ከወራት በፊት ለአንድ ዓላማ ነበር «የብሎኬት አካባቢ የጥምቀት በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ» በሚል ስያሜ ተሰባስበው በመምከር በጋራ መስራት የጀመሩት። ይሄም በዩኔስኮ የተመዘገበው የጥምቀት በዓል የዓለም ቅርስ መሆን ስለቻለ ለበዓሉ ድምቀት የድርሻቸውን ለመወጣት እና በ2013 ዓ.ም በቂ ዝግጅት ለማድረግ ነበር መነሻቸው። እናም ለበዓሉ መዘጋጀት፤ ለበዓሉ የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ ለማሟላት የሚያስችላቸውን አስፈላጊውን ሀብት ከማህበሩ ወጣቶች ማሰባሰብም ይጀምራሉ።
በዚህ ላይ እንዳሉ ግን እንደ አገር ሳይሆን እንደ ዓለም የሰው ልጆችን አቅም የፈተነ፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ሕይወት የቀጠፈና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችንም ከአልጋ ያዋለ የኮሮና ወረርሽኝ ተከሰተ። የችግሩን አሳሳቢነት ብቻ ሳይሆን የመከላከያ መንገዱን የተረዱት እነኚህ ወጣቶች ደግሞ በሽታው በኢትዮጵያ መከሰቱን እንደሰሙ ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሕዝብን ከበሽታው መከላከል የሚችሉበትን አቅጣጫ አሰቡ። ለዚህ ደግሞ ቀደም ብለው ለጥምቀት በዓል ድምቀት ሲያደርጉ የነበሩት ዝግጅት ለዚህ ተግባር ለማዋል ወሰኑ፤ እናም አደረጉት።
ፈረንሳይ 06 ብሎኬት ገበያ አካባቢ ከወጣት ማዕከሉ ፊት ለፊት ባለ ቦታ ላይ እጅ የማስታጠብና ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር ላይ ተሰማሩ። ወጣት ይታየው ተመስገን፣ በብሎኬት ገበያ አካባቢ ተወልዶ ያደገና እዚያው እየኖረ ያለ የማህበሩ/ኮሚቴው አባል ነው። ወጣት ይታየው እንደሚናገረው፤ ለበዓሉ ዝግጅት እያደረጉ ባለበት ወቅት ወረርሽኙ ተከሰተ። ከዚያም ለወገኔ ምን ላድርግ የሚል ሀሳብ አንስተው በመምከር እጅ ማስታጠብ ጀመሩ። ይህ ደግሞ እጅ በማስታጠብ እንኳን በሽታውን መከላከል እንደሚቻል በባለሙዎች የተነገረውን ታሳቢ በማድረግ ሲሆን፤ ወደዚህ ሥራ ሲገቡ ግን ከማንም ድጋፍ ሳይጠይቁ ከማህበሩ በተዋጣ ገንዘብ ዕቃዎችን በመግዛት ነበር።
ምክንያቱም እነርሱ በዚያ ቦታ እጅ በማስታጠብ ወገን ማዳን ከቻሉ 50 እና 100 ብር አውጥተው ሥራውን ቢጀምሩ ከምንም በላይ ለእነርሱ ዋጋ አለውና ነው። እናም ይሄን የተገነዘቡ 18 ወጣቶች ሥራውን እውን አደረጉት። ዋናው ነገር መጀመር ነውና፤ ሥራቸው ውሎ ሲያድር እነርሱም እየተበረታቱ፤ አንዳንድ ሰዎችም ሳሙና በመግዛት ጭምር ይደግፏቸው ጀመር። ከኅብረተሰቡ የሚያገኙት የሀሳብም የዓይነትም ማበረታቻ እነርሱም እንዲተጉ አደረጋቸው። እናም እጅ ከማስታጠብ ባለፈ ስለበሽታው በማስተማር፣ ሰዎች እጃቸውን እንዲታጠቡ በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ማከናወናቸውን አጠናከሩ።
እንደ ወጣት ይታየው አባባል፤ አሁን ላይ 50 በመቶ ያክሉ ኅብረተሰብ ሥራ ላይ አይደለም፤ ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸውም 100 በመቶ ተማሪዎች ከቤት ናቸው። ይህ የሆነው ደግሞ በሽታውን ከመከላከል አኳያ ኅብረተሰቡም ሆነ ተማሪዎች በቤት እንዲውሉ ለማድረግ ቢሆንም፤ በአመዛኙ ከቤት ይልቅ ውጪን፣ ተራርቆ ከመሄድ ይልቅ አንድ ላይ ታጅቦና ተቃቅፎ ነው የሚስተዋለው።
መጠጥ ቤቶች፣ የወጣት ማዕከላትና ሸማቾች አካባቢ ያለው የሰዎች ትፍፍግ ደግሞ ለወረርሽኙ መድኃኒት ተገኝቷል የተባለ ነው የሚመስለው። ለምሳሌ፣ መጠጥ ቤቶች ማታ ማታ ቢዘጉም ቀኑን ሙሉ ሲሰሩ ነው የሚውሉት። ይህ ደግሞ ለበሽታው መስፋፋት ሚናቸው የጎላ ነው። ኅብረተሰቡ ደግሞ በራሱ ላይ ካልደረሰ የሚያምን መስሎ እየታየ አይደለም። እነርሱም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት እጅ የማስታጠብ ተግባር ላይ ቢሆኑም፤ ከተወሰኑት በስተቀር ለመታጠብ እንኳን ፈቃደኛ አይሆኑም። ይህ ደግሞ ሕዝቡ ከመስማት ባለፈ ጉዳዩን ተገንዝቦታል ለማለት አያስደፍርም። እነርሱም ይሄን እጅ የማስታጠብና ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ የሚያከናውኑት ከሰው ሕይወት አይበልጥምና ሥራቸውን ትተው ነው። በመሆኑም ወጣቱ፣ ኅብረተሰቡ፣ የመንግሥት አካላትና ሌሎችም የሚመለከታቸው ተቋማት የሚጠበቅባቸውን መወጣት ይገባል።
በዚህም ሕዝቡ ከመንግሥትም ከጤና ባለሙያዎችም የሚተላለፈውን መልዕክት ተረድቶ ቢጠብቅ፤ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በየቦታው ያዘጋጁትን የእጅ ማስታጠብ ተግባር ተባባሪ ሆኖ ቢታጠብ፤ የመንግሥት አካላትም እንደ መጠጥ ቤት፣ ወጣት ማዕከላትና ሌሎች ሕዝብ የሚተፋፈግባቸው አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህ ሲሆን ችግሩን ሳይብስ መከላከልና የሚደርሰውን ጉዳት ማስቀረት ይቻላል።
እናም የዛሬ መራራቃቸው ስለምወድህ ነው ብለው ሊያስቡ ይገባል፤ ወደቤት ሲገቡ ቤት ውስጥ እናት አባት የሚወዱት ልጅና ባለቤት መኖራቸውንም ማሰብ ይገባል። ሌላው የኮሚቴው አባል ወጣት ሐብታሙ ክፍሌ በበኩሉ እንደሚናገረው፤ ይህ ሥራ ያለማንም ገፊነት ከምንም በላይ ወገንን አስቀድሞ መስራትን መሠረት ያደረገ ሲሆን፤ እጅ የማስታጠብና ስለ በሽታው ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ የምናከናውንበት ነው። ይህ ደግሞ ወረርሽኙ ጊዜ የማይሰጥ፣ ተይዞ ከመቸገር ይልቅ ቀድሞ በመጠንቀቅ መከላከልና ችግሩን ማቃለል እንደሚቻል ተገንዝበን እየሰራን ያለንበት፤ ለሌሎችም በተግባርም በቃልም የምናስተምርበት ነው።
አገልግሎቱን እየሰጡ ያሉበት ቦታም የገበያ ስፍራ ነው፤ የታክሲም ፌርማታ ነው፤ በርካታ ሰዎች የሚወጡ የሚወርዱበት አካባቢ ነው፤ የወጣቶች መዝናኛና መጠጥ ቤቶችም ያሉበት በጥቅሉ በርካታ ሰዎችን ተደራሽ ማድረግ የሚቻልበት ነው። ሥራውንም ይሄን ታሳቢ አድርገው የጀመሩት ሲሆን፤ እጅ በማስታጠቡም ሆነ ግንዛቤ በማስጨበጥ ሂደቱ በርካታ ሰዎችን ተደራሽ ማድረግ የሚችሉበትን ዕድል ፈጥሮላቸዋል። ይሄን በማድረጋችንም አንድም ወገናችንን ለመታደግ የድርሻችንን የተወጣንበት፤ ሁለተኛም የመንግሥትንና የጤና ባለሙዎችን መልዕክት ተግብረን እንዲተገበር ያደረግንበት ሲሆን፤ ተግባሩም ከምንም በላይ የህሊና እረፍትና እርካታን የሚፈጥርም ነው።
እርሱም ይሄን ሥራ ሲሰራ የታክሲ ሥራውን ትቶ ነው። ተግባሩም ሥራ የሚሰራው ሕዝብ ሲኖር ነው በሚል ለሌሎች ቅድሚያ የመስጠት እርምጃ ነው። ሆኖም አሁንም ግንዛቤው የሌላቸው በርካታ ሰዎች አሉ። ይህ ደግሞ ከእኛው ጀምሮ በሚኖር መዘናጋት የሚገለጽ ሲሆን፤ ከቤተሰብ ጀምሮ የትምህርት ቤት መዘጋትን ዓላማ በመዘንጋት ስለ ልጆቻቸው ግድ ማጣት መኖሩን በሚያሳይ መልኩ ኃላፊነትን አለመወጣት ይስተዋላል።
በመሆኑም ችግሩ ሳይቃጠል በቅጠል እንደመሆኑ፤ ከቤት እስከ መንግሥት አሁንም በመከላከሉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል። ወጣት ባህራን እሸቱ በበኩሉ እንደሚለው፤ ሥራውን ሲጀምሩት ሰዉ ላይቀበላቸውና ለመታጠብም ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት ነበረባቸው። ይሁን እንጂ ስፍራው በርካታ የንግድ፣ የገበያ፣ የመጠጥ ቤቶች፣ የታክሲ ፌርማታና የወጣት ማዕከላትን ዓይነት የበርካታ ሰው እንቅስቃሴ የሚስተዋልበት እንደመሆኑ ሰዉ ለመታጠብ እምብዛም አላስቸገረም።
አንዳንዱ ደስተኛ ሆኖና አመስግኖ፣ አንዳንዴም ማስተካከል ያለብንን ነገር አስተያየት ሰጥቶም ነው ታጥቦ የሚሄደው። ይሄን ስንሰራ በአብዛኛው ቦታ ሰዎች ውሃን እየከፈቱና እየዘጉ የሚታጠቡበትን እና ንክኪን ባስቀረ መልኩ ነው። ይህ ተግባር በተለያየ ምክንያት ከቤት መቀመጥ ላልቻሉ ወገኖች፣ ቶሎ ቶሎ ውሃ አግኝተው መታጠብ ለማይችሉ፣ ገበያ ገብተው ለሚወጡ፣ ከታክሲ ወርደው ወደቤታቸው ለሚሄዱና ሌሎችም ወገኖችን ታሳቢ አድርጎ የተጀመረ ሲሆን፤ ትልቁ ዓላማም ሰዎች በተለያየ ምክንያት ብዙ ንክኪ ስለሚፈጥሩ ቶሎ ቶሎ ንጽህናቸውን መጠበቅ የሚችሉበትን ዕድል መፍጠር ነው። ይህ ደግሞ እንደ ሳኒታይዘርና መሰል አልኮሎችን ማግኘት የማይችለው የኅብረተሰብ ክፍል በቀላሉ እጁን በመታጠብ ብቻ ወረርሽኙን መከላከል እንዲችል ማገዝንም፤ ማስተማርንም ማዕከል ያደረገ ነው። በቦታው ድንኳን ተክለው የማስታጠብ ሥራ ከጀመሩ ከ21 ቀን በላይ እንደሆናቸው የሚናገረው ወጣት ባህራን፤ በዚህ ሂደት በራሳቸው አቅም የጀመሩ ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦችም ሆኑ ወረዳው ሥራቸውን እየተመለከቱ አንዳንድ ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን ይናገራል።
ይህ ደግሞ እጅ ከማስታጠብና የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ከማከናወን ባለፈ አቅም ለሌላቸው ወገኖች የቁሳቁስ እርዳታ ስለማድረግ እንዲያስቡ ያደረጋቸው በመሆኑ ከወረዳው ጋር በቅንጅት ለመስራት ስለመጀመራቸው ይገልጻል። እንደ ወጣት ባህራን ገለጻ፤ የቁሳቁስ ድጋፍን ሲያስቡ አንደኛ በተለያየ ምክንያት ከውጭ ለሚመጡ ማቆያ ተብሎ የተለየ ስፍራ አለ። በመሆኑም በዚያ ማቆያ ውስጥ ሰዎች ሲገቡ ድጋፍ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው።
ሁለተኛ ደግሞ አካባቢው በርካታ አቅም የሌላቸው ወገኖች ያሉበት እንደመሆኑ እነዚህን ሰዎች መርዳትን መሠረት ያደረገ ነው። ምክንያቱም ቀድሞ መከላከል ሲቻል በተለያየ መልኩ በሚፈጠር ክፍተት ችግሩ ብሶ ከቤት እንዳትወጡ ቢባል ከዛሬ ተርፏቸው ለነገ ማስቀመጥ የማይችሉና ለዕለት በልተው የማያድሩ ወገኖች በመኖራቸው እነሱን ታሳቢ ያደረገ ሥራ እያከናወኑ መሆኑንና ችግሩ ሲፈጠርም ለእነዚህ ሰዎች ማድረስ በሚችሉበት አግባብ እየሰሩ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ ሰዉ ለመስጠት ፈቃደኛ ነው።
እኛም ከወረዳው ጋር ተነጋግረን እንደ ፓስታ፣ ማካሮኒና ዘይት የመሳሰሉትን መሰብሰብ ጀምረናል። 2013 ዓ.ም የሚከበርን የጥምቀት በዓል በድምቀት ማክበርን ታሳቢ አድርጎ ለመልካም ነገር የተጀመረው ይህ ተግባር፤ የችግሩን መከሰት ተከትሎ ቀድሞ መከላከል ላይ አተኩረው እየሰሩ ያሉበት ነው። ይሁን እንጂ ሥራቸውን ወደውና አመስግነው ብሎም አበረታተው የሚደግፉ የመኖራቸውን ያክል፤ ታጠቡ ሲባሉ ለእነርሱ ሳይሆን ለወጣቶቹ ሲሉ የሚታጠቡ አድርገው የሚቆጥሩበት አግባብ አለ።
ይህ ደግሞ ግንዛቤ ከማጣት ሳይሆን ያወቁትን ካለመተግበርና ከመዳፈር የመነጨ እንደሆነ ወጣቶቹ ይናገራሉ። ለዚህ አብይ ማሳያዎቹ ደግሞ ወጣቶቹ የበጎ ተግባር አገልግሎት በሚሰጡበት አካባቢ ያሉ የገበያ፣ የመጠጥ ቤቶች፣ የወጣት ማዕከል እና መሰል ነገሮች ላይ የሚታየው የሰዎች እንቅስቃሴ ሲሆን፤ ተግባሩ ግን የተሳሳተና ሊታረም የሚገባው ነው። ይህ የሚሆነው ደግሞ ሕዝቡም የመንግሥት አካሉም ተናብቦ ሲሰሩ፤ የየራሳቸውንም ኃላፊነት መወጣት ሲችሉ ነው። ለዚህ ደግሞ ከመንግሥትም ሆነ ከጤና ባለሙያዎች በሚሰጠው ምክር መሠረት ባለው ሁኔታ ሰዉ ከቤት ባይወጣ መልካም ነው።
መውጣት ግድ ካለው ግን በተቻለ መጠን ርቀቱን ጠብቆ መንቀሳቀስ፤ በየቤታቸው በተዘጋጁ የእጅ መታጠቢያ ስፍራዎችም ቶሎ ቶሎ እጁን መታጠብ ይኖርበታል። የመንግሥት አካላትም ከሕዝብ ደህንነት አይበል ጥምና በመጠጥ ቤቶች፣ በወጣት ማዕከላትና ሌሎ ችም ሕዝብ በዝቶ በሚ ገኝባቸው ስፍራዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ሥራ ከራስ የሚጀምር፣ ወደ ቤተሰብና ማህበረሰብ ሊያድግ፤ ለአገርም ሊተርፍ ይገባዋል።
በኢትዮ ጵያዊነት የመረዳዳት ስሜት አቅም የሌላቸውን መደገፍ፤ በኢትዮጵያዊ የመከባበርና መተሳሰብ ባህል ስለሌላኛችን ስንል ዛሬን ተራርቀን ስለ ነገ አንድነታችን ማሰብ ይጠ በቅብናል። ይህ ሲሆን ዛሬን ተሻግረን ብሩህ ነገን ማየት እንችላለን። ሻምበል አየነው እንዳየን፣ የፈረንሳይ አካባቢ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ወጣቶቹን በቅርበት እየተከታተሉ ከሚያግዙ የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አንዱ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የእነዚህን ወጣቶች ሥራ በቃላት ለመግለጽ ይከብዳል። ወጣቶቹ ወረርሽኙ ተከሰተ በተባለበት ወቅት ምንም በዚህ መልኩ ሥራውን ሳይጀምር ነው እጅ ማስታጠብ የጀመሩት። እስካሁንም ሳይሰለቹ እጅ በማስታጠብ፤ ስለ በሽታው በማስተማር ዘልቀዋል። ወጣቶቹ ወደዚህ ተግባር ሲገቡ የማንንም እርዳታ ሳይጠብቁ በራሳቸው አቅም ፕላስቲክ በርሜልም ሆነ የንጽህና መጠበቂያ ሳሙናና ውሃን ጨምሮ አሟልተው መሆኑን የሚናገሩት ሻምበል አየነው፤ በሞንታርቦ ታግዘው ሕዝቡን የመቀስቀስና እጁን በመታጠብ ራሱንም ሌሎችንም መጠበቅ እንደሚገባው በፈጣሪ ስም ሲማጸኑና ሲያስታጥቡ እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይህ ተግባራቸው የሚያስመሰግንና የሚያስደንቃቸው ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች አርዓያነት ያለው መሆኑን በመጠቆምም፤ ሌሎችም የእነርሱን ተግባር ሊከተሉ እንደሚገባ ይመክራሉ። እነዚህ ወጣቶች በዚህ መልኩ እጅ በማስታጠብ፣ የተለያዩ ድጋፎችን በማሰባሰብና ሕዝቡን በማስተማር ላይ ቢሆኑም፤ አሁንም በሌሎች ወጣቶች፣ በኅብረተሰቡም ሆነ በሌሎች አካላት ሊታረሙና ሊታሰቡ የሚገባቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን ይገልጻሉ።
የአንዳንድ ወጣቶችን ተግባር በምሳሌነት የሚጠቅሱት ሻምበል አየነው፤ ተቃቅፈው ሲሄዱና ሲላፉም ጭምር ተዉ ሲሏቸው «ምንድነው ፋዘር» በሚል ስላቃዊ ቃል አፊዘውባቸው እንደሚያልፉ ይገልጸሉ። ከዚህ ባለፈ መጠጥ ቤቶች፣ የወጣት ማዕከላት፣ የቀበሌ ሱቆችና መሰል ቦታዎች ላይ ያለው የሰዎች እንቅስቃሴ ለበሽታው መስፋፋት እገዛ የሚያደርጉ በመሆናቸው ሊታረሙ እንደሚገባውም አስገንዝበዋል። እንደ ሻምበል አየነው ገለጻ፤ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ ከሚያከናውኑት ተግባር ባለፈ ያለው የሕዝብ እንቅስቃሴና ተግባር በሽታው ስለመኖሩ ግንዛቤ ያላቸው ስለመሆኑ እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸው ነው።
ይህ ደግሞ የኢትዮጵያዊነት ስብዕናና አልነካም ባይነት ወኔ ጋር ፈጽሞ የማይሄድ፤ የጥንቃቄና ንቃት እሴቱን የማይገልጽ፤ ይልቁንም የመዘናጋት፣ የእንዝላልነትና ተስፋ የመቁረጥ መገለጫዎች ናቸው። ይሁን እንጂ የእሳትን ማቃጠል ለማወቅ የግድ መቃጠል እንደማያስፈልግ ሁሉ፤ ይህ ወረርሽኝም የሚደርሰውን ጉዳት ለማወቅ አሁን ላይ እንደ አገር ካለው ባለፈ ከሌሎች ያውም ኃያላን ከሚባሉት አገራት ትምህርት መውሰድ ይገባል።
መንግሥት፣ እስካሁን እየተወሰደ ያለው ተግባር የሚበረታታ፤ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንቅስቃሴ ስለ ሕዝብ መኖርን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ይህ ተግባር ሊጠናከር፤ በመጠጥ ቤቶችና ሌሎችም ስፍራ ያለው የሕዝብ እንቅስቃሴ ሂደት የሚገታበት አካሄድም ሊፈጠር ይገባል።
ምክንያቱም ዛሬን በትዕግስት ካልሆነ በሩጫ ማሸነፍ ስለማይቻል፤ ዛሬን አንዳችን ኖረን ሌሎችን ለማኖር ሲባል ተራርቆ ነገር በሳቅና በደስታ አብሮ የሚኖርበትን ዕድል መፍጠር ተገቢ ነው። በዚህ ሂደት የፈጣሪን አዳኝነት በማመን፤ የራስን ጥንቃቄ ማድረግ የግድ መሆኑን መገንዘብ ይገባል። ምክንያቱም ፈጣሪም እርዱኝ እረዳችኋለሁ ብሎ አዟልና ነው።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 2/2012
ወንድወሰን ሽመልስ
በክፉ ጊዜ የደረሱ ቀና ልቦች