• የልማት ተነሽ አርሶ አደሮችም የእድሉ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል
አዲስ አበባ፡-ለ376 ኢንተርፕራይዞች 92 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የካፒታል ዕቃዎች ሊዝ ግዥ በመፈጸም ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉን የአዲስ ካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር ገለጸ። በልማት ምክንያት ለተነሱ አርሶአደሮችም የተለያዩ ማሽኖች መስጠቱን ማህበሩ አስታውቋል።
የአዲስ ካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መሳይ ኢንሴኔ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፤ ማህበሩ ባለፉት ስድስት ወራት 92 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የተለያዩ የካፒታል ዕቃዎችን ግዥ በመፈጸም ለ 376 ኢንተርፕራይዞች አስተላልፏል። ከእነዚህ ኢንተርፕራይዞች ውስጥ 21 ማህበራት የልማት ተነሽ አርሶ አደሮች ናቸው።
ባለፉት ስድስት ወራት የካፒታል ዕቃዎች ሊዝ ፋይናንስ ስርዓት ተጠቃሚ ለመሆን 508 ኢንተርፕራይዞች ለማህበሩ ጥያቄ ማቅረባቸውን የተናገሩት አቶ መሳይ ለ376 ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ማሽኖች ግዥው ተፈጽሞ ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውንና ለ190 ኢንተርፕራይዞች ደግሞ 971 የማሽኖች በግዥ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ለተጠቃሚዎች ከተላለፉት መካከልም የብረታ ብረት፣ የእንጨትና የልብስ የስፌት ማሽኖች ይገኙባቸዋል ብለዋል።
376 ኢንተርፕራይዞቹ ውስጥ 21 የልማት ተነሽ አርሶ አደሮች ማህበራት መሆናቸውን አመልክተው 21ዱ ማህበራት 28 ነጥብ 9 ሚሊዮን ወጪ የተደረገባቸው የእህል ወፍጮዎች፣ የህትመት ማሽኖችና ተሽከርካሪ በማህበር ለተደራጁ ለ219 አርሶ አደሮች የተላለፈላቸው መሆኑን አብራርተዋል።
በዘንድሮ በጀት ዓመት 250 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ማሽኖችን ግዥ በመፈጸም ለኢንተርፕራይዞች ይተላለፋሉ ተብሎ ዕቅድ መያዙን ገልጸውልናል።
“99 በመቶ የሚሆኑት የእኛ ደንበኞች ስኬታማ ናቸው፤ ብድራቸውንም ከፍለው ጨርሰዋል ባለፉት ስድስት ወራት ከሊዝ ፋይንስ ተጠቃሚዎች መሰብሰብ የሚገባው ገንዘብ 29 ሚሊዮን ብር ሲሆን 28 ነጥብ 9ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል” ያሉት አቶ መሳይ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚ የሆኑት ኢንተርፕራይዞች አባላቶቻቸውን ጨምሮ ለ14ሺህ 438 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ገልጸዋል።
አክሲዮን ማህበሩ ከተቋቋመ አምስት ዓመት ቢሆነውም ሥራ ከጀመረ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ወዲህ እስካሁን ድረስ 330ሚሊዮን 332ሺህ ብር የሚያወጡ የተለያዩ ማሽኖችን በሊዝ ፋይናንስ ግዥ በመፈጸም ለሦስት ሺህ 156 ኢንተርፕራይዞች ማስተላለፉ ታውቋል። ከእነዚህ ኢንተርፕራይዞች ውስጥ 45 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብሩ የዋለው ለልማት ተነሽ አርሶ አደሮች እንደሆነ ማህበሩ ተገልጿል።
አዲስ ዘመን ጥር 15/2012
ጌትነት ምህረቴ
Профессиональный сервисный центр по ремонту бытовой техники с выездом на дом.
Мы предлагаем: сервис центры бытовой техники москва
Наши мастера оперативно устранят неисправности вашего устройства в сервисе или с выездом на дом!