‹‹የእከሊትን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም›› ይላል የአበው ፈሊጣዊ አነጋገር። እውነት ነው፤ ለዚህ አባባል መነሻ የሆነው ጉዳይ ለአባባሉ ተገቢ ነው። ሰሞኑን በዓለም የተከሰተውና ሁላችንንም በጭንቀት መከራ እያሳየን ያለው የወቅቱ ጉዳያችን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እና የሰዎች ሞት ሌሎች ጉዳዮቻችንን እንድንዘነጋና ትኩረታችንን ሁሉ በእርሱ ላይ እንዲሆን አድርጓል።
ቫይረሱ ከተከሰተባት ቻይና በይበልጥ በጣሊያን ላይ መዓቱ ወርዶባታል። የጣሊያን መንግሥት በሕዝቡ የደረሰው እልቂት አሳስቦትና የሚያደርገው ጠፍቶት ችግሩ አሳዛኝና ከአቅሙ በላይ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።
በጣሊያን በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስከወዲያኛው አሸልበዋል። ይህ በዓለም ሞት ካስመዘገቡ ሀገራት ከፍተኛውን ቁጥር እንድትይዝ አድርጓታል። በአገሪቱ የመቀበሪያ ሥፍራ እስከመሙላት ደርሷል። የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲቻልም ሕዝቡ ከቤቱ እንዳይወጣ ሲደረግ ከቤት ወጥቶ የተገኘ ሰው 140 ዩሮ ቅጣት እንደሚደርስበትም ተደንግጓል። በዚያች አገር በጥቂት ጊዜያት ከተመዘገበው 6 ሺህ 77 ሰዎች ሞት ውስጥ ከሦስት ሺህ በላይ የሚሆነው በሎምባርዲ ግዛት የተመዘገበ ነው።
ሌሎች አገሮች የሕዝባቸውን ደህንነት አደጋ ላይ ላለመጣል የመጓጓዣ መገልገያዎችን፣ የሕዝብ መሰብሰቢያዎችንና መዝናኛ ቤቶችን ሁሉ እስከማገድና በጸጥታ ኃይሎቻቸው እስከመቆጣጠር ደርሰዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም አካል በመሆኗ በአሁኑ ወቅት የከፋ ችግር ባይደርስባትም የዚሁ ችግር ተጋሪ ሆናለች። እስከትናንት እኩለ ቀን ባለው መረጃ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል።
ችግሩ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ መንግሥት የተለያዩ የጥንቃቄ መግለጫዎችንና ኅብረተሰቡ ሊከተላቸው የሚገቡ ጉዳዮችን መልዕክት ሲያደርስ ቢቆይም መላው ኅብረተሰብ ለመከላከሉና ለሚወሰደው ጥንቃቄ በቂ ትኩረት አልሰጠም። ይህ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍለን በመሆኑ አሁንም አልረፈደምና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
በሕዝብ መጓጓዣ ዘዴዎች ላይ የሚታየው መጨናነቅ፣ ማህበራዊ ጥግግትን ለማስቀረት ትኩረት ያለመሰጠቱ፣ በየምሽት መዝናኛ ቤቶች የሚታየው ፈንጠዝያ፣ አገሪቱ የቫይረስ ስርጭት የማይነካት የሚያስመስል ስሜት ውስጥ የከተተን ሆኗል። ስለዚህ ችግሩ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ አደጋ ከማስከተሉ በፊት ሕዝቡ ተገቢውን ጥንቃቄ መውሰድ አለበት።
የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን ሕይወት ለመታደግ የሕክምና ተቋማትን የማዘጋጀት፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን የማሰራጨት፣ የጥንቃቄ እርምጃ አወሳሰዶችንና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን የተመለከተ መመሪያዎችን አስተላልፏል።
ቀሪው ጉዳይ መላው ኅብረተሰብ መውሰድ የሚገባው የጥንቃቄ እርምጃ የራሱ ተግባርና ኃላፊነት ነው። በሳይንስ በልጽገው ሁሉን ችግር መቆጣጠር እንችላለን የሚሉት አገራት ምንም ማድረግ ተስኗቸው የሕዝባቸውን እልቂት በዓይናቸው እያዩ መሆኑን እየታወቀ፤ እያደመጥንና እያየን መዘናጋት ትክክል አይደለም። በራሳችን ላይ ችግርን መጋበዝ ነው። ጥንቃቄ እያደረጉ ያሉትን ወገኖች ጭምር ችግር ውስጥ የሚከት ነው። ስለሆነም ችግሩ ከደረሰባቸው አገራት ትምህርት በመውሰድ የመፍትሄው አካል ልንሆን ይገባል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 16 /2012
ችግሩን ተገንዝበን የመፍትሄው አካል እንሁን!