የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል።
በሽታው በጠናባቸው ታማሚዎች ላይ ደግሞ እንደ ሳንባ ምች (ኒሞኒያ)፣ ከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም የሚያሳይ ሲሆን የኩላሊት ሥራ ማቆምና ሞትን ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡
መተላለፊያ መንገዶች
• በሽታው በሳልና በማስነጠስ ወቅትና ከታማሚ ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ፣ ባልታጠበ እጅና በመሳሰሉት ይተላለፋል፡፡
• የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣
• እጅን በሳሙናና ውኃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ካደረጉ፣
• ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣
• ምክንያቱ ባልታወቀ በሽታ በታመሙም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ
በበሽታው መያዛቸውን የተጠረጠሩ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች
• ወደ ሀገር በተመለሱ በ14 ቀናት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ሕመም፣ ትኩሳትና እንደ ሳል ያሉ የሕመም ምልክቶች ካሳዩ፣ በተጨማሪ የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አሥራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገሮች ሄደው ከነበረ፣ በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ አገሮች ሄዶ የበሽታውን ምልክቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ እንዲሁም የበሽታውን ምልክት ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ በአስቸኳይ በ8335 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ሪፖርት ያድርጉ፡፡
• በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ ወይም በሶፍት መሸፈን፣
• አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድና እጅን ሁልጊዜ በውኃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ከአንድ ወር በፊት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በቻይና የተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ሥጋት መሆኑን አውጇል።እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሰውም ቫይረሱ ከቻይና በተጨማሪ ወደ ሌሎች አገሮች በመዛመቱ ነው። የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳስታወቁት፣ ቫይረሱ በሌሎች አገሮች መሠራጨቱ ለጤና ሥጋት ሆኖ እንዲታወጅ ምክንያት ሆኗል።
የጤና ሚኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ጃፓናዊ አማካይነት ኮረና ቫይረስ መገኘቱን አስታውቀዋል።የኮረና ቫይረስ ሥርጭትን መግታት የሚቻለው በመደናገጥ ሳይሆን፣ በሰከነ መንገድ ኃላፊነትን በመወጣት ነው።የኮሮና ቫይረስ ዓለም ላይ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የቫይረሱን ስርጭት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ በቫይረሱ የተያዘው የመጀመሪያው ሰው ከታወቀበት ዕለት ጀምሮ የመጀመሪያዎቹ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ለመያዝ 67 ቀናት መውሰዱን ገልጸዋል።
ቀጣዮቹ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ለመያዝ 11 ቀናትን ወስዷል ያሉት ዳይሬክተሩ፥ ሦስተኛ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ መያዛቸውን በመጥቀስ የቫይረሱን የስርጭት ፍጥነት አሳሳቢነት አመላክተዋል።
ዶክተር ቴድሮስ በመግለጫቸው ቫይረሱን ለመከላከል የቡድን 20 አባል ሀገራት መሪዎች በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቀርባለሁም ባሉት መሠረትም ጉዳዩ የቡድን 20 ሀገራትን ስቧል።ኢትዮጵያም የአፍሪካ ሀገራትን በመወከል የድርሻዋን በመወጣት ላይ ትገኛለች።በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገው ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠሉ በመንግሥትና በሚመለከታቸው አካላት በተደጋጋሚ እየተገለጸ ቢሆንም፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለወረርሽኑ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ጥንቃቄውን የበለጠ ማጠናከር አለበት።ሁሉም የአገሪቱ መግቢያ ጣቢያዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር መዘናጋት እንዳይታይበት፣ አጠራጣሪ ሰዎች ሲያጋጥሙ በፍጥነት ሪፖርት ማድረግና የግንዛቤ ማስጨበጫውን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ሳያሰልሱ ማሠራጨት የመንግሥት ኃላፊነት ነው።በሥራ አካባቢዎች፣ በመኖሪያ ሥፍራዎች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በቤተ እምነቶች፣ በስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ በትራንስፖርት አገልግሎቶች፣ በመዝናኛዎችና በመሳሰሉት የእጅና የአካላዊ ንክኪዎችን በከፍተኛ ደረጃ ማስወገድ ተገቢ ነው።በጤና ሚኒስቴርም ሆነ በኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካይነት የሚሰጡ መግለጫዎችን በትኩረት መከታተል የግድ ይሆናል።ማኅበረሰባችን የአኗኗር ዘይቤው በጣም የተቀራረበ በመሆኑ፣ ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዱ የጤና ምክሮችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው።ጥንቃቄው ውጤታማ ከሆነ ችግሩን በበቂ አቅም መቋቋም ይቻላል፡፡
የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደጋጋሚ እንደሚያሳስበው፣ ኅብረተሰቡ ከዚህ በፊት ማናቸውንም በሽታዎች ለመከላከል ሲጠቀምባቸው የነበሩ የበሽታ መከላከያ ዘዴዎችን ችላ ማለት የለበትም።ይልቁንም የመከላከያ ዘዴዎችን አጠናክሮ በመቀጠል የእጅ ንፅህናን ለመጠበቅ በውኃና በሳሙና አዘውትሮ መታጠብ፣ ለእጅ ንፅህና መጠበቂያ የሚውሉ አልኮል ነክ ምርቶችን አዘውትሮ መጠቀም፣ ባልታጠበ እጅ ዓይን፣ አፍንጫና አፍን አለመነካካት፣ ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው አገሮች ከመጡ መንገደኞችና ሳል ወይም ትኩሳት ካላቸው ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግና ቢያንስ እስከ ሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ፣ ሰዎች የሚበዙበት ሥፍራ በተለይ የሕመም ስሜት ካለ አለመሄድ፣ በማሳልና በማስነጠስ ጊዜ አፍና አፍንጫን መሸፈን፣ እንዲሁም ስለበሽታው በቂ መረጃ በማግኘት ተግባራዊ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው።ከእነዚህ ምክሮች በተጨማሪ በኅብረተሰባችን ውስጥ የተለመዱ የሰላምታ አሰጣጦች፣ ማለትም መጨባበጥና መተቃቀፍ ማስወገድ ጠቃሚ ነው።የቫይረሱ ሥርጭት በዓለም ዙሪያ እጅግ በጣም አሳሳቢ በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ይሉኝታ አስፈላጊ ባለመሆኑ አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ለሚመለከተው አካል በፍጥነት ሪፖርት ማድረግ መዘንጋት የለበትም።እዚህ ላይ ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ተጠርጣሪዎችን በቶሎ ወደ ሕክምና ተቋም በመውሰድ ሕይወታቸውን መታደግ እንጂ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ ማግለል ተገቢ አይደለም።ማግለል ሰብዓዊነት የጎደለው አስከፊ ድርጊት መሆኑን መረዳት ይገባል።ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በእጅጉ ይፈለጋል።ማግለል አደጋውን ያባብሳል እንጂ ምንም አይፈይድም፡፡
ኮረና ቫይረስ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ ነው።ቻይናን ሙሉ ለሙሉ ላለፉት ሁለት ወራት ሲዘጋ፣ ሌሎቹን የእስያ አገሮች በማካለል አውሮፓንና አሜሪካን በስፋት አዳርሷል።በአፍሪካ በ26 አገሮች ውስጥ መግባቱ ተረጋግጧል።የወረርሽኙ ሥርጭት ተስፋፍቶ የዓለም ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመገታቱ፣ በከፍተኛ መጠን የነዳጅ ዋጋ አሽቆልቁሏል።የኢትዮጵያ ኢኮኖሚም ተፅዕኖ ስለሚኖርበት ይህም የቅድመ ዝግጅቱ አካል መሆን አለበት።ለጊዜውም ቢሆን ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚፈስባቸውን ፕሮጀክቶች ያዝ በማድረግ፣ እየበረታ የመጣውን ተፅዕኖ ለመቋቋም መጠባበቂያ በጀት ማዘጋጀት የግድ ይሆናል።ምንም እንኳን ወረርሽኑ ለብዙ ጊዜያት እንደማይቆይ ትንበያዎች ቢኖሩም፣ በተቻለ መጠን ጉልህ ጉዳት እንዳያደርስ ሊታሰብበት ይገባል።ሰዎች ራሳቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ እየጠበቁ የማምረት፣ የማከፋፈልና የችርቻሮ ሥራዎች እንዲቀላጠፉ ልዩ ዕገዛ ማድረግም ተገቢ ነው።የአገሪቱ የጤና ተቋማት በሙሉ ትኩረታቸውን ለቅድመ ጥንቃቄው በማድረግ፣ አምራቹም ሆነ ነጋዴው በሥራቸው ላይ እንዲገኙ ራሳቸውን ብቁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።በተለይ መንግሥት በቁጥጥሩ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙኃን ሳያሰልሱ ቅድመ ጥንቃቄው ላይ እንዲሠሩ፣ ባለሙያዎችን እየጋበዙ ምክር እንዲለግሱ እንዲያስችሉ ማመቻቸት አለበት።ማኅበረሰቡም ተባራሪ ወሬዎችን ሰምቶ ከማመን ወይም ራስን ከማደናገጥ፣ የባለሙያዎችን መረጃና ምክር በጥንቃቄ ማዳመጥና ተግባራዊ ማድረግ ይሻለዋል።መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በማግኘት፣ ራስን ከተሳሳቱ መረጃዎች በመከላከል መደናገርና ፍርኃትን ማስወገድ ያስፈልጋል።ቅድመ ጥንቃቄው በዚህ መንገድ ተጠናክሮ ሲቀጥል ኢኮኖሚውን መታደግ ይቻላል።የሕዝቡን ተስፋ ማለምለም እንዲሁ፡፡
እንደሚታወቀው ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ከሥፍራ ወደ ሥፍራ ይንቀሳቀሳሉ።በዚህም ምክንያት በጤና ላይ ለየት ያለ ነገር ሲያጋጥም በቶሎ ወደ ሕክምና ተቋማት መሄድ ያስፈልጋል።ይህ የሚጠቅመው በመጀመሪያ ደረጃ የገዛ ሕይወትን ለማትረፍ ሲሆን፣ ቫይረሱ ቢከሰት እንኳ ሥርጭቱን ለመግታት ይረዳል።የኮረና ቫይረስ ምልክት ሊሆን ይችላል የሚባል ለየት ያለ የጤና መታወክ ሲያጋጥም፣ ለ14 ቀናት ያህል ወደ ተዘጋጀ ለይቶ የመከታተል ማዕከል መግባት የግድ ነው።በዓላማችን ታዋቂ ሰዎች ሳይቀሩ የክትትል ማዕከል ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።ዝነኛው የፊልም ተዋናይ ቶም ሐንክስ ከባለቤቱ ሩት ዊልሰን ጋር፣ አውስትራሊያ ውስጥ የክትትል ማዕከል መግባቱን በኢንስታግራም ገጹ አስታውቋል።የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከእነ ባለቤታቸው፣ እንዲሁም የአርሰናል እግር ኳስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ማይክል አርቴታና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች በክትትል ሥር መሆናቸው ታውቋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 19 / 2012
ዓለምን ያመሰው የኮሮና ቫይረስ