ዳንኤል ዘነበ
በየትኛውም የዓለማችን ክፍል በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መንገድ የሚሰጡ ትምህርቶችን ውጤትና የተማሪዎች የዕውቀት ጥግ ለመለካት ምዘና ማካሄድ የተለመደ ጉዳይ ነው። በተለይ በዘመናዊ የትምህርት ስርዓት ውስጥ የትምህርት ምዘና ከመማር ማስተማሩ ሂደት ጎን ለጎን በእኩል ዓይን ይታያል።
የተለያዩ ሀገራት በፈተና/ምዘና ስርዓት ሂደታቸው ላይ የተለያዩ የልኬት ደረጃና የምዘና ዘዴ የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገ የፈተና እና የምዘና ስርአትን በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።
በአብዛኛው የዓለማችን ክፍል የሚጠቀምበት ወረቀትና እርሳስን መሠረት ያደረገውን የፈተና ስርዓት ነበር። የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለዘመናዊው የማህበረሰብ ግንባታ ዋነኛው አማራጭ ሆኖ መጥቷል።
ይሄንኑ ተከትሎ በትምህርት ዘርፍ ተራማጅ ውጤት ለማምጣት አጋዥነቱ ጎልቶ የሚጠቀሰው የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አንዱ ክፍል ወደ ሆነው ኮምፒዩተርን መሰረት ወዳደረገው የፈተና እና የምዘና ስርአት ተሸጋግሯል። ኮምፒዩተርን መሠረት ያደረገ የፈተናና የምዘና ሥርዓት ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በተለያዩ መልኮች ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።
የሀገራት ተሞክሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ተቀባይነት ከማግኘት ባሻገር በስፋት እያገለገለ በሚገኘው ኮምፒዩተርን መሰረት ባደረገ የፈተና ስርዓት በርካታ ሀገራት ውጤታማ ሆነዋል።
ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ቀረብ ሊሉ የሚችሉትን እንደ ናይጄሪያ፣ ግብጽ፣ ኢንዶኔዥያ ያሉ ሀገራት ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና በመጠቀም ተማሪዎቻቸውን በመመዘን እጅግ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ በመሆን ረገድ ይጠቀሳሉ።
እነዚህ ሀገራት ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ የፈተና ስርዓትን ለመገንባት ያለፉበትን ተሞክሮ ሀገሮቹ ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ የህዝብ ብዛት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና የምጣኔ ሀብት ደረጃ ያላቸው ናቸው። በተጨማሪም እንደ ጆርጂያ፣ ፊንላንድ፣ ሆላንድ እና ፈረንሳይ የመሳሰሉ የበለፀጉ ሀገራት ተሞክሮ፤ ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና ስርዓትን መዘርጋት መቻል ያለውን ፋይዳ ያመላክታል።
የሀገራችንን የፈተና ስርዓት የማዘመን ሂደት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የተማሪዎች ምዘና ስርዓት ባህላዊ ነው። በሀገራችን ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው ባህላዊ የፈተና ስርዓት እጅግ በጣም ውስብስብ፣ አድካሚና ከፍተኛ ወጪ የሚያሳጣ፤ ለስርቆት፣ ኩረጃና ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚዳርግ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል።
በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በተመሳሳይ ችግሮቹ እንዳሉ በማመን መፍትሄ ፍለጋ ሲዳክር ይስተዋላል። ኤጀንሲው ከፈተና ስርዓቱ ጋር ተያይዞ ለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ ለማበጀት ባለፉት ዓመታት ጥናቶች ሲያካሂድ ነበር። ከባህላዊ የፈተና /ምዘና ስርዓት በመውጣት ወደ ዘመናዊ ስርዓት መሸጋገርን የመፍትሄ ቁልፍ እንደሆነ በማመን እንቅስቃሴ ከጀመረ ውሎም አድሯል።
ሪፎርም የሚሻው ባህላዊ የፈተና ስርዓቱን ከላይ የተጠቀሱትን ሀገራት ተሞክሮ መሠረት በማድረግ ኮምፒዩተርን መሠረት ወደ አደረገ የፈተና ስርዐት መሸጋገር የተሻለ መፍትሔ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ የፈተና ስርዓት መዘርጋቱ ችግሮቹን ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ ባይቻልም በከፍተኛ ሁኔታ ማቃለል እንደሚያስችል በማመን በቅርቡ ተግባራዊ ለማድርግ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።
በሀገራችን ተግባራዊ የሚደረገው ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገው የፈተና ስርዓት በነባሩ የአመዘጋገብ ስርዓት ሲፈጠሩ የነበሩና የተፈታኝ ተማሪዎችን የወደፊት እድል የሚያበላሹ በርካታ ችግሮችን መቅረፍ ያስችላል፡፡ ከዚህ አኳያ በወረቀትና በእርሳስ ከሚሰጠው የፈተና ስርዓት ያሉትን ጥቅሞች መመልከቱ ያስፈልጋል።
የፈተና ደህንነትን ማስጠበቅ በኮምፒዩተር ላይ የተመሰረተ ፈተና የመጀመሪያው ከፈተና ደህንነትን ከማስጠበቅ አኳያ ያለው ጠቀሜታ ይጠቀሳል። በወረቀት እርሳስ ምዘና አሰጣጥ እያንዳንዱ የፈተና ወረቀት፣ የማስተላለፊያ ሂደት ውስጥ ፈተናው ለአደጋ ሊጋለጥ ወይም ሊሰረቅ የሚችልበት ሁኔታ አለ። በፈተና ስርዓቱ ክፍተት የሚፈጥሩ ችግሮችን ኮምፒዩተርን መሰረት ባደረገ የፈተና /የምዘና ስርዓት ወቅት መፍትሄ ያገኛሉ። መልካ ምድራዊ ሁኔታ አልያም የተፈታኙ መሠረት ምንም ይሁን ምን ሁሉንም የደህንነት አደጋዎች ይቀንሳል።
በርካታ የታተሙ የፈተና ወረቀቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉትን መጠነ ሰፊ የስርቆትና የመጥፋት አደጋዎች በመቀነስ ከደህንነት ጋር ተያይዞ ሲፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል። በተማሪዎች መካከል መኮራረጅ እንዳይኖር በማድረግ ብሎም ሌሎች አድካሚ የስራ ሂደቶችን ማቃለል ያስችላል።
ከተለዋዋጭነት አኳያሌላው የተለዋዋጭነት አኳያ ሲሆን፤ ኮምፒዩተር ላይ የተመሰረተ ፈተና በምዘና አስተዳደር መስኮች በኩል ተለዋዋጭ ፈተናዎችን ያቀርባል። የአቅርቦት ሞዴሎቹ የተሟሉ ሆነው የሚገኙት በወረቀት እርሳስ ፈተና/ምዘና እንጠቀም ከነበረው አስተዳደር መስኮቶች ጀምረው በተከታታይ እንደ አስፈላጊነቱ ለአንድ የተወሰነ ፕሮግራም የተመረጠው አስተዳደራዊ አካሄድ የተፈታኞችን ተደራሽነት፣ ደህንነት፣ የቅንብር መንገዶች፣ የህትመት ድግግሞሽ እና ስታንዳርድ ማውጣትን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያካትታል።
በወረቀት ላይ ከተመሰረተው ጋር ሲነጻጸር የተፈታኙን ተደራሽነት ማሻሻል የሚችለው ከፍላጎት እና አቅርቦት ጋር ሲነጻጸር የደህንነት ተጽእኖ ቀለል ማድረግ የሚችለውን ውስን የአስተዳደር መስኮቶችን የጊዜ ሰሌዳ ማስያዝ ይቻላል።
የፈተና ውጤትን በፍጥነት ይፋ ማድረግ ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና የውጤት ሪፖርቶች በፍጥነት እና ትክክለኛነትን ይጨምራል። የምዘና ሰጪው ተቋምም የመፈተኑ ሂደት እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የፈተናውን ውጤቶች ለተፈታኞቹ የማቅረብ አማራጭ አላቸው። ይሁን እንጂ ፈተናው መጠናቀቁን ብቻ ለማረጋገጥ ውጤቶቹ እስከሚቀጥሉ ቀናት ሊቆዩ ወይም ሊዘገዩ ይችላሉ።
አስቸኳይ ውጤት ሪፖርት ለማድረግ ብዙውን ጊዜ በኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና ይጠበቃል፤ ከይዘት እና መቁረጫ ነጥብ ጋር በተያያዘ ሁሉም ፎርሞች ሚዛናዊ እንዲሆኑ ይጠይቃል። ወዲያውኑ ፈተናዎችን ማረም በጥያቄ ባንክ መጠን፣ በጥያቄ ምርጫ፣ ፎርሞች ማደራጀት እና ስታንዳርድ ማውጣት ላይ ተጽእኖ አለው።
ወጥነትበወረቀት እና እርሳስ የምዘና ዘዴ አካባቢ ውስጥ ያለው አለመመጣጠን የምዘና ውጤቶች የፈታኞችን እውነተኛ ችሎታ የሚያንፀባርቁ አይደሉም ማለት ይቻላል። ለምሳሌ በትልቅ የመፈተኛ ክፍል ውስጥ ፈተና በሚወሰድበት ወቅት ሊኖሩ የሚችሉ መረበሽን ማየት ይቻላል። ስለሆነም ቁጥጥር ከሚደረግባቸው አካባቢዎች ውስጥ ኮምፒዩተር ላይ የተመሠረተ ፈተና የምዘና ማዕከላት መኖራቸው ይበልጥ አስተማማኝ ውጤቶችን በሚያስገኘው የፈተና አካባቢ ውስጥ ወጥነትን በጉልህ ያረጋግጣል።
በዳታ የበለፀገ የምዘና ውጤት ትክክለኛ የመለኪያ አስፈላጊነት በሁሉም የሙከራ መርሃ ግብር ማዕከል ላይ እንደሚገኝ ይታመናል። የወረቀትና እና እርሳስ ምዘና ለቀላል ትንታኔ አስፈላጊ የሆኑትን መሠረታዊ መረጃዎችን ብቻ ይሰጣል። ከእነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ባሻገር በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ የምዘና አሰጣጥ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ሰዓትን የእረፍት ጊዜን እያንዳንዱ የጥያቄ ክፍል የሚወስደውን የጊዜ መጠንን እና የዳሰሳ ጥናት ምላሾችን ጨምሮ በርካታ መረጃዎችን ያቀርባል።
እንደ ነጻ አወቃቀር ጽሁፍ እና መጣጥፎች ያሉ የተገነቡ ምላሾች በእጅ ከተጻፉ ምላሾች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃዎች ሳይኖሯቸው በኤሌክትሮኒክስ በቀላሉ ሊመዘገቡ፣ ሊሰበሰቡ ይችላሉ። ሊጠፉ እና ብዙ ጊዜ ሊቀየሩ ከሚችሉ ከወረቀት እና እርሳስ ምላሾች በተቃራኒ በኮምፒዩተር ላይ የተመሰረቱ ምዘናዎች ሁሉንም ምላሾች የቁልፍ ጭረት (key stoke) በመባል በሚታወቅ ሂደት ይመዘገባሉ። ይህ እጅግ በጣም የበለጸገ የአቀራረብ ዘዴ ነው። ተፈታኙን እና የምዘና ባህሪያትን ለመገምገም እንዲሁም ለደህንነት ምርመራዎች የመረጃ ምንጭ መኖር አስፈላጊ ነው።
አዲስ ዘመን ጥር 24/2013