አዲስ አበባ፡- በአዲስ አበባ ቤት ለቤት ደረቅ ቆሻሻ የሚያነሱ ማህበራት ሰራተኞች ለኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንዳይሆኑ ለማድረግ የደህንነት መጠበቂያ እቃዎች እየተሰጣቸው መሆኑ ተገለጸ።
በአዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ የግንዛቤ ስርፀትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ሂርጳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ በኋላ ቤት ለቤት የሚደረገው ቆሻሻ ማሰባሰብ ላይ የተለወጠ አሰራር ባይኖርም፣ ቤት ለቤት እየዞሩ ቆሻሻ የሚሰበስቡት ሰራተኞች የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አቅጣጫ ተቀምጧል። ሰራተኞቹ ርቀታቸውንና ንፅህናቸውን ጠብቀው እንዲሰሩ የተለያዩ ቁሳቁስ ተሰጥቷቸዋል።
ሰራተኞቹ በቀን ሁለቴ ቆሻሻዎችን በየተመደቡበት ቦታ እንዲያወጡ እየተሰራ መሆኑን አቶ ምትኩ ጠቅሰው፣ ቆሻሻ ከየቤቱ በሚሰበስቡበት ወቅት የተለየ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል። በከተማው የሚገኙት ማህበራት ስለ ቫይረሱ ግንዛቤ እንዲያገኙ የማድረግና የደህንነት መጠበቂያ እቃዎች እየተሰጣቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
ኤጀንሲው ገንዘብ ወጪ አድርጎ የተለያዩ ድጋፎች እያደረገ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ ምትኩ፤ የቆሻሻ አሰባሰብ ስራው ምንም እንከን ሳይገጥመው እየተከናወነ እንደሚገኝ አመክልተዋል። የደህንነት መጠበቂያ ግብዓት እጥረቶች መጀመሪያ አካባቢ እንደነበረ አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ችግሮቹ መፈታታቸውን ጠቁመዋል።
አዲስ ዘመን ሰኔ 9/2012
መርድ ክፍሉ
ለማህበራቱ የደህንነት መጠበቂያ እቃዎች እየተሰጣቸው እንደሚገኝ ተገለጸ