
አዲስ አበባ ፦ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮረና ቫይረስ ተጨማሪ 118 ሰዎች ማገገማቸው ተገለጸ ። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 738 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
የውጭ
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 5 ሺ 102 ሰዎች መካከል 109 ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው 60 ወንድ እና 49 ሴት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ1 – 78 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆኑንም አመልክተዋል ።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው 81 ከአዲስ አበባ ከተማ፣ 3 ከአማራ ፣ 9 ከኦሮሚያ፣ 2 ከሀረሪ ፣ 3 ከአፋር ፣ 3 ከትግራይ፣ 4 ከሶማሌና 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል መሆኑ ተጠቁሟል።
ሚኒስትሯ እስካሁን በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይ ረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3630 መሆኑን፣ ከእነዚህ ውስጥ 2829 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ መሆናቸውንና 32 ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል እንደሚገኙ ጠቁመው፤ እስካሁን ለ 192 ሺ 087 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ መሰራቱን ገልጸዋል።
በቫይረሱ በአጠቃላይ የ61 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ ሁለት የውጭ አገር ሰዎች ደግሞ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ አይዘነጋም።
አዲስ ዘመን ሰኔ 10/2012
በጋዜጣው ሪፖርተር