ኮሮና ቫይረስ በዓለም ማህበረሰብ ጤናና አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ
ቀውስ እየፈጠረ ነው::ቻይናን ሙሉ ለሙሉ ላለፉት ሁለት ወራት እንቅስቃሴዋን
ዘግታ ማገገም ስትጀምር ፣ ሌሎቹን የእስያ አገሮች በማካለል አውሮፓንና አሜሪካ
ገፈቱን መቅመስ ጀምረዋል::በአፍሪካ 50 በሚጠጉ ሀገራት ተከስቷል::በጣሊያን
ያለው የቫይረሱ ጉዳት ደግሞ በእጅጉ የከፋ ነው::
ጣሊያናውያን ከመነሻው ጀምሮ ለቫይረሱ የሰጡት ግምት አናሳ መሆንና
መዘናጋት በእጅጉ ዋጋ አስከፍሏቸዋል::ጣሊያናውያን መዘናጋትና ችላ ባይነት
የሚያደርሰውን ጥፋት ከእኛ ተማሩ በማለት የቁጭት መልዕክት እያስተላለፉ
ነው::እነሱ አሁን እኛ ዘንድ እንዳለው ሁኔታ ውስጥ ሆነው የጥንቃቄ መልዕክቶች
ከማስጠንቀቂያ ጋር ሲነገራቸው፣ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በመቁጠር
በሬስቶራንቶች፣ በመጠጥ ቤቶች፣ በጭፈራ ቤቶችና በመሳሰሉት ሥፍራዎች በገፍ
እየተገኙ ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት መሆናቸውን ዛሬ በሰቆቃ እየተናገሩ ነው፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓርብ መጋቢት 4 ቀን
2012 ዓ.ም በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ
ጃፓናዊ አማካይነት ኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለቫይረሱ የተሻለ ትኩረት
ተሰጥቶታል::በተለይም መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየወሰዳቸው ያሉ
እርምጃዎች ከብዙዎች ምስጋና ተችሮታል፡፡
በቅርቡም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መንግስት ተጨማሪ
መመሪያዎችን አሳልፏል። ከመጋቢት 14 ጀምሮ የደኅንነት ዘርፉ በቁጥር ብዙ ሰው
የሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎች እንደሚያስቆምና ማኅበራዊ ርቀቶች መጠበቃቸውን
እንደሚያረጋግጥ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም መከላከያ ሠራዊት በድንበር አካባቢ የሚደረጉ
እንቅስቃሴዎችን በሙሉ እንደሚገታ አስታውቋል::የፖለቲካ ፓርቲዎችን
ጨምሮ የመንግሥት ተቋማት ማኅበራዊ ርቀት መጠበቅን ተፈጻሚ ማድረግና
ስብሰባን ሲያካሂዱ ቫይረሱን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተፈጻሚ ማድረግ
እንደሚኖርባቸውም ማሳሰቢያ ሰጥቷል::ሠራተኞችም እንደየ ሁኔታው ከቤት
ሆነው እንዲሰሩ የሚቻልበት አሰራርም ፈጥሯል::የቫይረሱን ስርጭትም ለመግታት
እንዲያግዝ መንግስት 5 ቢሊዮን ብር መመደቡንም አስታውቀዋል።
በመንግስት የተወሰዱት እርምጃዎች መልካም ቢሆኑን አፈጻጸም ላይ ግን
ክፍተቶች ይስተዋላሉ::አሁንም በየታክሲ መጠበቂያው፣ በከነማ ፋርማሲዎች፣
በአልኮል መሸጫ ሱቆችና በታከሲዎች ሰዎች ከሚገባው በላይ ታፍገውና
ተጨናንቀው ይታያሉ::በገዢው ፓርቲ ሳይቀር በርካታ ህዝብ የተሳተፈባቸው
ስብሰባዎች ሲደረጉ ተመልክተናል::አሁን የተሻለ አዝማሚያ ቢያሳዩም በእምነት
ተቋማትና በአምልኮ ስፍራዎች በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ በተጨናነቀ ሁኔታ
አምልኮ ሥርዓቱን ሲያካሂድ ይታያል፡፡
በተለይ ምሽትን ተገን አድርገው ታክሲዎች ከወትሮው ባልተለየ መልኩ ተሳፋሪን አጨናንቀው
ሲጭኑ መመልከት አሁንም የቫይረሱን አደገኛነት ምን ያህል እንዳልተገነዘብነው ማሳያ
ነው::ማህበራዊ ርቀትን ሳይጠብቁ መንቀሳቀስና በወረፋ ትራንስፖርት መጠበቅ ዛሬም የምናያቸው
አሳሳቢ ችግሮቻችን ናቸው፡፡
እንደመርካቶ ባሉ ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴ በሚከናወንባቸው ስፍራዎች አሁንም ሰዎች እጅብ
ብለው ሲሸምቱ ይታያሉ::በጎዳናዎችም ላይ የሚስተዋለው የጎዳና ተዳዳሪዎች ውሎና አዳር አሁንም
መተፋፈግና መጠጋጋት የተለየው አይደለም::በእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ስለበሽታው
ያለው ግንዛቤ በራሱ አጠያያቂ ነው፡፡
በአጠቃላይ በሀገራችን የቫይረሱ መከሰት ከተነገረ ጀምሮ እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች
መልካም የሚባሉ ቢሆንም ከላይ የጠቀስናቸውንና መሰል ችግሮች በአፋጣኝ መቅረፍ ካልተቻለ እንደ
ሀገር የሚያስከፍለን ዋጋ የበዛ ስለሚሆን ከወዲሁ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይገባል::በየትኛውም
ሁኔታ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 19 / 2012
ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል