ነ
ትውልድ እና እድገታቸው በቀድሞ አጠራር አርሲ ክፍለ አገር አርባ ጉጉ አውራጃ መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ ነው። በያኔው አጠራር አለማያ እርሻ ኮሌጅ በ1974 ዓ.ም በእጽዋት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል። ከእንግሊዝ አገር ኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ በምርጥ ዘር ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ፣ በዘር ቴክኖሎጂ ደግሞ ሶስተኛ ዲግሪ ሰርተዋል።
በኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የባሌ ምርጥ ዘር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ በሞዛምቢክ ወርልድ ቪዠን መስሪያ ቤት የግብርና ልማት ሃላፊ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ በአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጄኔቫ የአፍሪካ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ልምድ አካብተዋል።
በዩኤንዲፒ ስር የአርሲ ባሌ ገጠር ልማት ፕሮጀክት በምርጥ ዘር ባለሙያነት፣ በዩኤንዲፒ (የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም) የግብርና ኤክስቴንሽን የምርምር ድጋፍ ሰጪ፣ እንግሊዝ አገር የእጽዋት ምርምር ድርጅት ውስጥ በተመራማሪነት ሰርተዋል።
ዘንድሮ ወደ አገራቸው ተመልሰው የሲቪል ሶሳይቲ ፎረም የቦርድ ሊቀመንበርና የጥምረቱ የቦርድ አባል ሆነዋል። ሲሲአር ዲኤ (የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ድርጅቶች ህብረት) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ንጉሱ ለገሰ የቅዳሜ እንግዳችን ናቸው።
አዲስ ዘመን፡- መንግስት ዘንድሮ ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ፣ ምህዳሩንም ለማስፋት ጥረት እያደረገ ይገኛል። በእናንተ በኩል ሂደቱ ተዓማኒ፣ ፍትሃዊና ተቀባይነትን እንዲያተርፍ ሚናችሁ እንዴት ይገለጻል?
ዶክተር ንጉሱ፡- መንግስት ለራሱ ሲል ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ ያደርጋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ባያደርግ ራሱን ይጎዳል።ችግርም ይገጥመዋል። ምክንያቱም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባለመደረጉ እና ችግር በመፈጠሩ ነው ይህ ለውጥ የመጣው። ይህ መንግስት ከእዛ ብዙ ተምሯል ብለን እናስባለን። ከእዛ አኳያ ያንን ለመንግስት እንተወውና በእኛ በኩል በየትኛውም አገር በእዚህ ጉዳይ ኃላፊነት ያለው ምርጫ ቦርድ ነው። ምርጫን በተመለከተ የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንኳን ጣልቃ ለመግባት ኃላፊነት የላቸውም። በምርጫ ቦርዱ የምርጫ ሰንጠረዥ መሰረት መራጮችን ማስተማር፣ ማሳወቅና ስለመብታቸው የማስገንዘብ እንዲሁም ለምን እንደሚመርጡ ስራችን ይሆናል።
ሌላው የመታዘብ ስራ እንሰራለን።ምዝገባ ሲጀምር ትክክለኛ ሰዎች ምዝገባ ስለማድረጋቸው እንመለከታለን። ብዙ አገሮች ላይ የታዘብናቸው አሉ። እኔ አፍሪካ ውስጥ ብዙ ምርጫዎች ላይ ተሳትፌያለሁ። ዚምባብዌ፣ ኮንጎ፣ ብሩንዲ፣ የሱዳን ሪፈረንደምንም ሲካሄድ ታዝቤያለሁ። ብዙ የገጠሙን ነገሮችም ነበሩ። አንዳንዶቹ አገራችን ውስጥ ይከሰታሉ ብዬ የማላስባቸው ነገሮች ሆነው ተመልክቻለሁ። መታወቂያቸውን ይዘው ሰዎች ማንነ ታቸው እየተጣራ ሲመዘገቡ አይቻለሁ። ከሲዳማ ሪፈረንደምም ልምድ አለን።
ምዝገባው መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀመር ይጠበቃል። ከእዚህ ቀን ጀምሮ በያለንበት ጣቢያ ላይ በሚኖሩ ወደ 83 የምርጫ ዞኖች በምንችለውና ባለን የሃብት መጠን ለመሸፈን ጥረት እያደረግን እንገኛለን። ግን ከደንቦችና ከአሰራሮች እንዳንወጣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ይመራናል። ይህም ከምርጫ ቦርድ ጋር ተጣጥሞ የወጣው ህግ ጋር ተያይዞ እኔን እንደ ሲሲ አር ዲኤ ወይም እንደፎረሙ ሊቀመንበር ካየኸኝ በውስጡ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም አሉ።
አዋጁ በአሁኑ ሰዓት የውጭ ድርጅቶች የምርጫ መታዘብንም ሆነ የማስተማር ነገሮችን አልፈቀደም። ስለዚህ ጥንቃቄ አድርገን አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች ብቻ ምርጫውን የማስተባበርና የማስፈጸም ተግባር እንዲፈጽሙ ተደርጓል። ይህ በአዋጁ የተቀመጠ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወንና መንግስትም ትኩረት የሰጠው ጉዳይ በመሆኑ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም «ከፖለቲካ ሳንወግን ከየትኛውም ወገን ሳንሆን ምርጫውን ለመታዘብ ተዘጋጅተናል» ትውልድ እና እድገታቸው በቀድሞ አጠራር አርሲ ክፍለ አገር አርባ ጉጉ አውራጃ መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ ነው። በያኔው አጠራር አለማያ እርሻ ኮሌጅ በ1974 ዓ.ም በእጽዋት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል። ከእንግሊዝ አገር ኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ በምርጥ ዘር ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ፣ በዘር ቴክኖሎጂ ደግሞ ሶስተኛ ዲግሪ ሰርተዋል።
በኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት የባሌ ምርጥ ዘር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ በሞዛምቢክ ወርልድ ቪዠን መስሪያ ቤት የግብርና ልማት ሃላፊ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ በአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ጄኔቫ የአፍሪካ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ልምድ አካብተዋል።
በዩኤንዲፒ ስር የአርሲ ባሌ ገጠር ልማት ፕሮጀክት በምርጥ ዘር ባለሙያነት፣ በዩኤንዲፒ (የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም) የግብርና ኤክስቴንሽን የምርምር ድጋፍ ሰጪ፣ እንግሊዝ አገር የእጽዋት ምርምር ድርጅት ውስጥ በተመራማሪነት ሰርተዋል።
ዘንድሮ ወደ አገራቸው ተመልሰው የሲቪል ሶሳይቲ ፎረም የቦርድ ሊቀመንበርና የጥምረቱ የቦርድ አባል ሆነዋል። ሲሲአር ዲኤ (የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ድርጅቶች ህብረት) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ንጉሱ ለገሰ የቅዳሜ እንግዳችን ናቸው።
አዲስ ዘመን፡- የበጎ አድራጎት አዋጅ መሻሻል በስራችሁ ላይ ያመጣውን ለውጥና በመሻሻሉ ሂደት የነበራችሁን ሚና ቢገልጹልኝ ?
ዶክተር ንጉሱ፡- በእውነት ብዙ መሻሻሎችና ለውጦች አሉ። መሻሻሉ ካመጣው ነገር ቀድሞ የሚጠቀሰው የተገኘው ነጻነት ነው። ነጻ ሆነህ በሰላም እንደፈለግክ መንቀሳቀስ ቀደም ካለው ጋር ሳነጻጽረው መሻሻል አለው።የስራ ገደብ አልተጣለም።እስካሁን ስናየው ወደእዚህ ተመለስ፣ወደዚያ አትሂድ የሚል ወሰን የለም።ስለዚህ ህብረተሰባችን ጋር ደርሰን ያለበትን ችግር ሳይሸማቀቅና ሳይሳቀቅ የፈለገውን እንዲናገር እያገዝን ነው።በፊት ለመሰባሰብ ብዙ ፈቃድ መጠየቅ ያስፈልግ ነበር፤ አሁን የለም። የፈለግነውን ጠርተን ሁሉንም ማወያየት ችለናል። ይህ ራሱ የመሰባሰብ ነጻነት መፈጠሩን ያሳያል።
አሁን መናገር ያለብንን ነገሮች በመረጃ እያስደገፍን እንናገራለን።ችግሮች ካሉ እንዲስተካከሉ ማድረግ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች አሉ። የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የሰራቸውን ስራዎች እንድንገመግም ጠርቶን ተወያይተናል። አንድ የመንግስት ተቋም ሲቪል ሶሳይቲን ሰብስቦ ስራዎቹን ማስገምገሙ የዴሞክራሲ ስርዓቱ መስመሩን እየያዘ እንደሚገኝና ድርጅቱ ገደብ እንደሌለበት የሚያሳይ ነው። አንድ የመንግስት ድርጅት የበጀት እንቅስቃሴውን፣ የእቅዱን አፈጻጸም ማስተቸት መቻሉ የሚበረታታ ነው። በመንግስት ደረጃ ግልጽ እየሆነ የመምጣት አዝማሚያ ይታያል። ተጠያቂነት፣ የኃላፊነትና የግልጽነት ስርዓት እንዲሰፍን ጥረት የማድረግ ሁኔታዎች ሲተገበሩ አይተናል።
አዲስ ዘመን፡- የሲቪክ ሶሳይቲ ማህበራት ጥምረት የመመስረታችሁ ዓላማ ምንድን ነው? ቁጥራችሁስ ምን ያህል ደርሷል?
ዶክተር ንጉሱ፡- የሲቪክ ሶሳይቲ ማህበራት ጥምረት መስራቾች በአሁኑ ሰዓት 125 ደርሰናል። ባጠቃላይ የሲቪክ ማህበራቱ ጥምረት በማሰባሰብና በመሰባሰብ በጋራ ምርጫውን ለመታዘብ ነው ዋነኛ ዓላማችን። መራጮችም ሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሰዎች ስለምርጫ ትምህርት ለመስጠት፣ በየክልሉ የሚገኙ አባሎቻችንን በተገቢው መንገድ አቀናጅተን በክልሉ ወደ የወረዳውና ቀበሌዎች ተሰማርተው እንዲሰሩ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ቅንጅት ተፈጥሮ ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ራሱን ችሎ ስራ ጀምሯል። በተለይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ‹‹በሲዳማ ሪፈረንደም ላይ አግዙን›› በሚል ስለጠየቀን የቀረበውን ጥያቄ ተቀብለን በተገኘው ሃብት በእዛች አጭር ጊዜ ውስጥ 200 የሚደርሱ ታዛቢዎችን አሰማርተናል። ሂደቱ ለመንግስትም ሆነ ለምርጫ ቦርድ በሰዓቱ ዱብ ዕዳ ነበር። በደንብ ዝግጅት አልተደረገም ነበር። ውሳኔው የተደረገው፣ ሁሉም ነገር የተካሄደው በአጭር ጊዜ ውስጥ ነበር። በእዛን ጊዜ ቅንጅቱ ስላልተመዘገበ ስራው ይካሄድ የነበረው በኮሚቴ ነበር።
እንዲህ አይነት ትርፍ ስራ ለብሄራዊ ምርጫ ሊያዘጋጀን አይችልምና የግድ ተሰባስበን ድርጅቱን አስመዝግበን፣ ራሱን ችሎ ዳይሬክተርም ተመድቦለት፣ ሃብት ባይኖረውም ከእያንዳንዳችን ሰራተኞች መድበን መቋቋም አለበት በሚል አምነን ወስነናል። ተሳክቶልን ተቋቁሟል። ግን አሁንም የማጠናከር ስራዎች ይቀራሉ። ልምድ እንዳለው ተቋም የምናግዛቸው አንዳንድ ነገሮች አሉን። ድርጅቱ ገና በመሆኑ ወጪን በተመለከተ የፖሊሲ ዶክመንት ያስፈልጉታል። በተለይም የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች ሰነዶችን ስለሚፈልጉና ልምድ ስለሚጠየቅ ያንን ለማሟላት ምርጫው እስከሚያልፍ ሂደቱ በእዚህ የሚቀጥል ይሆናል።
አዲስ ዘመን፡- መንግስት ዘንድሮ ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ፣ ምህዳሩንም ለማስፋት ጥረት እያደረገ ይገኛል። በእናንተ በኩል ሂደቱ ተዓማኒ፣ ፍትሃዊና ተቀባይነትን እንዲያተርፍ ሚናችሁ እንዴት ይገለጻል?
ዶክተር ንጉሱ፡- መንግስት ለራሱ ሲል ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ ያደርጋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ባያደርግ ራሱን ይጎዳል።ችግርም ይገጥመዋል። ምክንያቱም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባለመደረጉ እና ችግር በመፈጠሩ ነው ይህ ለውጥ የመጣው። ይህ መንግስት ከእዛ ብዙ ተምሯል ብለን እናስባለን። ከእዛ አኳያ ያንን ለመንግስት እንተወውና በእኛ በኩል በየትኛውም አገር በእዚህ ጉዳይ ኃላፊነት ያለው ምርጫ ቦርድ ነው። ምርጫን በተመለከተ የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንኳን ጣልቃ ለመግባት ኃላፊነት የላቸውም። በምርጫ ቦርዱ የምርጫ ሰንጠረዥ መሰረት መራጮችን ማስተማር፣ ማሳወቅና ስለመብታቸው የማስገንዘብ እንዲሁም ለምን እንደሚመርጡ ስራችን ይሆናል።
ሌላው የመታዘብ ስራ እንሰራለን።ምዝገባ ሲጀምር ትክክለኛ ሰዎች ምዝገባ ስለማድረጋቸው እንመለከታለን። ብዙ አገሮች ላይ የታዘብናቸው አሉ። እኔ አፍሪካ ውስጥ ብዙ ምርጫዎች ላይ ተሳትፌያለሁ። ዚምባብዌ፣ ኮንጎ፣ ብሩንዲ፣ የሱዳን ሪፈረንደምንም ሲካሄድ ታዝቤያለሁ። ብዙ የገጠሙን ነገሮችም ነበሩ። አንዳንዶቹ አገራችን ውስጥ ይከሰታሉ ብዬ የማላስባቸው ነገሮች ሆነው ተመልክቻለሁ። መታወቂያቸውን ይዘው ሰዎች ማንነ ታቸው እየተጣራ ሲመዘገቡ አይቻለሁ። ከሲዳማ ሪፈረንደምም ልምድ አለን።
ምዝገባው መጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀመር ይጠበቃል። ከእዚህ ቀን ጀምሮ በያለንበት ጣቢያ ላይ በሚኖሩ ወደ 83 የምርጫ ዞኖች በምንችለውና ባለን የሃብት መጠን ለመሸፈን ጥረት እያደረግን እንገኛለን። ግን ከደንቦችና ከአሰራሮች እንዳንወጣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ይመራናል። ይህም ከምርጫ ቦርድ ጋር ተጣጥሞ የወጣው ህግ ጋር ተያይዞ እኔን እንደ ሲሲ አር ዲኤ ወይም እንደፎረሙ ሊቀመንበር ካየኸኝ በውስጡ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም አሉ።
አዋጁ በአሁኑ ሰዓት የውጭ ድርጅቶች የምርጫ መታዘብንም ሆነ የማስተማር ነገሮችን አልፈቀደም። ስለዚህ ጥንቃቄ አድርገን አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች ብቻ ምርጫውን የማስተባበርና የማስፈጸም ተግባር እንዲፈጽሙ ተደርጓል። ይህ በአዋጁ የተቀመጠ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወንና መንግስትም ትኩረት የሰጠው ጉዳይ በመሆኑ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም
ተገንዝበውታል። በልማት ስራ ላይ አጋሮቻችን ናቸው። መንግስት በራሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት እውቅና የሚያሰጣቸው እንደአፍሪካ ሕብረት አይነት ታዛቢ አካላት አሉ።
አዲስ ዘመን፡- ለሥራው ምን ያህል በጀት ተመድቧል? ምን ያህልስ የሰው ኃይል ታሳትፋላችሁ ?
ዶክተር ንጉሱ፡- በእዚህ ጉዳይ እውነት ለመናገር ለጋሾች ያን ይህል ገፍተው የሰጡን የለም፡ ግን አንድ ድርጅት ኤን ዲ አይ (ናሽናል ዴሞክራቲክ ኢንስቲትዩት) የተባለ የአሜሪካ ድርጅት የምዝገባውን ሂደት ብቻ ለመታዘቢያ 100 ሺ ዶላር (አንድ መቶ ሺ ዶላር) ፈቅደውልናል።ድጋፉ በየምእራፉ የሚቀጥል ይሆናል።ሌላ ያገኘነው ገንዘብ ስለሌለ ከእዚህ በመነሳት ሙሉውን ባንደርስም 178 ታዛቢዎችን በ2 ሺ 123 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለመወከል ተዘጋጅተናል።አይ አር አይ የተባለ ድርጅት በተለይ ለሲሲ አር ዲኤ 50 ሺ ዶላር ሰጥቷል።በጋራ ካቀድናቸው ጣቢያዎች ውጪ ለመጨመር የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራን እንገኛለን።የአውሮፓ ህብረት ኢካስ የሚባል ድርጅት ወጪ እንዲሸፈን እየተነጋገርን ነው።
አዲስ ዘመን፡- መንግስት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን በሚል በር ቢከፍትም በአንዳንድ አካባቢዎች እንቅስቃሴን የማገድ ነገር ይታያልና በመታዘብ ስራችሁ ተግዳሮት እንዳይሆን ምን ትላላችሁ?
ዶክተር ንጉሱ፡- እኛ በፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ እጃችን ጣልቃ አይገባም።እነሱ ለመመረጥ፣ ዞሮ ዞሮ ለስልጣን ነው የሚሄዱት።ያዋጣቸውን መንገድ ለዘመቻ ይዘው ይነሳሉ።እኛ ግን ሁልጊዜም መታወቅ ያለበትና የምንለው ምርጫ ሲካሄድ የምርጫ ኡደትን ተከትሎ እንዲሰራ ነው።የምርጫ ኡደት ከምዝገባ ሰዓት ጀምሮ የሚከሰቱ ውጥረቶችን አደጋ ለመቀነስ አስቀድመን ተዘጋጅተን የሰላም ግንባታ ስራ ለመስራት አስበናል።ነገሮችን የሚያበርድ፤ የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ተሰሚነት ያላቸውና በብዙሃኑ የሚከበሩ ሰዎችን አካትተን ለማቋቋም እየተዘጋጀን እንገኛለን።እነዚህ አካላት ችግር በሚፈጠርበት አካባቢ ተገኝተው ነገርን ለማብረድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።ብዙ አገሮች ላይ ምርጫን ተከትሎ የተከሰቱ ነገሮች አሉ። በተግባርም በ1997 ዓ.ም በተካሄደ ምርጫ ተመልክተናል።
አዲስ ዘመን፡- በጎ አድራጎት ማህበራት በምርጫ 97 የታዛቢነት ሚና ምን ይመስል ነበር?
ዶክተር ንጉሱ፡- በወቅቱ የእዚህ (የሲሲ አር ዲኤ) የቦርድ ሊቀመንበር ነበርኩ። በእዛ ጊዜ ፈተና ነበር። ምርጫም እንዳንታዘብ ተከልክለን ነበር። ቢቸግረን የቦርዱ መሰብሰቢያ የነበረው (ቃለ ምልልስ የተደረገበት የሲሲ አር ዲኤ መሰብሰቢያ ክፍል) ይህ መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው። በወቅቱ የደረስንባቸው ውሳኔዎች ነበሩ። እርሱም ምርጫ ቦርድን እንክሰስ የሚል ነበር። ግን ማንን ማን ላይ ነው የምንከሰው በሚል ጭቅጭቅ ተፈጥሮ ነበር። ራሱን በራሱ ላይ የሚደረግ ክስ ይቅር አያዋጣም፤ ህግ አውጭው፣ ህግ አስተርጓሚውና ሕግ አስፈጻሚው አካል ያልተለያዩበት ሁኔታ ስለነበር በክሱ ላይ ብዙም ተስፋ አልነበረንም። ግን እንክሰስና በታሪክ ይቀመጥ ብለን በድምጽ ብልጫ ተወስኖ የያኔውን ምርጫ ቦርድን ከሰስን።
ሁሉም ዳኞች አንድ አይደሉም ለሕሊናቸው የቆሙ ዳኞችም አሉ። ይሄ ዳኛ ለምርጫ 97 አናጎሜዝ የምትመራው ሃይል ከአውሮፓ ህብረት ታዛቢ እየመጣ ባለበት ሁኔታ፣ ከሰሜን አሜሪካ ደግሞ በጂሚ ካርተር የሚመራ ሃይልም እየመጣ፤ የራሳችንን ዜጎችን እንዳይታዘቡ መከልከል አይገባም በሚል ይመስላል ለእኛ ወሰነ። ምርጫውንም እንድንታዘብ ተፈቀደ። ውሳኔውን ስንሰማ በድል አድራጊነት ስሜት ተደሰትን። ከእኛ በተቃራኒ የቆሙ ባልደረቦቻችንንም ወቀስናቸው።
ሆኖም ምርጫ ቦርድ አላፈረም ወደ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሄደ። ‹‹ፍርዱ ትክክል አይደለም›› በሚል ይግባኝ አሉ። ግን አሁንም እንደሚሸነፉ ስላወቁት ምርጫው አንድ ወር ከምናምን ሲቀረው ለሌላ ጊዜ ተቀጠረ። የትም አይደርሱም ከአዲስ አበባ ሳይርቁ እናስቀራቸዋል የሚል ይመስላል። ምርጫው ግንቦት ሰባት ቀን 1997 ዓ.ም እሁድ ሊካሄድ አርብ ዕለት ግንቦት አምስት ቀን 1997 ዓ.ም 11፡ 00 ሰዓት ተቀጠረ።
እስከመጨረሻው የራሳችንን ዝግጅት እያደረግን ቆየን። ማሰልጠኑን፣ ማስተማር፣ ተሽከርካሪዎችን የማዘጋጀት፣ አባሎቻችንን ማሰባሰብን ሰራን። እንደተወሰነ በየአቅጣጫው ስምሪት አደረግን። የወከልናቸው ሁሉ ባሰማራናቸው ቦታዎች አስመርጠውና አስቆጥረው ተመልሰዋል። በቆጂ ላይ ብቻ ከሆቴል እንዳይንቀሳቀሱና በምርጫ ጣቢያ እንዳይደርሱ ተከልክለዋል። ያንን ትግል በማድረጋችንም እንደጠላት ተፈርጀን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ አዋጅ ቁጥር 621/2001 እንዲወጣ ነው የተደረገው።
በዚህ አዋጅ እንደልባችን እንዳንቀሳቀስ ታጠረ። እንደተቃዋሚ ተቆጠርን። 10 ዓመታት ገድቦን የኖረው ያ ህግ ነው። ህጉ ከጸደቀ በኃላም የኤጀንሲው በኃላፊነት የተሾሙት ሰው ነገሮችን የበለጠ አጠበቡት። በተለይም ሲሲአርዲኤ አስተባባሪ ስለነበር ዋነኛ ጠላት ተደርጎ ታየ። ያን ጊዜ በእዚህ ያሳለፍነው በእዛ መልክ አሳለፍን። ከባድ የፈተና ጊዜ ነበር። ህጉ ሲጸድቅና ስራ ሲጀምር እኔም በሌላ ስራ ምክንያት ከአገር ወጣሁ። አሁን አዲስ ህግ ሲጸድቅ ከስድስት ወራት በፊት ወደ አገሬ ተመልሻለሁ።
አዲስ ዘመን፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ አዋጅ ቁጥር 621/2001 ወጥቶ መተግበሩ በአገሪቱ ላይ ምን አስከትሏል?
ዶክተር ንጉሱ፡- እውነት ለመናገር አንደኛ የሞራል ውድቀት አሳድሯል። ብዙ ነገርም ገድቧል። በጎ አድራጎት ማህበሩ እንዳይኖር አድርጓል። በአገሪቱ ላይም ትልቅ የልማት ኪሳራ ነው አድርሷል። በተለይ በሲቪክ ማህበረሰቡና በማህበረሰቡ አካባቢ ብዙ ስራዎች ተገድበዋል። መንግስት ፊት በመንሳቱና በአዋጅ በመገደቡ ደጋፊዎቻችንም ብዙዎቹ ድጋፍ አቆሙ። በተለይም በሰብአዊ መብት ዙሪያ፣ በሰላምና በማህበረሰብ ልማት ግንባታ፣ከዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ ከምርጫና ከመሳሰሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ይሰሩ የነበሩ ድርጅቶች በሙሉ ስራቸውን አቆሙ፣ ብዙዎቹም ተዘጉ።
ከ90 በመቶ በላይ ገንዘብ ከውጭ አካላት የሚያገኝ ድርጅት ተብሎም በውጭ ድርጅትነት ይመዝገብ የተባለበት ሁኔታም ነበረ። በእርግጥ በጉዳዩ አንዳንድ ጥያቄዎችን አቅርበን ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ ቢሯቸው ሰብስበው አናግረውን ነበር። በእዛን ጊዜ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልማት ኮሚሽን ኃላፊ እንደመሆኔ ከእዚህም ከእዛም መጣሁ የማትል፣ ከኢትዮጵያ ሌላ መክሰስ የማትችልና ከጃንደረባው ጀምሮ ተቋቁማ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን 90 ከመቶ ከውጭ ስለምታገኝ ውጪ ሄደሽ ተመዝገቢ ስንል የት ሄዳ ነው የምትመዘገበው? የሚል ጥያቄ አንስቼ ነበር።
ይሄንን አይነቱን እናየዋለን ተብሎ እንደገና ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በጎ አድራጎት ማህበር ተብለው እንዲመዘገቡ ተደርጓል። ግን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የመብት ጉዳይ ላይ እንዳይሰራ በማድረግ ህገ ወጥ ነገሮች ተደርገዋል። በእዛ ወቅት አራት ሺ የሚደርሱ በጎ አድራጎት ማህበራት ነበሩ። ባለፈው ሳምንት በቀረበ ሪፖርት እንደሰማሁት ድጋሚ ምዝገባ ያደረጉት ሁለት ሺ አይሞሉም። ብዙዎቹ ከስመዋል። በእርግጥ በቀረበው ሪፖርት ከ680 በላይ አዲስ ተመዝጋቢ ድርጅቶች አሉ። አዋጅ ቁጥር 621/2001 ለእነዚህ ድርጅቶች መጥፋት አንዱ ምክንያት ነው የሆነው። በአየር ንብረት ለውጥ፣ በአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ፣ ከግብርና ስራ ጋር ተያይዞ የሚሰጠው የኤክስቴንሽን ስራ፣ ከከፍተኛ ተቋማት ጋር በተገናኘም የሚደረገው የምርምር ስራን ገድቧል። ያደረሰው ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም።
በጥቅሉ የሞራል ውድቀት አምጥቷል ማለት ይቻላል። በውጭ ምንዛሬ ይገባ የነበረው ገንዘብ ጥቅሙ የመንግስትም ነበር። ይሄንን ሁሉ ነው ያሳጣው። ምናልባት ይሄ ከምንም አልተቆጠረም።ከስልጣን ስለማይበልጥ በወቅቱ መንግስት ያስበለጠው ስልጣንን ነበር። ለደሃው ህብረተሰብ ማቅረብ ይቻል የነበረው የጤና ጉዳይ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲገደብ በማድረግ ስራው እንዲስተጓጎል አድርጓል። መንግስት ፖሊሲ ማውጣት እንጂ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ ውጤታማ ይሆናል ብዬም አላምንም። ይሄንን በደርግ ስርዓተ መንግስትም አይተነዋል። ባልትና እስከመሸጥ ድረስ መንግስት የሄደበት ሁኔታ ነበር። ያ ኢኮኖሚ የትም አላደረሰንም። ስለዚህ የሲቪል ማህበረሰቡ መሯሯጥና ለህብረተሰቡ አንዳንድ ነገሮችን ማድረግ ብዙ አስተዋጽኦዎች ይኖሩት ነበረ።
አዲስ ዘመን፡- በ2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ በሚጠበቀው አገር አቀፍ ምርጫ ጥምረቱ አቅም ከመገንባት እና ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ ሚናው ምን ይሆናል?
ዶክተር ንጉሱ፡- የተለያዩ አገራት ልምዶችን በመውሰድ እምንተገብረው ይሆናል። መቼም እንደ አለመታደል ሆኖ በአገራችን በተካሄደ ምርጫ እንድንማር፣ ልምድ እንድንቀስም አልተደረገም። ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሆኖ ያየነው በትንሽም ቢሆን ምርጫ 97 ነበር። አለመታደል ነው የምለው አንድን ነገር የምትማረው ስትሰራው በመሆኑ ነው። በተግባር ስትሰራው፣ ምርጫውን ስትታዘብ፣ በየጊዜው ሂደቱን ስትከታተል እና ስትሳተፍ ትምህርት ታገኛለህ፣ ታሻሽላለህም። በነበረው ሁኔታ ግን ከእዛ ውጪ ነን። ልምዱ የነበራቸው ሰዎችም በምርጫ 97 ግማሾቹ ታስረዋል፣ ተሰድደዋልም። እናም ብዙ ነገር አጥተናል።
አሁን የሚሰባሰቡ ሰዎችን ስልጠና የመስጠትና ልምድ እንዲቀስሙ የማድረግ ሁኔታ ይኖራል። ምርጫ ቦርድ በሲዳማ ሪፈረንደም እንድንሳተፍ ሲጠይቀን በተግባር መሳተፋችን ብዙ ነገር በማየት ለቀጣዩ በቂ ትምህርት እንቀስማለን ከሚል ነው የተሳተፍነው።በመሆኑም ብዙ አባሎቻችንን የአሰልጣኞች ስልጠና የመስጠት፣ ህብረተሰቡን የማሰልጠንና ግንዛቤ መፍጠር በእቅዳችንም ይዘነዋል። ስራውንም በአጭር ጊዜ ውስጥ የምንሄድበት ነው።ግን የምናካሂደው የምርጫ ቦርድን የስራ መርሀ ግብር ተከትለን ነው። አሁን ራሳችንን በማደራጀት ላይ ነን።
አዲስ ዘመን፡- ስለምርጫ 97 ደጋግመው አንስተውልኛል። በወቅቱ ከነበረው የምርጫ ሂደት መወሰድ አለበት የሚሉትን መልካም ተሞክሮ ቢነግሩኝ?
ዶክተር ንጉሱ፡- በእዛን ጊዜ ሲቪል ሶሳይቲ ተብሎ ባይታወቅም አባላቱ 320 ይደርሱ ነበር። አሁን ከ400 አልፈዋል። በእዛ ወቅት አንድ ሆኖ በእልህ የሚሰራ ነበር። እልህ ለጥሩ ነገር መልካም ነው። እንድትማር፣ ብዙ እንድትሰራ ያደርጋል። ያን ጊዜ የነበረው ስህተት ሁለተኛ እንዳይደገም አቅምና ህጉ በፈቀደ መጠን አሁን እንድንሰባሰብ ረድቶናል። ከነበሩት እስከመጨረሻው ደረጃ የሄድነው 34 ድርጅቶች ነበርን።
ወደመጨረሻው የቀረነው ደግሞ 15 የምንሆን ነን። በሰዓቱ የእኔም ድርጅት በምርጫው ለመሳተፍ ደስተኛ አልነበረም። እንዲታዘቡ ከተላኩት ገዢው ፓርቲ ስለተሸነፈ ከስራቸው የተባረሩም ነበሩ። ብዙ ነው ታሪኩ። ከእዛ የምንማረው ነገር ቢኖር አሁን ብዙ መሻሻሎች ያሉት በመሆኑ እርስ በእርሳችን በጋራ መቆም እንዳለብን ነው። በተቻለ መጠን ከየትኛውም ያልወገንን መሆን ይገባል። የምንደግፈው ሊኖር ይችላል። ያ የግል ጉዳይ ነው። መምረጥ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መብት ቢሆንም ከስራው ጋር እንዳይገናኝ መጠንቀቅ ይገባል።
ምክንያቱም በተለይ ዕድሉን ያጡ ኃይሎች ስም ሊያጠፉ፣ ወቀሳ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ማንም ሰው ጥፋት ቢሰራ፤ መንግስትም ሆነ ገዢው ፓርቲ ላይ የምንመለከተውን ነገር ከመተቸት ወደ ኋላ አንልም። ይህንን አስቀድመን አሳውቀናል። ያ እንዳይደገም ጥንቃቄ እናደርጋለን። እድል የመጀመሪያ ነው። በለውጥ አራማጆች አማካኝነት የተገኘው ዕድል ላይደገምና ላይገኝ ይችላል። በመሆኑም የመጀመሪያውን ዕድል አጥብቀን መያዝ አለብን።
አዲስ ዘመን፡- በተለያዩ አገራትና በአገርዎ ጭምር ከተሳተፉባቸው የምርጫ ሂደቶች በመነሳት አንዳንድ ፖለቲከኞች የሚያስቀምጡት የቅድሚያ ግምት አለ። እርስዎ በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ ?
ዶክተር ንጉሱ፡- በተግባር ሂደቱን አይተን ውጤት እስኪነገር ድረስ የምንለው ነገር የለም። ይህ የእኛ ጉዳይ አይደለም። ሌላው ቀርቶ የመንግስት መስሪያ ቤትም ጉዳይ አይደለም። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጉዳይ ነው። በምንታዘብበት ሰዓት የምናየው ነገር ካለ እንኳን ከቦርዱ ውጪ ለማንም አንነግርም። ለምርጫ ቦርድ ግን የታዘብነውን እንዲመለከቱ መረጃ እንነግራቸዋለን። ምርጫ ላይ በጣም ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል። አለበለዛ ትንሿ ነገር እሳት ልትጭር ትችላለች። ይህንን
ብዙ ተወያይተንበታል።
በተለያዩ አገራትም ብዙ ነገሮች ተመልክተናል። ከእነዛ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የማይከሰቱ የምንላቸው ግን ሌሎች አገራት የተከሰቱ አሉ። አንዳንድ ቦታ ላይ በህይወት የሌሉ ሰዎች መራጭ ይሆናሉ ተብለው መታወቂያ የተሰጠበት አጋጣሚ ነበር። ይህ ቀደም ሲል በዕቅድ ተይዞ ሲሰራበት የኖረ ነው። ለመጥቀስ ያክል ዚምባብዌ ላይ እ.ኤ.አ በ2013 ምርጫ ተመልክተናል። ውጤቱ የተነገረው ገና በምዝገባው ወቅት ነበር።
ዚምባብዌ ላይ ይህ የተደረገበት የእራሱ ምክንያትም ነበረው። ሙጋቤ በስልጣን ለመቆየት ያላደረጉት ጥረት አልነበረም። ታግለው የነበሩትን በወቅቱ ሕይወታቸው እንዲቀጠፍ ያደረጓቸው ብዙ ሰዎችም ነበሩ።
ምርጫን የመገልበጥ፣ የማጭበርበርና ሌሎች ነገሮች ተደርገው አይተናል። በኮንጎ እ.ኤ.አ 2018 በተካሄደው ምርጫ በጭራሽ ያልታሰበ ሰው ነበር አሸንፏል የተባለው። አብያተ ክርስቲያናት ህብረት 11 ሺ ታዛቢዎችን ስናሰማራ ካቶሊክ ብቻ 44 ሺ ገደማ ታዛቢ አሰማርተዋል። በተጨማሪነት የአፍሪካ ሕብረትና ሌሎችም ታዛቢዎች አሉ። ይህ ግለሰብ አሸንፏል እየተባለ እያለ ይፋ ሲሆን የተገለጸው ግን ሌላ ሰው ነው። እንዲህ አይነት ነገሮችም ይከሰታሉ። ይህ ችግር ያስከተለው ውዝግብ እስካሁን ድረስም አልበረደም። በአገራችን ይከሰታል ብዬ የምለው ግን የለኝም። በተቻለ መጠን እነዚህን እንደምሳሌ እያነሳን እርስ በእርስ እየተወያየን ጥንቃቄ እናደርጋለን። በታዛቢነት ስንሳተፍ ምንም ነገር ውስጥ ላለመግባት ነው አንዱ ዝግጅታችን።
አዲስ ዘመን፡- ምናልባት አሁን ሌሎች አገሮች ተከስቷል ብለው ካነሱልኝ መካከል አንዳንድ ፖለቲከኞች ከሚያነሱት የቅድመ ግምት ጋር ይገናኛል አፈና፣ ማጭበርበር፣ ኮሮጆ መገልበጥና የመሳሰሉት እንዳያጋጥም ሚናችሁ ምንድን ነው? ምንስ መሰራት አለበት?
ዶክተር ንጉሱ፡- የምርጫ ቦርድ ስራ ቢሆንም ኮሮጆ እስከሚከፈትበት ሰዓት ታዛቢ በምንሆንበት ጣቢያ ላይ መገኘት አለብን። ለድምጽ መስጠት ዝግጁ ለማድረግም ኮሮጆ ሲከፈት ተገልብጦ ባዶ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አንዱ ስራችን ነው። ምርጫው ተጀምሮ ኮሮጆ እስከሚዘጋበት ሰዓት መለየት የለብንም። ታዛቢ የሆኑ አባሎቻችን ተቆጥሮ እስኪፈራረሙ ድረስ ይቆያሉ። ቢያሳድርም እስኪጠናቀቅ ዋጋ ይከፍላሉ። ይህንን ደግሞ በአጭር ጊዜ በተሳተፍንበት የሲዳማ ሪፈረንደምም አድርገነዋል። በሌሎችም አገራት ላይ ይሄንን ነው ያደረግነው። ከተቆጠረ በኋላ ያለው ጉዳይ የእኛ ሥራ አይደለም። የየጣቢያችንን ውጤትም እኛ እንይዛለን። ያየነውን እና የተከሰተውንም እንመዘግባለን።
በእኛ አገር ፖለቲከኞች ቀድመው ምርጫው ሳይካሄድ ብዙ ያወራሉ። ብዙ ነገርም ያደርጋሉ። የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጠው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በተቻለን መጠን በተሰጠን ስልጣን፣ የጊዜ ገደብና ስፍራ ላይ ክትትል የማድረግ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ለምርጫ ቦርድ ሪፖርት ማድረግ ብቻ ነው ከእኛ በኩል የሚጠበቀው።
አዲስ ዘመን፡- የምርጫ ውጤቱ ከሚያስከ ትለው ውጤት አንጻር ብጥብጥ ሊያስነሳ ይችላል በሚል ስጋት አንጻራዊ ሰላም እስኪፈጠር ድረስ ቢራዘም ይሻላል የሚሉ ወገኖች አሉ። እርስዎ ስጋቱ ለመራዘም ተጨባጭና ምክንያታዊ ነው ይላሉ?
ዶክተር ንጉሱ፡- ውሳኔው የምርጫ ቦርድ ነው። ግን በአንድ በኩል የሚኖረኝ ምልከታ ቢራዘም ምን ልናሻሽል እንችላለን የሚል ነው። ሰላም ማምጣት እንችላለን ወይ ? ከሆነ ለምን እስከ አሁን አላደረግነውም። ባለፉት ከ12 እስከ 18 ወራቶች ውስጥ ያላመጣናቸው የሰላም ነገሮች ከሌሉ ቢራዘም እናመጣለን የምንልበት ዋስትናው ምንድን ነው? ስድስት ወራትም ይሁን ሁለት ዓመታትም እናራዝም ብንል ምን ሊመጣ ይችላል። ይሄ ችግር የመጣው ለውጥ ከተደረገ በኃላ ሰው ነጻነት በማግኘቱ ነው። አንዳንዴ ዴሞክራሲ ስንጠይቅ መብታችንን ይከበር በማለት እየጠየቅን ነው። ግን አንዳንዴ የማየው ግዴታችንን እየሳትን ይመስለኛል። ከህግ ውጪ መሆን አይገባም። ለረጅም ዓመታት የኖርኩበት እንግሊዝም ሆነ የትኛውም አገር ከህግ ውጭ የሚሆን ነገር ካለ ተጠያቂ ነው የሚያስደርገው።
አሁን መንግስት ሆደ ሰፊ ሆኖ ሲችልና ሲያቻችል ይታያል። ይህ እንደውም አንዳንዶቹን መረን እንዲለቁ አድርጓቸዋል ነው የምለው። ከሚገባው ቃላት ውጪ መጠቀም ተገቢ አይደለም። ገደብም ያስፈልጋል። በእኔ በኩል ጊዜውን የማራዘም መብቱ የምርጫ ቦርድ ነው። አንዳንዶቹ እንዲህ የሚሉ ሰዎች ምናልባትም ለራሳቸው ጊዜ ለማግኘት ካልሆነ በስተቀር ይሻሻላል ከሚል ነው ብዬ አላስብም። ዞሮ ዞሮ ግን ውሳኔው የምርጫ ቦርድ ነው። እኔ ግን ብዙ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላምንም።
ምርጫዎች ሲካሄዱ ውጥረቶች ይኖራሉ። በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ሰዓትና ከምርጫ በኋላ ሊሆን የሚችለውን ከወዲሁ አውቀን እየተዘጋጀን እንገኛለን። ምርጫ ቦርድም የራሱን ዝግጅት እያደረገ ነው። በተቻለን መጠን ነገሮችን ለማብረድ በእድሜያቸው አዛውንቶች የሆኑና ችግሮችን ለማብረድ የሚችሉ ሰዎችን ለማሳተፍ ጥረት እያደረግን ነን። እንግዲህ የሚነሱ ስጋቶች ሊኖሩም ላይኖሩም ይችላሉ። ግን ‹‹ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም›› ስጋቱን ፈርተን ለምርጫው ሌላ አምስት ዓመት እንጨምር ብንል አይሆንም። ምክንያቱም የሕዝቡ ፍላጎትና ለአገሪቱ መረጋጋት፣ ለልማት ምርጫው መካሄዱ ይመረጣል። አጋሮቻችን አንድ ነገር ላይ ደርሶ ማየት ይፈልጋሉ።መቼ ነው፣ እንዴት ነው የሚካሄደው ለሚለው ምላሽ ይሆናል። እንደኔ ከሆነ በዕቅዱ መሰረት ይካሄዳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
የጊዜውን መራዘም ጉዳይ በተመለከተ ከሲቪል ሶሳይቲው ጋር የሚገናኝ ነገር አይደለም። ይሄ የምርጫ ቦርድ ከህገ መንግስቱና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በማገናዘብ አደናጋሪ ነገሮች እንዳይፈጠሩ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት ነው። ዞሮ ዞሮ እኛ የምንከተለው ምርጫ ቦርድ የሚሰጠውን ጊዜ ነው።
አዲስ ዘመን፡- ታግተዋል የተባሉ ተማሪዎች ባልተፈቱበት፣ በህግ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችም ባልተያዙበት፤ እንደልብ መንቀሳቀስ በማይቻል በትና በመሳሰሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ምርጫውን ማካሄድ ምን ያህል ውጤታማ ያደርጋል ? እናንተ ተንቀሳቅሳችሁ ለመታዘብስ ያስችላችኋል ወይ ?
ዶክተር ንጉሱ፡- ይህ ከጸጥታ ጋር የሚገናኝ ነው። በተለያየ መድረክ ላይ አንስተነዋል። በተለይ አንዳንድ ቦታዎች በኮማንድ ፖስት ስር ናቸው። በእንዲህ አይነት አካባቢ ላይ እንዴት እንደሚካሄድ፣ ታዛቢዎች መድረስ የሚችሉበት ሁኔታ ዝርዝር ሁኔታዎች ይታያሉ። ይህንን ምርጫ ቦርድና የጸጥታ ኃይሎች እየተወያዩ የሚያከናውኑት ነው። እዛ ቦታ ላይ ሰዎች ታግተዋል የሚሉትን እኛም በብዙሃን መገናኛ መረጃ እንሰማለን። ይሄ ከምርጫው ጋር ምን ያህል ይያያዛል የሚለው ጥያቄ ቢሆንም መንግስት ከምርጫ ቦርድ ጋር ተወያይቶ የሚወስነው ይሆናል።
የሰዎች መፈታትና መታሰርን በተመለከተ በየትኛውም አገር ላይ ቢሆን ወንጀል ያለባቸው ሰዎች ሲኖሩ ይታሰራሉ ይፈታሉም። ይህ ከፍትህ ስርዓቱ ጋር ተይይዞ የሚሆን ነው። መንግስትና ምርጫ ቦርድን አንድ ላይ የሚያገናኛቸው ነው። እንደሲቪል ማህበረሰብ የጸጥታ ሁኔታን አጣርተን ነው ታዛቢዎቻችንን የምናሰማራው።
አዲስ ዘመን፡- የሚካሄደው የዝናብ ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለመንቀሳቀስ ምቹ አይደለም በሚል የሚነሳ አስተያየት አለ። እናንተ በዕቅዳችሁ መሰረት ሰዎች ልካችሁ ለመታዘብ ምን ያህል ምቹ ነው?
ዶክተር ንጉሱ፡- ይሄ የቁርጠኝነት ጉዳይ ነው። ብዙ አገር ምርጫ በበረዶ ሰዓትም ሊካሄድ ይችላል። በበረዶ ወቅት ተከናንበው ምርጫ አካሂደው ይመለሳሉ። ነሐሴ 10 ቀን ይበልጥ የዝናብ ወቅት ነው። አሁን ወደ ነሐሴ 23 ተዘዋውሯል። ይሄ ጊዜ ነሐሴ ወር እያለቀ ነው፣ አንዳንድ ቦታዎች ዝናብ ቢሆንም ብዙ ቦታዎች በተለይም ቆላማ፣ ወይና ደጋ ቦታዎች ብዙ ዝናብ ይኖራል ብዬ አልገምትም። ስለዚህ ብዙም የእኛን ታዛቢዎች አያግዳቸውም። ለመታዘብ ቆርጠን ተነስተናል። በሚካሄደው ምርጫም ደስተኞች ነን። የዝናብ ጊዜም ቢሆን ብዙ ችግር ያመጣል ብዬ አላስብም።
አዲስ ዘመን፡- መንግስት ነጻ ምርጫ አደርጋለሁ ብሎ በገባው ቃል መሰረት እንዲሳካ የጥምረቱ አባላት ነጻ፣ ገለልተኛ መሆናቸውና ከየትኛውም አለመወገናቸው የሚረጋገጠው በምንድን ነው?
ዶክተር ንጉሱ፡- እያንዳንዱ ሰው በውስጡ የራሱ ፍላጎት ሊኖረው ይችላል። ያ በግሉ ነው። ግን ለመታዘብ ወደ ምርጫ ጣቢያ በሚሄድበት ሰዓት የጥቅም ግጭት እንዳይኖር በተቻለ መጠን ጥንቃቄ እንዲደረግ ደግመን ደጋግመን እርስ በእርሳችን ተነጋግረናል። ካልሆነ ግን አንድ ሰው በሚፈጥረው ችግር ለሲቪል ሶሳይቲው ሌላ ስም ይሰጠዋል። በእዚህ አኳያ ከፖለቲካ ሳንወግን ከየትኛውም ወገን ሳንሆን ምርጫውን ለመታዘብ ተዘጋጅተናል።
ተገቢ ያልሆነ ነገር ስንሰራ ብንገኝ ሪፖርት ይደረጋል። ያ ደግሞ ያስጠይቃል። የምርጫ ስነ ምግባር፣ የታዛቢዎች ስነ ምግባር መመሪያ አለ። በሰነዶቹ መሰረት ሂደቱን እንከታተላለን፣ እንለካለንም። ከእዚህ ውጪ የሆነ ሰው ካለ ርምጃ የምንወስድበት ሁኔታ አለ። በምርጫው ሂደት የስነ ምግባር ጉዳይ ለሲቪል ማህበረሰብ ወሳኝ ነው። እገሌ እንዲህ ነው ተብሎ ደም ውስጥ ተገብቶ የሚለይበት ነገር የለም። ግን ርግጠኛ ነኝ ደጋግመን ስለተነጋገርንበት ሁሉም አውቆት ወደስራ ይገባል። ሁላችንም ኃላፊነት ያለብን ከመሆናችን አኳያም በእዚህ ረገድ ያን ያህል ችግር ይፈጠራል ብዬ አላስብም።
አዲስ ዘመን፡- ጥምረቱ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ገለልተኛ ሆኖ ተአማኒነትን ያተረፈ ምርጫ ሊያካሂድ ይችላል? ከመንግስት፣ ከተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ስውርና ረጃጅም እጅ ታድጋችሁ እምነትን ያተረፈና በታሪክ የሚመዘገብ ስራ እንሰራለን ብላችሁ ታምናላችሁ?
ዶክተር ንጉሱ፡- እኔ ይቻላል ነው የምለው። ከሁሉም ነገር ነጻ ነን። እንደውም ባይገርምህ ከጥምሩም ባሻገር መንግስት የሌለበት የሲቪል ማህበረሰብ ምክር ቤት በቅርቡ ይቋቋማል። የፎረሙ የቦርድ ሰብሳቢ እንደመሆኔ ታስክ ፎርስ አቋቁመናል። በታስክ ፎርሱ ተከታታይ ስብሰባዎች በማድረግ ላይ ነን። ራሳችንን በእራሳችን ነው የምናስተዳድረው። ንቁ፣ በራሱ የሚንቀሳቀስና በምንም ነገር ወደኋላ የማይል አካል ለማደራጀት እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። ከምርጫው ጋር በተገናኘ መንግስት የሌለበትን ምክር ቤት እያቋቋምን ነን። በቅንጅቱ በኩል ግን የተለየ ፍላጎት ያለው አንድም አካል ወደ ውስጣችን ሊገባ አይችልም።
አዲስ ዘመን፡- ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራ ሲያዊ፣ ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን ከህዝቡ፣ ከተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከመንግስት፣ ከጸጥታ አካላትና ሌሎች ይመለከታቸዋል ከምትሏቸው ምን ትፈልጋላችሁ ?
ዶክተር ንጉሱ፡- ሕብረተሰቡ ባለበት ደረጃ ግንዛቤ አግኝቶ፣ ምርጫ ለምን እንደሚጠቅመው ተገንዝቦ እንዲመርጥ ያስፈልጋል። ‹‹መርጠነዋል፣ ይሰራልናል›› ማለት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንፈልጋለን። የከተማ፣ የወረዳ፣ ሹም ነገ ሊጠይቁት የሚችሉትን ዜጋ ወይንም ኃላፊና ተቆጣጣሪ ለይተው ድምጽ መስጠትና መምረጥ ይጠበቅባቸዋል። ሕዝቡ ተሳታፊ እንዲሆን አሳታፊ ምርጫ ማድረግ ይኖርብናል።
እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ሰብአዊ መብት፣ዕንባ ጠባቂና የመሳሰሉ የዴሞክራሲ ተቋማትም ባግባቡ ስራቸውን መስራት አለባቸው። ባወጡት ህግ መሰረት የዜጎች መብት ስለመጠበቁ፣ መሳተፍ የሚገባቸው አካላት እንዲካተቱ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ሂደቱ በትክክል ስለመፈጸሙና ባግባቡ መካሄዱን መከታተልም ይኖርባቸዋል።
በየደረጃው የሚገኘው የመንግስት መዋቅር ምርጫ ቦርድ ባወጣው ህግ መሰረት ምርጫው ሲካሄድ ጸጥታ ተጠብቆ፣ ሕዝቡ ያለስጋት ወጥቶ መምረጥ እንዲችል የማድረግና የማስደረግ ኃላፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል። ትኩረት ሰጥተው በመከታተል ችግር ካለም ችግሩ እንዲበርድ ስራዎች እንዲሰሩ ከመንግስት አካላት እንጠብቃለን። በተለይም ከሰላም ሚኒስቴር የምንጠብቀው ትልቁ ኃላፊነት ይህ ነው። ኃላፊነት ስላለባቸውም ጭምር በሰላም ምርጫው እንዲካሄድ የሚችሉትን ሁሉ ሌላውንም እያስተባበሩ ጭምር መስራት ይጠበቅባቸዋል። እናም በሰላም እንዲካሄድ የማድረግ ሚና ስላለብን ይሄንን እናደርጋለን። በጥቅሉ ከሁሉም ጋር ተቀናጅተን አንዲት አገር ኢትዮጵያ፣ ያደገች የበለጸገች አገር ማየት እንድንችል ሁላችንም አንድ ሆነን እንድንሳተፍና መጪውም ጊዜ ብሩህ እንዲሆን የበኩላችንን ለመወጣት እንጥራለን ።
አዲስ ዘመን፡- የመጨረሻ መልዕክት ካለዎት ?
ዶክተር ንጉሱ፡- መጪው ምርጫ መቼም ቢካሄድ ሰላማዊ እንዲሆን፣ ሕብረተሰቡ ያለስጋትና ተጽእኖ ተሳትፎ የሚፈልገውን የሚመርጥበት እንዲሆን ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ ይገባል። የተመረጠው አካል በተመረጠበት ቦታ ላይ የመረጠውንም ሆነ ያልመረጠውን ሕዝብ እኩል አገልጋይነት ስሜት ተላብሶና ቃል ገብቶ የሚተገብርበት አስተሳሰብ መላበስ ይኖርበታል። እስካሁን የጎደሉ የሰላም እሴት የሚገነባበት፣ በልማት የጋራ ርብርብ በማድረግ ኢትዮጵያን ወደፊት የምናራምድበት ሁኔታ መፍጠር የሚቻልበት መድረክ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።
አዲስ ዘመን፡- ለነበረን ቆይታ በዝግጅት ክፍሉ ስም ከልብ አመሰግናለሁ!
ዶክተር ንጉሱ፡- እኔም ለተሰጠኝ ዕድል ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው!
አዲስ ዘመን መጋቢት 12 / 2012 ዘላለም ግዛው