻሉም› የሚሉ ጥናትን መሠረት ያደረጉ ትችቶች ይሰማሉ። ከላይ ለመመልከት እንደተሞከረውም በተጨባጭ ችግሩ መኖሩን ተመልክተናል። የግል ከፍተኛ ተቋማትን በተመለከተ ከሰሞኑ ወደ አደባባይ የወጣው መረጃ ደግሞ ስለ ተቋማቱ የነበረውን አተያይ ፍጹም እንዲቀየር ያደረገ ነበር። እጅን በአፍ የሚያስጭን ሆኗል።
ሽግግር – ከትምህርት ወደ ንግድ ማዕከልነት
ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በትምህርት ጥራት ላይ ውይይት አድርገው ነበር። በወቅቱ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ እንዳሉት በሀገራችን በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው ትምህርት የጥራት መጓደል አሣሣቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ዋና ዳይሬክተሩ በመቀጠል፤ «አንዳንድ የትምህርት ተቋማት አሥረኛ ክፍል ላቋረጡ ተማሪዎች ዲግሪ ይሰጣሉ፡፡ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ሰዎችም እንዲሁ ወረቀት እየወሰዱ ይገኛሉ» ነበር ያሉት። በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማሩ ሂደት «ከጥራት የተጣላ መሆኑ ሣያንስ፤ ዲግሪን በሽያጭ እየሰጡ መሆኑ በእጅጉ ያስደነግጣል” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎችም አሉ። ይህ መረጃም የብዙዎችን ልብ በድንጋጤ ቆሞ እንዲቀር አድርጎት ነበር፡፡
በሀገራችን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ጥራት ችግር ያለባቸው ስለመሆኑ ከህብረተሰቡ ያልተሠወረ ቢሆንም፤ በዚህ ደረጃ ከእውቀት ማዕከልነት ወደ ንግድ ተቋማነት ይሸጋገራሉ ብሎ ለመገመት ይከብዳል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱዓለም ከሕዝብ እይታ ተደብቆ የኖረውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ‹ሀገር አፍራሽ፣ ትውልድ ገዳይ› ድርጊትን በግልጽ በማውጣት ያንቀላፉትን ሁሉ ያነቃ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ችግር ዶ/ር አንዱዓለም ከገለጹት ትይዩ፤ ከጥራትና አግባብነት ጋር ተያይዞ ፈታኝ ችግሮች ስለመኖራቸው ተነግሯል። በሀገሪቱ ፈቃድ አውጥተው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሕግ ውጪ በመንቀሳቀስ፣ በትምህርት ጥራት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደሩ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
በሀገራችን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ለሚታዩት ጉድለቶች በመነሻነት ከሚጠቀሱት መካከል ደግም፤ የተቋማት የትምህርት ሥርዓት ዝግጅት ማነስ፣ የመምህራን አቅም ውስንነት፣ ያለ በቂ ዝግጅት ትምህርት ቤቶችን ከፍቶ ለማስተማር መንቀሳቀስና መሰል ዓይነት ችግሮች ይገኙበታል፡፡ በአንዳንድ ትምህርት ተቋማት ደግሞ መቁረጫ ነጥብ ሣያሟሉ ትምህርቶቻቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ከመኖራቸው ጋር የሚያያዝ መሆኑን ኤጀንሲው ያምናል።
ከሀገር አፍራሽ፤ ትውልድ ገዳይ› አካሄድ መውጫ ቁልፍ
በሀገር አቀፍ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር እንደሚለው ግን፤ መንግሥት ተቋማቱን እያገዘ ባለመሆኑ የትምህርት ጥራትና መሠል ችግሮች ለመከሰታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ያመላክታል። የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንደሌሎች ኢንቨስትመንቶች እንዲጠናከሩ ማድረግ ይገባ ነበር። በሀገሪቱ መንግሥት በኩል ለተቋማቱ ድጋፍ በማድረግ እንዲጠናከሩ አልተደረገም።
ይህም የትምህርት ጥራቱን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጎዳው መሆኑን ነው ማህበሩ ያስታወቀው። በሀገሪቱ ከሚገኙት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከራይተው የሚያስተምሩ መሆኑን በማንሳት «አብዛኛዎቹ ተቋማት ቤተ-ሙከራዎች፣ ቤተ-መጽሐፍት፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የጥናትና ምርምር ማዕከላት እና ሌሎች መሠረታዊ ሠርቶ ማሣያዎች ተቋማቱ አሁን በሚገኙበት ቁመና ላይ ማሟላት እንዳይችሉ አድርጓቸዋል።
ይህም የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ሁኔታ እንዲፈጠር አድርጓል ሲል ይሞግታል። የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከነጉድለታቸውም እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ ተደራሽ በመሆኑ ከፍተኛ የተማረ የሰው ኃይል በማምረት ረገድ ትልቅ ሥራን እየሰሩ ይገኛሉ። በተቋማቱ ላይ የሚስተዋሉትን ክፍተቶች መሙላት የሚያስችል አሠራርና ድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም፤ የሪፎርሙ አካልና ባለቤት ማድረግ መቻሉ ችግሮቹን መቀነስ ይቻላል የሚል የመፍትሄ ሐሳብ አቅርበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አድማሱ፤ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚስተዋሉትን ችግሮች መቅረፍ የሚቻለው ርምጃ በመውሰድ ብቻ እንዳልሆነ ይናገራሉ። «ችግሮቹን ለመፍታት ተቀራርቦ መሥራትና መደጋገፍ ይገባል» ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ይህም ሁሉንም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ትክክለኛው መሥመር የሚያስገባ ይሆናል። ከዚህ በኋላ እውቅና የሚሰጣቸው ተቋማት ተመዝነው የጥራት መሥፈርት የሚያሟሉበት ሥርዓት ይዘረጋል።
ኤጀንሲው ለተግባሩ መሣካት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ነው ያስታወቁት ። በተመሣሣይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከሣቱት መንገድ ወደ ትክክለኛው መሥመር የሚመለሱበት ሁኔታ ስለመኖሩ ያመላከቱት የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሣሙኤል ኡርቃቶ ደግሞ የሀገራችንን የሣይንስ ፖሊሲና ስትራተጂ የትኩረት መሰኮች፣ የማስፈፀሚያ ሥልቶች በሚመለከት እውቀትና መረጃን ከማቀናጀት፤ ሀገርበቀል ዕውቀትና የሣይንስና ምርምር ሥራዎች ሀገር ዓቀፍና አለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ከማድረግ አኳያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ማስተካከል የሚገባ መሆኑን ይገልጻሉ።
እነዚህና መሠል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ በሚከናወኑ ሥራዎች የግል ከፍተኛ ተቋማቱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነትና ሚናቸውን ከመረዳት ባሻገር መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ ነበር ያሳሰቡት። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከ‹ሀገር አፍራሽ፤ ትውልድ ገዳይ አካሄዳቸው የመውጫ ቁልፍ ከላይ የተዘረዘሩትና መሠል ሐሳቦችን ወደ ተግባር መቀየሩ ችግሩን የሚቀይር መሆኑ ተጠቁሟል። ይህም ከጥራት የተጣሉትን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ትክክለኛው መሥመር እንደሚመልሱ እምነት ያሣድራል ባይ ነን።
የተለያዩ በባህሪ ለውጥ የሚገለጹ ምልክቶች ለምሣሌ ከንፈር መምጠጥ፣ መሣቅ፣ መሮጥ፣ ራቁት መሆን፣ መቆጣትና ሥሜታዊነት ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በኋላ የሚከሰቱት በአብዛኛው መርሣት፣ ከባድ እንቅልፍ እና ራስ ምታት የመሣሠሉት ናቸው።
ስታተስ ኢፒለፕቲክስ፤ ይኼኛው በተደጋጋሚ የሚከሰት የሚጥል በሽታ /የኢፒለፕሲ ምልክት ነው። ብዙ ጊዜ የሚከሰተው መድሃኒት በድንገት በማቋረጥ ወይም በመመረዝ ምክንያት ነው። ይህ ችግር ሲከሰት ፈጥኖ ሐኪም ቤት ካልተወሰደና ተገቢውን አስቸኳይ የመድሃኒትና ሌላ የሕከምና ዕርዳታ ካልተደረገለት ሞትን ሊያስከትል ይችላል።
ፌብራይል (ከትኩሳት ጋር የተያያዘ)፤ ይኼኛው ዓይነት ሕመም የሚከሰተው ሕፃናት ላይ ነው። ይህንን ሕመም የሚያስከትሉ የትኩሣት በሽታዎች ናቸው። ይህም ማለት እንደ ጉንፋን፣ የጆሮ ኢንፌክሽንና ሌሎች ከባድ ትኩሣት ለያስከትሉ የሚችሉ ሕመሞች ናቸው። በዚህ ወቅት በቀዝቀዛ ፎጣ ትኩሣትን ማብረድ እና ሕፃኑን ለምርመራ መውሠድና ተገቢውን ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ የግድ ነው።
ሕመምተኛው ማድረግ ያለበት ጥንቃቄ፤ የአካልና የአዕምሮ ጤንነትን መጠበቅ፣ በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮችን አለመጠቀም፣ ጭንቀትን ማራቅ፣ መጠነኛ የሆነ ስፖርትን አዘውትሮ መሥራት፣ በሽታውን ከሚያባብሱ ነገሮችን ማራቅ ማለትም ብርሀን የበዛበት ነገር እንደ ቴሌቪዥን የመሣሠሉት ነገሮች ላይ ረዥም ቆይታ አለማድረግ ናቸው።
በግራንድማል ሲዠር (ሰዎች ራሳቸውን ሠተው በወደቁ ሰዓት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች) ሕመምተኛውን ከውሃ አካባቢ፣ ከእሣት አካባቢ እና ከመኪና መንገድ ማራቅ ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ከሕመምተኛው አካባቢ ማራቅ ልብሶቹን ማላላት፣ መነጽር ማውለቅ ከጭንቅላት ሥር ለስላሣ ነገር ማድረግ ሕመምተኛውን በአንድ ጎን ማስተኛት ሕመምተኛው እስኪነቃ ድረስ ከሕመምተኛው ጋር መቆየት አስፈላጊ ነው።
በግራንድማል ሲዠር (ራሳቸውን በሣቱበት ሰዓት የማይደረጉ ነገሮች) በአፍ ውስጥ ምንም ዓይነት ነገር አለመክተት፣ ክብሪት ጭሮ አለማሽተት፣ የሚጠጣ ነገር አለማጠጣት፣ ማንቀጥቀጡን ለማስቆም አለመሞከር፣ ለሚጥል ሕመም (ኢፒለፕሲ) የሚሰጡ የሕክምና አገልግሎቶች የሚጥል በሽታ ሕክምና ከጥቂት ዓመታት እስከ ዕድሜ ልክ ክትትል ሊያስፈልገው የሚችል የሕመም ዓይነት ነው። የቅርብ ክትትልና ቁጥጥርም ያስፈልገዋል። አንድ ጊዜ ሕክምና ከተጀመረ ሐኪሙ መድሃኒቱን መውሰድ አቁም እስከሚል ድረስ ታማሚው መድሃኒቱን በታዘዘለት መጠን እና ሰዓት መውሰድ አለበት።
መድሃኒቱን በድንገት ማቋረጥ ሀይለኛ የሚጥል በሽታ እንዲያገረሽ ያደርጋል። በሽታው መጣሉን ቢተውም እንኳን መድሃኒቱን ማቋረጥ አይገባም። ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች መድሃኒቱን ሕፃናት በማይደርሱበት ቦታ ማስቀመጥ ሩቅ መንገድ ከሄዱ መድሃኒቱን ይዞ መሄድ መድሃኒቱን ሙሉ በሙሉ ከመጨረሱ በፊት ሌላ ተጨማሪ ማሣዘዝ ናቸው።
ህብረተሰቡም የሚጥል ሕመም የማይተላለፍባቸው መንገዶች በአግባቡ በማወቅ ሕመሙ ያለባቸውን ሰዎች አደጋ እንዳይደርስባቸው መርዳት ይገባዋል። በሽታው የማይተላለፍባቸው መንገዶች በንክኪ፣ በምራቅ፣ በሕመሙ ምክንያት የወደቀውን ሰው በመርዳት አይተላለፍም። የሚጥል በሽታ እርግማን አይደለም። ሕክምናም አለው። በሕክምና ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል መቆጣጠር ይቻላል። የሚጥል በሽታ መድሃኒት በየቀኑ ሣይቋረጥ ረዘም ላለ ጊዜ መወሠድ አለበት። ለሁሉም ሕመሞች ቅደመ ጥንቃቄ የማይተካ አማራጭ ነው።
አዲስ ዘመን የካቲት 08 /2013