ከአዲስ አበባ ከተማ 155 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገብረጉራቻ ከተማ ተወልደው አድገውበታል፡፡ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም የተከታተሉት በእዚህችው ትንሽ ከተማ ውስጥ ነው። ለትምህርት የነበራቸው ፍላጎትና ታታሪነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍልን እንዲቀላቀሉ አድርጓቸዋል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የሕግ ትምህርት ቤት በነበረበት፣ በዓመትም ከ50 ያልዘዘ ተማሪ በሚመረቅበት ወቅት በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ይዘዋል።
አሜሪካ ከሚገኘው ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍልም በሕግ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል።ከረዳት ዳኝነት እስከ ሕግ ማማከር ልምድ አካብተዋል።ቀይሽብር ችሎት በመባል የሚታወቀውን የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተከሰሱበት ችሎት ላይ በዳኝነት ተሳትፈዋል።አቶ ሰለሞን አረዳ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ሲሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እየመሩም ይገኛሉ ፤አቶ ሰለሞን አረዳ የዛሬው የተጠየቅ እንግዳችን ናቸው።
አዲስ ዘመን፡- አቶ ሰለሞን ማን ናቸው? የትምህርት ሁኔታና የሥራ ልምድዎን ይንገሩኝ?
አቶ ሰለሞን አረዳ፡- በመጀመሪያ ለስምንት ዓመት የሰራሁት ረዳት ዳኛ ሆኜ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው።ከዚያም ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሾምኩ።ይህንን የምነግርህ እንግዲህ ከዛሬ 22 ዓመት በፊት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የሕግ ትምህርት ቤት ብቻ በነበረበት ወቅት ማለት ነው።45 ተማሪ በዓመት የሚመረቅበት ጊዜ ነው።ለዚህ ነው ለተወሰኑ ጊዜያት ብቻ በረዳት ዳኝነት ከሰራን በኋላ በክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ በዳኝነት የተሾምኩት።ለአራት ዓመታትም ሰራሁ።የአምቦን ቆይታዬን በልዩ ሁኔታ ነው የምመለከተው።በተደጋጋሚ ነው ይህንን ነገር የማነሳው።ገና በ23 ዓመት ዕድሜ ላይ እያለሁ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ስር የሚወድቁ ከባድ ወንጀሎችን፣ የግድያ ጉዳዮችን፣ ከባድ ዘረፋ፣ በሞት ፍርድ የሚያስቀጡ ወንጀሎችን ፍርድ መስጠትን እመለከት ነበር።ምንም እንኳ ነባር ዳኞች ቢኖሩም ዞሮ ዞሮ ፍርድ መስጠት በጣም ከባድ ነበር።በዚያን ወቅት ያደረኳቸው ግን ደግሞ አሁን ቢሆን ኖሮ የማላደርጋቸው ብዬ የማስባቸው ነገሮች አሉ።
አዲስ ዘመን፡- የሚፀፅትዎትና የሚጠቅሱት ነገር አለ?
አቶ ሰለሞን፡- አዎ! ለምሳሌ ሰከን ብሎ ያለመናገር፣ መቸኮል፣ ልምድና እውቀት ያላቸውን ሰዎች ከመስማት ይልቅ እኛ ትክክል ነን ብለን የምናደርጋቸው ነገሮች አሁን ላይ ሳስበው ትክክል እንዳልነበርኩ አስባለሁ።አሁን ለወጣት ዳኞችም ሁልጊዜ እኛ ብቻ ትክክል ነን በማለት ለሌሎች ዕድል መንፈግና ስሜታዊ መሆንን እንዲያስቀሩ እመክራለሁ።
በአወንታዊ መልኩ የምወስደው ደግሞ በጣም ብዙ የተማርኩበት ነው።በወቅቱ ደግሞ አምቦ አካባቢ የዳኝነት ሥራ በጣም ፈታኝ የነበረበት ሰፊ እንቅስቃሴዎች ነበሩ።ትርምሶች ነበሩ።ተማሪዎች ሰልፍ ይወጣሉ፣ ይታሰራሉ፣ የዋስትና ጥያቄዎች ይቀርቡና ዋስትና እንፈቅዳለን፣ ከመንግስት አካላት ጋር የመነታረክ፣ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤቶች የሚሰጡትን ትዕዛዞች ያለመቀበልና መገፋፋቶች ነበሩ።እነዚያ ነገሮች በወቅቱ ትልቅ ተግዳሮቶች ናቸው።አሁን ለደረስኩበት ሕይወቴ ጠንካራና በራስ መተማመን ስላጎናጸፈኝ እንደ ትልቅ ዕድል ነው የምቆጥረው።
ዳኝነት በተለይም ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ ለማየት ችያለሁ።በዚያ የአፍላነት ዕድሜ ብዙ ነገሮች በማየቴም በአወንታዊ መልኩ እመለከተዋለሁ።አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም የሰዎችን መብት ከማስከበር አንፃር የሰራኋቸው ሥራዎች ዛሬም ድረስ እኮራበታለሁ።አራት ዓመት ከሰራሁ በኋላ ለቅቄ ንግድ ባንክ በአማካሪነት ተቀጠርኩ።እዚያም አልቀረሁም ተመልሼ ወደ ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኜ ተመልሼ አገለገልኩ።በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እድገት አግኝቼ በ1995 ዓ.ም ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ገባሁ።
ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በሕይወቴ ትልቅ ነው ብዬ የማስበውን ሥራ ሰርቻለሁ።ወደፊትም ቢሆን በኩራት ነው የምናገረው።ምክንያቱም የዳኝነት ወሳኙ ጉዳይ እሱ በመሆኑ ነው።ከወቅቱ ሙቀትና አየር ንብረት ጋር ብቻ ሳይሆን ወደፊትም በታሪክ አጋጣሚ በማህበረሰቡም በግለሰቦችም ራሳችን ስንጠይቅም ትክክለኛ ነኝ ብዬ የምወሰድው ነው።ይህ ማለት ሰዎች አይሳሳቱም ማለት አይደለም።ግን ዛሬም ድረስ የማይቆጨኝ አንዱ ነገር በወቅቱ ቀይሽብር ችሎት የሚባል የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተከሰሱበት ችሎት ላይ ለአራትና አምስት ዓመት ሰርቻለሁ።
ከዚያም በተለያዩ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰርቻለሁ።ድሬዳዋም በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኝነት ሰርቻለሁ።በ2001 ዓ.ም ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኜ ለአንድ ዓመት ከሰራሁ በኋላ በርቀት ትምህርት አምስተርዳም ዩኒቨርሲቲ ማስተርሴን ተማርኩኝ።
ትምህርት ላይ እያለሁ በግሌም እፃፃፍ ስለነበርና አዳዲስ ነገሮችን ለማወቅ እሞክር ነበር።ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ገቨርመንት ትምህርት ክፍል ተቀበሉኝ።ክፍያው ወደ 90 ሺ ዶላር ስለነበር ስፖንሰር ለማፈላለግ ከፍተኛ ጥረት አደረኩኝ።አንድ ዓመት አጣሁና እንደገና ወደ ሌላ ዓመት አስተላለፍኩኝ።በዚህ ሳልወሰንም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አመለክት ስለነበር ሴንተር ኦልኢንተርናሽናል የሚባል ዓለምአቀፍ ተቋም ሙሉ ወጪህን እንሸፍናለን ብለውኝ ወደ ቦስተን ሄድኩኝ።
እንደአጋጣሚ የሕግ ሰው መሆኔን የሚያውቅ ፕሮፌሰር መምህሬ የሕግ ትምህርት ቤት እንድማር ገፋፋኝ፤ የትብብር ደብዳቤም ፃፈልኝና ማስተርሴን ተማርኩ።ከዚያ ከሃርቫርድ ኬኔዲ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን ማስተርሴን ከጨረስኩ በኋላ እዚያው ሃርቫርድ የሕግ ትምህርት ክፍል በሕግ የማስተርስ ዲግሪ ሰራሁ።ተመልሼ ስመጣ ግን በርካታ ተግዳሮቶች ናቸው ያጋጠሙኝ።ስሄድ ፍቃድም ሆነ ሁሉንም ሕጋዊነት አሟልቼ ነበር የሄድኩት።ግን በወቅቱ መሄዴን አልወደዱትም ነበር።እኔም የመንግሥት ሥራ የመስራት ፍላጎት ስላልነበረኝ በቀጥታ ወደ ግሉ ዘርፍ ገባሁ።
የግሉ ዘርፍ ላይ የራሴን አማካሪ ድርጅት አቋቋምኩኝና ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ የሚባሉ ዓለምአቀፍ ድርጅቶችን የማማከር ዕድል አጋጣመኝ።በርካታ ገንዘብም አገኘሁ።ዓለምአቀፍ ፍርድቤቶች ጭምር እሰራ ጀመር።ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ ወደ መንግሥት ተቋም የተመለስኩት።እኔ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ተመልሼ እመጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር።ትንሽ ለራሴም ለቤተሰቤም እሰራለሁ ብዬ ነበር ያቀድኩት።ፍርድ ቤት ላይ ደግሞ ብዙ ቅሬታዎች አሉ።ስለለውጥ ይነሳል።ሃሳቡ አሁን ከመጡ አመራሮች ሲቀርብልኝ ጥሪውን ተቀብዬ መጣሁ።
አዲስ ዘመን፡- የቀይሽብር ችሎትን የመዳኘት ሂደት ምን ይመስላል?
አቶ ሰለሞን፡- በተቻለ መጠን ማስረጃዎችን ሰምተናል።አብዛኞቹ የሰነድ ማስረጃዎችና የሰው ምስክሮች ናቸው።በኢህአፓ፣ በመኢሶን በተለያዩ ምክንያቶች በአዲስ አበባ ከተማ ላይ የደህንነት ሚኒስትር የነበሩ እነ ተስፋዬ ወልደስላሴ፥ አብዮታዊ ማዕከላዊ ምርመራ የነበሩ መርማሪዎች እነዶክተር አለሙ አበበን ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበሩት በአጠቃላይ በዘር ማጥፋት ዘመቻ የተሳተፉ ሰዎች ክስ በጣም ብዙ ተም ሬበታለሁ።
ፍትሃዊ በሆነ መንገድ አስተናግደናል ብዬ አስባለሁ።በወቅቱ ስንሰራው የነበረውን ነገር ፍትሃዊ እንደነበር በስልክ ሳይቀር አስተያየታቸውን የሰጡን አሉ።በተቻለ መጠን በጥንቃቄ ነበር የምንሰራው። እንዲያውም አንዳንድ ውሳኔዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከደረሱ በኋላ ይሻሩብን ነበር።እኛም የወቅቱን ሁኔታ እናገናዝብና ጥፋትም አጥፍተዋል፤ ግን ወቅቱስ ምን ነበር የሚለውን ነገር ትኩረት ሰጠተን ነበር የምናየው።ለምሳሌ ኮሎኔል ደበላ ዲንሳን 13 ዓመት ገደማ ነው የቀጣነው።ግን እነ ዶክተር አበበ አለሙን ጨምሮ ጉዳያቸው ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መጥቶ ወደ ሞት ነው የተቀየረው።እኛ በወቅቱ ያገናዘብነው ደበላ ዲንሳ በቀይ ሽብር ውስጥ ተሳተፈ የሚባለው በፃፋቸው ደብዳቤዎች ነው።ደብዳቤዎቹ«በቀይሽብር የሚገደሉና አብዮታዊ እርምጃ የሚወሰድባቸው ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ አስክሬኖቻቸው በየሜዳው እየተጣሉ የሰው ልጅ ክብር በሚያጎድፍ መልኩ ሜዳ ላይ መጎተት ነውር ስለሆነ በቀይ ሽብር የሚገደሉ ሰዎች አስክሬን ለቤተሰባቸው ይሰጥ፤ በክብርም እንዲያርፉ ይደረግ» የሚል ነበር።ደብዳቤው በሂደቱ መሳተፉን ያሳያል፤ በሌላ መልኩ ደግሞ የሰውየውን ስብዕና ያመለክታል።ስለዚህ ተሳትፏል ግን ቀጥታ ተሳታፊ አልነበረም።ስለዚህ ቅጣቱን ማቅለል አለብን ብለን ነበር።
በደርግ ሥርዓት ማዕከላዊ ውስጥ በተፈጸመው በርካቶች ለፍርድ ቀርበው ተቀጥተዋል።ግን ይህንን ያደረገ መንግሥት ቤቱን እንኳ ሳይቀይር ድርጊቱን ቀጥሎበታል።በማዕከላዊ ውስጥ የነበሩት ቶርቸሮች፥ ግድያዎች፥ በሰብአዊ መብት ላይ የሚደረጉት ወንጀሎች ተመሳሳይ ነገር ነበር የቀጠለው።እያንዳንዳቸው መርማሪዎች ሳይቀሩ ለፍርድ ቀርበዋል።ይሄ ተደጋጋሚ የአዙሪት ክሰተት መቆም አለበት።
አዲስ ዘመን፡- እርስዎ ዳኛ በነበሩበት ጊዜ ጣልቃ ገብነት ነበር ወይ። እንዲህ አድርግ ወይም ፈጽም ብሎ ጫና ያሳደረብዎ ካለ ቢነግሩኝ?
አቶ ሰለሞን፡- አምቦ በምሰራበት ጊዜ ችግሮች ነበሩ።እኛ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ያለመርካት ነገር ነበረ። አንዳንድ ጊዜ ግልጽ አውጥቶ በአለቆቻችን በኩል መጥፎ ፊት የማሳየት ነገር ይኖራል እንጂ እንዲህ አድርግ የሚል ነገር እውነት ለመናገር ገጥሞኝ አያውቅም፣ ብባልም እንደማላደርገው አውቃለሁ።ግን ተጽእኖ ማለት ቀጥታ እንዲህ አድርግ መባል ብቻ እኮ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ በምትሰራበት ሁኔታ ውስጥ ይገለጻል፡፡ሙያዊ ሥራ ላይ ተጽእኖ አለው፣ እድገት የማግኘት ዕድልህ ሊጠብ ይችላል፣ የመፈረጅ ዕድል ሊኖር ይችላል፣ ብዙ የተለያዩ ጫናዎች ሊመጡብህ ይችላሉ። በሌሎች ሰዎች ላይ ደግሞ ጫናዎች ሲደርሱ ታየዋለህ።
ለምንድን ነው እገሌ እንዲህ የሆነው፣ እሱ እኮ ሲኒየር ሆኖ እስካሁን የተቀመው እንዲህ አድርጎ እኮ ነው የሚሉ ነገሮች ይኖራሉ።ከእዚያ አንጻር ጫናዎችና ስጋቶች የሉም ማለት አይደለም። በግልጽ የቀይ ሽብር ችሎትንም ስሰራ እንደነገርኩህ እነአበራ የማነህ አብ ላይ እኛ ዘጠኝ ዓመት ፈርደን ያለመርካት ነገር ነበረ። ጉዳዩም በዜና አልተዘገበም። የእኛ ውሳኔ ተሽሮ 25 ዓመታት ሲወሰን ግን በዜና ሰምተናል።ከእዚያ በኋላ የሚሆነው ነገር ምቾት አይሰጥም። በርግጥ እኛም ተሳስተን ሊሆን ይችላል። እኛ ፍጹም ነን ለማለትም አይደለም። የበላይ ፍርድ ቤት ሲሽረው የተሳሳትነው ነገር ሊኖር ይችላል።አንዳንድ ጊዜም ዝም ብለህ ታስባለህ። በግልጽ እንዲህ አድርግ የሚል ሳይሆን ሥነልቦናዊ ይዘት ያላቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ።አንዳንዴ ደግሞ ዳኛው ላይ ግላዊ ማንነቱ ላይም የማይታሰብ ነገር ሊያስብ ይችላል፣ ሊያስቆጣ የሚችል ነገርም ይገጥማል።ግን በግልጽ እንዲህ አድርግ ብሎ ያዘዘኝ እስከማስታውሰው ድረስ የለም።
አዲስ ዘመን፡- በአንድ አገር የዳኝነት አካል አስፈላጊነቱ ምንድን ነው?
አቶ ሰለሞን፡- የዳኝነት አካል በኅብረተሰብ እድገት ውስጥ መንግሥት የሚባለው አካል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ አብሮ የተፈጠረ፣ በዓለማችን ላይ ረጅም ታሪክ ያለው ነው፡፡ፍርድ፣ ፍትህ የሚባለውን አገልግሎት የሚሰጥ፤ ከጥንት የዓለም ሥልጣኔ ጀምሮ በእያንዳንዱ የዓለም ኅብረተሰብ እድገት ውስጥ የነበረ በተለይም ከሥነ መንግሥት ጋር ተያይዞ እያደጉ ከመጡት አስተሳሰቦችና እድገቶች ጋር በየጊዜው እየጎለበተና እያደገ የዳኝነት አገልግሎትን የሚሰጥ አካል ነው።
በዘመናዊ አስተሳሰብ መንግሥት ከተዋቀረበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥት ሥስት አካላት አሉት።እነዚህም ሕግ አውጪው፣ ሕግ አስፈፃሚ፣ ሕግ ተርጓሚ ወይም የዳኝነት አካል የሚባለው ነው።የዳኝነት አካል ሕግን በመተርጎም የዜጎች መብቶች መከበራቸውን የሚያረጋግጥ፣ ለዜጎች መብት መከበር ዋስትና የሚሰጥ፣ ጥበቃ የሚያደርግ፣ ለሕገመንግሥታዊነትና ለሕገመንግሥት መከበር ዘብ የሚቆም በመሆኑ ነው።ከዚህ አንፃር ለዜጎች ቅርብ የሆነውና በጣም ጠቃሚና ቅድሚያ የሚሰጡት ተቋም ይህንን የዳኝነት አካል ነው።
የዳኝነት አካል ዋናው ተግባሩ ሕግን በመተርጎም ለዜጎች ፍትህ መስጠት ነው።የፍትህ አገልግሎት የዜጎች መብት በሚጣስበት ጊዜ መብቴ ተጥሶብኛል የሚለው ወገን የመብቱ መጣስ እንዳይቀጥል ወይም እንዲቆምና ሌሎች መብቶቹ የሚጠበቁለት ወደዚህ አካል መጥቶ ነው።ሕግ የተላለፈ አካልም ግዴታውን እንዲወጣና የሌሎችን ሰዎች መብት እንዲያከብር ለማድረግ ቁልፍ ሚና የሚጫወተው ይሄው የዳኝነት አካል ነው። በተለይ አዲስ ዘመን ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም
ጉልበትና ኃይል አለው ተብሎ የሚታሰበው መንግሥት የዜጎችን መብት እንዳይጥስና እንዳይጎዳ ሊያስቆም የሚችለው ይህ የዳኝነት አካል ነው።በዚህ መሠረት
ደግሞ ውሳኔዎችን በመስጠት፣ ፍትህ በማረጋገጥ፣ ለሕገመንግሥቱ መከበርም ዘብ የሚቆም አካልም ነው። አሜሪካኖች ዛሬ ለደረሱበት የኢኮኖሚ እድገት፣ የሕግ የበላይነት መከበር፣ የዜጎችና የግለሰቦች መብት ጥበቃ
ሕገመንግሥታቸውን ካፀደቁበት ጊዜ ጀምሮ እያደገ ያለው ይህ የዳኝነቱ አካል ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።ስለዚህ የዳኝነቱ አካል ሰብአዊነትን ከማስከበርና ኢኮኖሚን በማበልፀግ ትልቅ ሚና አለው።በአጠቃላይ ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ስለሀገር ግንባታ ማሰብ አይቻልም።በሀገር ግንባታ ውስጥ ሕገመንግሥታዊነት፣ የሕግ የበላይነት፣ ሥርዓት ያለው የመንግሥት አወቃቀር፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ ዋስትና የሚባሉት ነገሮች ሁሉ
ያለዳኝነት አካሉ ሊታሰቡ አይችልም።ለዚህ ነው እንግዲህ የዳኝነት አካሉ ለዜጎችም ሆነ ለአንድ አገር የማይተካ ሚና የሚጫወተው የምንለው።
አዲስ ዘመን፡- በኢትዮጵያ የዳኝነት አካል አሠራር ምን ይመስላል? በተለያዩ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ የነበረውን አሠራር እያነፃፀሩ ይግለፁልኝ?
አቶ ሰለሞን፡-እንግዲህ የዳኝነት አካል በኢትዮጵያ በሥነመንግሥት ረጅም ታሪክ አለን። በተለይም ደግሞ በዘመናዊ መንግሥት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ወይም በንጉስ ኃይለሥላሴ ዘመናዊ ሕጎች በኢትዮጵያ
እንዲወጡ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ከአውሮፓ በመውሰድ ከአገር ሁኔታ ጋር እንዲዛመዱ ጥረቶች ተደርገዋል።ያንን መነሻ በማድረግ ዘመናዊ ፍርድ ቤቶችም በተወሰነ መልኩ ተደራጅተዋል።በተለይም እ.አ.አ 1955 የወጣው
ሕገመንግሥት የዘውዳዊ ሥርዓትን መነሻ ያደረገ፤ እውቅና የሰጠ ነበር። ስለዜጎች መብት፣ ስለመንግሥት አወቃቀር፣ ስለፍርድ ቤቶች ሥልጣንም፣ ዝርዝር ድንጋጌ ያለው ነው። ትንሽ ግን የመንግሥትንና የሦስቱን አካላት ሥልጣን የማደበላለቅ ነገሮች ቢኖሩም፤ ንጉሱ በሁሉም አካላት የበላይ ነው፣ የሥራአስፈፃሚውም፣ የሕግአውጪውም የበላይ ነው፤ የዙፋን ችሎት የሚባልም ነበር።የዳኝነት ሥራ ኃላፊነትም አላቸው።እነዚህ ነገሮች እንግዲህ በሥልጣን ክፍፍል ወቅት የመደበላለቅ ነገር ቢኖርም በተወሰነ መልኩ በአገራችን ዘመናዊ ሕጎች መተግበር ተጀምሮ ለዚያ ሕግ ደግሞ የውጭ ባለሙያዎችን ተቀጥረው ነው የመጀመሪያዎቹ ሕጎች እንዲወጡ የተደረጉት።እነዚያን
ሕጎች ለመተርጎም ያስችል ዘንድም የዳኝነቱ ሕጎች ብዙዎቹ የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ።ታዋቂ የውጭ ባለሙያዎችን በማምጣት የዳኝነት አካሉ ስር እንዲሰድ በጥልቅ ሁኔታ ላይ የተገነባ እንዲሆን በጎ ጅምሮች ነበሩ ተብሎ ይወሰዳል። የኢትዮጵያ የዳኝነት አካሉ ኢትዮጵያ ከምትከተላቸው የፖለቲካ መስመሮችና አካሄዶች ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው።ለዚህ ነው በደርግ ጊዜ በተለይም በኋላ ላይ አገሪቱ የተከተለችበት መስመር ግራ ዘመም የፖለቲካ አስተሳሰብ ከመሆኑ አንፃር የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የተደራጁትም የግራዘመም የፖለቲካ መስመርን ከማሳካት አንፃር ነው።አንዱ የመንግሥት አካል ሌላውን እንዲቆጣጠርና እንዲከታተል፣ ሕገመንግሥታዊነት እንዲሰፍን፣
ጥበቃ ከማድረግ አንፃር ሥራዎቻቸውን ሲያከናውኑ አልነበረም።ይህ እንደትልቅ ክፍተት ይወሰዳል፡፡
በወቅቱ ከነበረው አስተሳሰብ ጋር አብሮ የመቆራኘት ነገር ነበር።በኋላም የሥርዓት ለውጥ ከመጣና በ1987 ዓ.ም ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ ሕገመንግሥቱ በጣም የተደረጀ ነው።በተለይ ነፃ የዳኝነት አካል እንደሚደራጅ፣ የዳኝነት አካል ደግሞ የዳኝነት አገልግሎት እንደሚሰጥ እና ሰብአዊ ጥበቃዎችና ዝርዝር ድንጋጌዎች በሕገመንግሥቱ እንዲቀመጡ ተደርጓል።በዚያ መልኩ የዳኝነት አካሉ የተደራጀ በመሆኑ ሕገመንግሥቱም ዘመናዊ ሕገመንግሥት ተብሎ የሚወሰድ ነው።ዞሮ ዞሮ ሌሎች ችግሮችም አሉ።የፍርድቤትን ሥልጣን ምሉዕ ከማድረግ አንፃር የእኛ ሕገመንግሥት አሁንም ክፍተት ይታይበታል። ከእዚህ ባሻገር ሕገመንግሥቱ በጣም የተደራጀ ነው ብሎ መውሰድ
ይቻላል። ፍርድ ቤቶቹ በእውነት ለዜጎች መብት መከበር ዘብ ሆነው ሲሰሩ ነበር ወይ? የዜጎች መብቶች ጥበቃ እንዲያገኙ
የሚያደርጉ ተቋማት ነበሩ ወይ? ሕገመንግሥታዊነት እንዲጎለብት በተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ልክ
እየተንቀሳቀሱ ነበር ወይ? ቢባል በርካታ ክፍተቶች አሉባቸው።አሁን ያለንበት ሁኔታም ይህንኑ ያንፀባርቃል፡፡
አዲስ ዘመን፡- ስለኢህድሪ ሕገ መንግሥት እስቲ ትንሽ ያብራሩልን?
አቶ ሰለሞን፡- እኔ እንደተረዳሁት የኢህድሪ ሕገመንግሥት የቆየችው ከ1980 ጀምሮ ሦስት ዓመት ለማይሞላ ጊዜ ውስጥ ነው።ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ከሶቭየት ህብረት መንግሥት የተገለበጠ ነበር።ያም ሆኖ ስለዜጎች መብቶች ጥበቃ ያደርጋል። የእኛ አገር ሕገመንግሥቶች ሲቀረፁ በተቻለ መጠን ወቅቱ የሚጠይቃቸውን ዘመናዊ አስተሳሰቦች ሁሉ ያካትታሉ።ዋናው ችግር ግን እነዚያን ነገሮች ወደመሬት አውርዶ ተግባራዊ ማድረጉ ላይ ነው።ለዚህ ነው እንግዲህ በወቅቱም ስለደርግ ጊዜ ፍርድቤት በሚነገርበት ጊዜ በተወሰነ መልኩ እኔም የቀይሽብር ችሎት ላይ በምሰራበት ጊዜ ያስተዋልኩት ያለፍርድቤት ትዕዛዝ ሰዎች ይገደሉ ነበር።ዞሮ ዞሮ መሠረታዊ የሰው ልጅ መብት ሕይወት እስከሚያሳጣ ድረስ ውሳኔ ሊወስን፣ በሰውልጆች የንብረት መብትም፣ የሌሎች ነፃነትና መብቶችን ያለፍርድ ቤት ውሳኔ መንግሥት የሚባለው አካል በመንግሥትነቱ ብቻ
የሚያደርጋቸው ከሆነ ፍርድቤት የሚባለው ነገር መኖሩን አጠያያቂ ያደርገዋል።ይህ በደርግ ወቅት በስፋት የሚታይ
ክስተት ነው፡፡
አዲስ ዘመን፡- በኢህአዴግ ዘመን የዳኝነት አካሉ መጠቀሚያ ሆኗል በሚባለው ሃሳብ ይስማማሉ?
አቶ ሰለሞን፡- በአገራችን ፍርድ ቤት ላይ ሰዎች እምነት አጥተዋል ይባላል።የፍርድ ቤት እምነት ማጣት መሰረቱ በመንግሥት ላይ እምነት ማጣት ነው።አንድ ሰው በፍርድ ቤት ላይ እምነት ካጣ በአጠቃላይ በሥርዓቱ ላይ እምነት ያጣል።ያን ጊዜ ነው እንግዲህ በአጠቃላይ
በአገሪቱ ሰላም ማጣትና ያለመረጋጋት የሚሰፍነው። ከዚህ አንፃር ክፍተቶች አልነበሩበትም ወይ? ብለህ ከጠየቅከኝ
በትክክል ክፍተቶች ነበሩበት።
እምነት ያጣነው እነዚህ ፍርድቤቶች በሚሰሯቸው ተፈጥሯዊ የዳኝነት አካሉ ሚና መወጣት ባለመቻላቸው ነው።አሁንም ትኩረት ሰጥቼ መናገር የምፈልገው ሕዝብ በፍርድ ቤት ላይ እምነት አጣ ማለት በሕግ ላይ እምነት ያጣል።ይህም የመንግሥትን ቅቡልነት አደጋ ላይ
ይጥለዋል።ያን ጊዜ የመንግሥት ተፈጥሯዊ ባህሪ ሰዎች በሰላም ወጥተው በሰላም መግባት የሚችሉበት ሁኔታ አደጋ ላይ ይጥላል።አጠቃላይ ቀውሶችም ይፈጠራሉ፡፡ ይህ የሚታወቅና የኖርንበትም ነው።ከዚህ አንፃር እንግዲህ ፍርድ ቤቶች ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ማለት አይቻልም።ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ስለሕጋዊነት፣ ስለሕግ የበላይነት፣ ስለሀገር ግንባታ፣ ስለሕገመንግሥታዊነት፣ስለሕግ የበላይነት መናገር አይቻልም። ባለፉት 27 ዓመታትም የተፈጠረው ክፍተት ይሄ ነበር።
አዲስ ዘመን፡- የዳኞች ሥራ ይመዘናል ብለው ያምናሉ?
አቶ ሰለሞን፡- የዳኝነት ሥራ አይመዘንም የሚሉ በርካታ ሰዎች አሉ።የዳኝነት ምዘናን ከዳኝነት ነፃነት እና
ጣልቃ ገብነት ጋርም የሚያያይዙ አሉ።በበርካታ አገሮችም አልዳበረም።በምዘና ሰበብ ሥራን እንዲህ አልሰራህም በሚል በሥራዬ ውስጥ ጣልቃ ገብነትና ጫና መፍጠሪያ ነው ብለው የሚወስዱም ዳኞች አሉ።በሌላ በኩል ደግሞ አሁን እየጎለበተ የመጣው ዳኝነት ማለት ሙያዊ አገልግሎት (professionalism) ነው።የሙያ አገልግሎት ደግሞ በሙያ መሠረት መሰራቱና አለመሰራቱ መመዘን
አለበት።ሙያው የሚጠይቀውን እውቀት መነሻ በማድረግ ሊሰራ የሚችል በመሆኑ በአግባቡ መተግበሩ መታየት
አለበት ብለው የተለያዩ አገራት የምዘና ሥራ ተግብረዋል።
ለእዚህ ነው እኛም ሌላ ነገር እንዳያስነሳ በሚል ዓለምአቀፍ ልምድ ያለው አሜሪካዊ ዜጋን ቀጥረን በተለያዩ አገሮች ልምድ መነሻነት ሥራው ከጥራት አንጻር እንዴት እንደሚመዘን የሰራነው። የዳኝነት ነፃነትንም በማይጋፋ የዳኛውን የመወሰንና የመተርጎም ሚናውን በማይነካና መንገድ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ ጥረት እየተደረገነው።ዳኞች አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጓል።ተግባራዊ ሲደረግም በተሻለ መንገድ በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ የተወሰነ ለውጥ እናመጣለን የሚል እምነት አለኝ፡፡
አዲስ ዘመን፡- የዳኝነት አካሉን ነፃ ለማድረግ
ምን እየሰራችሁ ነው?
አቶ ሰለሞን፡- ተጨማሪ አዳዲስ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት እንዲመጡ አድርገናል።የሕግ ማሻሻያ ለውጦችንም ለማካሄድ ሁለት ሕጎች ላይ ዝርዝር ጥናቶች አድርገን ረቂቅ ሕጎችን ለምክር ቤት ልከናል፡፡ የአሠራር ሥርዓቶችን ለማዘጋጀት በውጭ ባለሙያዎች ጥናቶች ተሰርተዋል።የዳኞች ሥነምግባር ኮድ ኦፍ ኮንታክት እንደአዲስ ተጠንቷል።የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ማለትም ጉዳዮች ፍርድ ቤቶች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁበት ድረስ እንዴት መመራት እንዳለባቸው የሚገልጽ የጊዜ መለኪያዎችን አዘጋጅተናል፡፡
የፍርድ ቤቶች መርህ አስማሚነትን ተግባራዊ ለማድረግ ጥናቶች ተደርገዋል።ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ጉዳዮችን ለመቀነስ ፍርድ ቤቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ የድርድር ማዕከላትን በየፍርድ ቤቶች አደራጅተን በአዲሱ ሕግ ውስጥ አካተናል።የንግድ ችሎቶችን በሚመለከት አሠራሮችን ለማሻሻል የሚያስችል ጥናት ተካሂዷል።
አዲስ ዘመን፡- የፍርድ ቤቶች እንደገና ማሻሻያ አዋጆች ማለትም፤ የዳኝነት አስተዳደር አዋጅና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማደራጃ አዋጅ ምን አዳዲስ ነገሮች ይዘዋል?
አቶ ሰለሞን፡- በተቻለ መጠን ማሻሻያዎቹ ያደጉ አገራትን ልምድ አምጥቶ መገልበጥ ሳይሆን ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እንዲዛመዱ የተደረጉ ናቸው።ፍርድ ቤቶቻችን ሊለውጡ ይችላሉ ብለን የምናስባቸውን አዳዲስ አሠራሮችንና አስተሳሰቦችን በሕግ ማሻሻዎቹ ላይ አካትተናል።ለምሳሌ የዳኝነት ነፃነት ትልቁ ችግራችን ነው ብለን አንስተናል።የዳኝነት ነፃነትን ለማረጋገጥ ምን መደረግ እንዳለበት፣ እንዴት ቢደራጅ የተሻለ እንደሚሆን፣ የዳኛውን ግላዊ ነፃነትንም የዳኝነት አካሉን ተቋማዊ ነፃነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችና የሕግ ጥበቃዎች ዝርዝር ድንጋጌዎችን አስ ቀምጠናል። አካላዊ የዳኛውን ግላዊ ነፃነት፣ የዳኝነት አካሉን ተቋማዊ ነፃነት፣የበጀት ችግር ለመመልከት ተችሏል።ዳኝነት ሥራ ነው።አገልግሎት በእቅድ የሚሰራ እንደመሆኑ የሚለካውም በአቅም ልክ ነው። ሀብት ሳታፈስ አንድን ነገር መጠበቅ አትችልም።እንዲህ ዓይነት መሠረታዊ ችግሮች አሉ።ሲታቀድ ቅልጥፍናን ውጤታማነትን እንዲህ አደርጋለሁ፣ ምቹ የሥራ ሁኔታን እፈጥራለሁ ተብሎ ይታቀዳል።እነዚህ ሀብት የሚጠይቁ ከሆነ መጀመሪያውኑ መሞከርም መታሰብም የለበትም። ከበጀት ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለመደው ነገር በጀቱ በፓርላማ ይጸድቃል።በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም ይሄ ነገር አለ።ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ አቅርበን በፓርላማ አጸድቀናል።ለገንዘብ ሚኒስቴር በጀታችንን አልላክንም።በሕጉም ዝርዝር ነገር ነው ያስቀመጥነው እንጂ ዋናው ነገር በሕገ መንግሥቱ ተቀምጧል።በቀጥታ ሕገ መንግሥቱ ለምክር ቤት አቅርበን የበጀት ጥያቄያችንን እንደምናጸድቅ ይደንግጋል።ባለፈው ዓመት እኛ ወደ ኃላፊነት እንደመጣን ያደረግነው ይህንን ነው። በጀታችንን በቀጥታ ለምክር ቤት አቅርበን አጸድቀናል።ይሄ ባለፉት 27 ዓመታት ከተሰራው ውስጥ አንዱ ነው።የበጀት ዕቅድ ላኩ ሲሉም አንልክም ብለን ጫና ፈጥረን ነው ወደ ምክር ቤት የሄድነው። በማሻሻያው ያካተትነው ሌላው ነገር በጀትን የሚመለከት ነው።ሌሎች አገሮች በጀት ሲመደብላቸው መስፈርት አላቸው።እኛ የሚመደብልን በጀት አገሪቱ ከምትመድበው በጀት ዜሮ ነጥብ ሦስት (0.3) በመቶ ነው።በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰሩ ጥናቶችን እንዳየነው ለፍርድ ቤቶች የሚመድቡት እስከ ሦስት በመቶ አጠቃላይ የአገሪቱ በጀት ይደርሳል።በቂ ሀብትና በጀት ሳትመድብ ስለ ሕግ የበላይነት፣ ስለሕገ-መንግሥታዊነት፣ ስለፍትህ ማረጋገጥ ማሰብ አይቻልም።መንግሥትም ግዴታውን አልተወጣም ማለት ነው።መንግሥት በግብር ከፋዩ ገንዘብ ዜጋው ይህንን አገልግሎት እንዲያገኝ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት ፍርድ ቤቱ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣና ተልዕኮውን ማሳካት እንዲችል ለማድረግ ትግበራውን ማከናወን የሚያስችል በጀት መመደብ አለበት።እኛ እየጠየቅን ያለነው የአሜሪካው ዓይነት ፍርድ ቤት አይደለም።አገሪቱ አቅም የላትም።የምንጠይቀው ግን የአገሪቱ ኢኮኖሚ ካመነጨው ፍትሃዊና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በጀት ለፍርድ ቤቱ እንዲመደብ ነው።
በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሠረት ከአጠቃላይ የአገሪቱ በጀት እስከ ሦስት በመቶ ይሄዳል።ይሄ ቀርቶ አንድ፣ አንድ ነጥብ አምስትና ሁለት በመቶ ቢመደብልን ፍርድ ቤትን መለወጥ እንችላለን።በጀት መመደብ ብቻ ሳይሆን ሌላ አገር የሚደረገው (Consolidated judiciary
Fund) ጥቅል በጀት ከተመደበ በኋላ ራሳቸው የፍትህ አካላቱ ይወስናሉ።ግን ሥራ ላይ ስለመዋሉ በመንግሥት ኦዲት ይደረጋል።ከተያዘው በጀት ርዕስ መውጣት አይቻልም።ይህንንም የሚቆጣጠረው የገንዘብ ሚኒስቴር ነው።ይሄ ዓለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ አይደለም። መንግሥት የግብር ከፋዩን ገንዘብ የመመደብ ግዴታ አለበት።ከፍርድ ቤቶች ከዳኝነት የሚሰበሰቡ ገቢዎች አሉ።ሌሎች አገራት ይህንን ገቢ ለመንግሥት ገቢ አያደርጉም።ያደጉት አገራትም በሕገ መንግሥቶቻቸው ላይ ያስቀምጣሉ። ለምሳሌ የጋናን ሕገ መንግሥት ብንመለከት «ከ .ር . ቤ . የ .ሰ .ሰ .ውገ .ዘ . የ .ር .
ቤ . አ .ቃ .ይየ .ጀ . አ .ልይ .ና .» ይ .ል .ይ .ን .
ዝ .ዝ . ድ .ጋ . አ .ር .ንለ .ክ . ቤ . ከ .ላ . በ .ላ ይ .ድ .ልብ .ንእ .ስ .ለ .፡ .
የ .ዳ .ችፍ .ትአ .ተ .ደ .ንበ .መ .ከ . ጉ .ዮ .
ከ .ጀ .ሩ .ትአ .ስ . እ .ከ .ጠ .ቀ . ድ .ስበ .ዜ መ .ዘ . ከ .ፍ . ለ .ስ .መ . የ .ያ .ች . ሕ .ዊጥ .ት አ .ጠ .ተ .ል .፡ .ን . የ .ደ .ፍሕ .ዊእ .ቅ . እ .ዲ .ረ .
አ .ራ .ንየ .ያ .ልየ .ዳ .ችመ .ገ . አ .ያ . አ .ራ .
ይ .ና .። .ሕ .ች . የ .ለ .ደ . ክ . የ .ቀ .ብ .ት . መ .ስ የ .ቀ .ብ .ት . ማ .ረ . የ .ቀ .ብ .ትበ .ሑ . መ .ኑ .
ነ .። .ሁ . በ .ክ .ሎ . የ .ደ .ፈአ .ራ . ብ .ጀ .ርሕ .ዊ መ .ረ . የ .ን .፡ .ቀ .ልየ .ነየ .ዝ .ብአ .ያ . ሥ .ዓ .
ፍ .ድቤ . ይ .ረ .ል . ዝ .ዝ .ንደ .ሞጠ .ላ . ፍ .ድቤ .
ያ .ጣ . የ .ልድ .ጋ . አ .ጥ .ንበ .ዚ . የ .ግማ .ቀ .አ .ት .ና .። ይ . የ .ጠ .መ . ብ . ፍ .ድቤ .ችክ .ን በ .ረ .ትፎ .ምብ . ሳ .ሆ . በ .ስ .ምላ . ማ .ቀ .ጥ__
ጀምረዋል።ክስ፣ የምስክሮች ቃል፣ መልስ፣ የሰነድ ማስረጃዎች ኮምፒዩተር ላይ የሚቀመጡበት ሥርዓት ተዘርግቷል።ዳኞች የሚሰጡት ትእዛዞች፣ ውሳኔዎች ጭምር ይቀመጣሉ።የጊዜ መመዘኛ ከተቀመጠ የትኛው ጉዳይ በምን ያህል ጊዜ እንዳለቀ፣ ከአንድ ፍርድ ቤት ወደሌላው ፍርድ ቤት ምልልሱ በሶፍት ኮፒ ለማድረግ፣ ዳኞች ወረቀት አንብበው አንዱ ለሌላው የማስረዳት ሳይሆን እያንዳንዱ ዳኛ በሲስተም ያለውን በመመልከት ለውይይት ብቻ እንዲገናኙ ለማድረግ ታስቧል።ይህ የዳኛውን ሥራ በጣም ያቀላጥፋል።ግን ለእዚህ የሕግ ማዕቀፍ የለንም።በአዲሱ አዋጃችን ይህንንም አስገብተናል።
ዳኝነት የሙያ አገልግሎት ነው።የዳኞች እጥረትም ይኖራል።ሌሎች አገሮች ሥራዎች የሚሰሩት በቋሚ ዳኞች ብቻ አይደለም።ጊዜያዊ ዳኞች ከቀድሞ ዳኞች፣ ከጠበቆች፣ ከዐቃቤ ሕጎች መካከል ይቀጥሩና ለስድስት ወራት፣ ለአንድ ዓመት እንዲሰሩ አድርገው ያንን ችግሮቻቸውን ይፈቱበታል።ልዩ እውቀት ያላቸውን ሰዎችም አስገብቶ የመጠቀም ሁኔታ የተለመደ ነው።እውቀት፣ ሙያና ችሎታ ያለውን ሰው በማንኛውም ጊዜ መጠቀም የሚቻልበት ሁኔታ መዘርጋት ያስፈልጋል።ሹመት ቢያስፈልግም ለስድስት ወራትና ለአንድ ዓመት ማድረግ ይቻላል።ኃላፊነቱንም እንዲወስዱ ይደረጋል።በሰፊው ብዙ አገራት እየሰሩበት ነው።እንደአዲስ በሕጉ ውስጥ ካካተትናቸው ያልተለመዱ አሠራሮችም ውስጥ ይሄ አንዱ ነው።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሾማል ይላል።ሲነሱ እንዴት እንደሚነሱ ሕጋዊ አሠራር አልተቀመጠም።በሌሎች አገሮች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ላይ የሚታዩት ትላልቅ አገራዊ ጉዳዮች ናቸው።በእኛም ሀገር ከትግራይ፣ ከጎንደር፣ ከቦረናም፣ ከአሶሳም ከጅግጅጋም ይመጣል።ዜጎች ወደ ሙግት በሚገቡበት ጊዜ ያዋጣኛል፤ አያዋጣኝም የሚል ስሌት ሰርተው አይደለም።ይህ የዜጎችን እንግልት ፈጥሯል፣ ፍርድ ቤቶች ላይም ጫና አሳድሯል።ጠቅላይ ፍርድ ቤትም መስራት ያለበትን የአገሪቱን የሕግ ሥርዓት የመምራትና ማሻሻል ቢሆንም እስካሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በትናንሽ ጉዳዮች የመዋጥ ሁኔታ ይታያል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላይ ወደ 50 ገደማ ዳኞች አሉን።ይሁን እንጂ አሁንም የዳኛ እጥረት አለን።በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለ300 ምናምን ሚሊዮን ሕዝብ ያሉት ዘጠኝ ዳኞች ሲሆኑ፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሥልጣንን አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ በመገደባቸው ባሉት ውስን ዳኞች ተግባራቸውን መወጣት ችለዋል።አሁንም ወደታች ያለውን ፍርድ ቤት አጠናክረን አብዛኛው ሥራ እዚያ እንዲሰራ እያደረግን ነው።የሰበር ሥልጣንንም የመፈተሸ ሥራዎች በአዲሱ አዋጅ ተሰርቷል።ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዲሆን ጉዳዮች በአብዛኛው ወደ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እንዲወርዱ እንዲሁም የወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዮችንም ሥልጣን ወደ ታች እንዲወርዱ ለማስቻል ሥራዎች ሰርተናል።
ሌላው ድጋፍ ሰጪ ሠራተኛውን የሚመለከት ነው።እነዚህ የአስተዳደር ሠራተኞች ደጋፊዎች አይደሉም።እነዚህ ሠራተኞች የዳኝነቱ አካል ናቸው።ቀደም ሲል የአስተዳደር አካሉ በሲቪል ሰርቪስ ይተዳደር ነበር።ብዙ ጊዜ በፍርድ ቤቱ ስር ነው የሚሆነው።ይህን ሕጋዊ ማዕቀፍ ሊቀይር በሚችል መልኩ ሕጉ ውስጥ ከትተናል።የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የአባላትን ስብጥር አብዛኞቹ ዳኞች እንዲሆኑ የሚያስችል ለማድረግ ታቅዷል።በዳኞች ጉዳይ ዳኛው እንዲወስን የቀድሞ አወቃቀርን የሚቀይር ድንጋጌ ከትተናል።ዝርዝር በርካታ አዳዲስ ነገሮች ተካትተዋል።በቀጣይነት በምክር ቤት ውይይት ይደረግበታል።
አዲስ ዘመን፡- አንዳንዶች የዳኝነት አካሉ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተጽእኖ ስር መውደቁን ያነሳሉ።ከዐቃቤ ሕግ ጋር በምትሰሩት ሥራ ላይ ምን ያህል ጥንቃቄ ታደርጋላችሁ?
አቶ ሰለሞን፡- ወደኃላፊነቱ እንደመጣን ሰሞን ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረግነው ውይይት ፍርድ ቤት በመንግሥት ተጽእኖ ስር ወድቋል፣ በወንጀል ወይም በፍትሐብሔር ጉዳይ መንግሥት ተከራካሪ ሆኖ ሲቀርብ ሁልጊዜ እረቺ ይሆናል እንጂ አይረታም፣ በእዚህም ሰው ተስፋ ቆርጧል የሚሉ አስተያየቶች በተደጋጋሚ ይነሱ ነበር።በተለይም በጣም ወሳኝ በሆኑ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ነው የሚያነሱት። በእዚህ ጉዳይ ላይ እኛም የተገነዘብናቸው የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ።ከዳኞች ጋርም በግልፅ ውይይት አድርገንባቸዋል።ከጊዜ ቀጠሮ መዝገብ፣ ከፍተኛ የመንግሥት ከሆኑ ጉዳዮች ጋር፣ ዳኞች ምስክር የሚሰሙበት፣ ማስረጃ ከመመዘን አንጻርና ከመሳሰሉት ለመንግሥት የሚያደሉ አሠራሮች እንደነበሩ በአስተያየት ይነሳ ነበር፡፡
አንድ ሰው መለቀቅ ካለበት መለቀቅ ይኖርበታል፣ መቀጣት ካለበትም መቀጣት አለበት።መለቀቅ ያለበትን ሰው ከቀጣ ተጠያቂነትን ያስከትላል፣ መቀጣት ያለበትን ደግሞ አላግባብ ከለቀቀ ተጠያቂነትን ያስከትላል።የእኛ የተጠያቂነት ደረጃ በዳኝነት ማህበረሰብ በተለይ በወንጀል ተከስሶ የተቀጣ ሰው አላግባብ ነው የተቀጣሁት ብሎ በዳኛ ላይ ተጠያቂነትን የማስከተል አሠራር አልተለመደም።ብዙ ጊዜ ተጠያቂነትን ሊያስከትል የሚችለው መንግሥት ነው በማለት ለምን ተለቀቀ ብሎ አተኩሮ መስራት ላይ እንጂ በዋስትና መለቀቅ ያለበትን ሰው ዋስትና ከከለከለ ብዙም ተጠያቂነት አልነበረም።ተጠያቂነት በሁለቱም ተከራካሪዎች መካከል ሚዛናዊ መሆን አለበት።ይሄንን ለማስገንዘብ ውይይት ተደርጓል።በተቻለ መጠንም ይህ አስተሳሰብ ፍርድ ቤቱን አደጋ ላይ እንደጣለ ተገንዝበናል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሐግ ቁልፍ ባለድርሻ አካላችን ነው። የማይካድ ሃቅ ነው።አብረው በሚያሰሩን ጉዳዮች ላይ በጋራ እንሰራለን።ምክንያቱም የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነት በፍርድ ቤት ላይ የሚለካው ፖሊስ፣ ዐቃቤ ሕግ ውጤታማ ሲሆኑ ነው።የፍርድ ቤቱም የዳኝነት አገልግሎቱም ውጤታማ ሊሆን የሚችለው እነዚህ አካላት ጠንካራ ሲሆኑ ነው።እዚያ አካባቢ ላይ ውጤታማነት ከሌለ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በፍርድ ቤት የዳኝነት አገልግሎት ተጽእኖ ይኖረዋል።ስለዚህ ግልጽ በሆኑ በጋራ ጉዳዮች አብረን እንሰራለን።
ያ ማለት ግን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መንግሥትን ወክሎ የሚከራከር ሲሆን ከሌሎች ተከራካሪዎች እኩል ሕግና ማስረጃ በመመዘን የዳኝነት አገልግሎት መሰጠት የለበትም ማለት አይደለም።ይህንን ለማስተካከል በርካታ ርቀቶችን ተጉዘናል።ይህንን የኅብረተሰቡን አስተሳሰብ ሊቀይር በሚችል መልኩ ከአቀራረብ ጀምሮ ለመለወጥ እየተሰራ ነው።ችግር የለም ማለት አይደለም።«አንዳንድ ጊዜ ችሎት ሥነሥርዓት ላይ የቱ አቃቤ ሕግ ነው የቱ ዳኛ ነው ብለን መለየት በሚያቅተን ደረጃ ላይ ደርሰናል» የሚሉ ስሞታዎች ይነሳሉ።አቃቤ ሕጎች ዳኞች ሲሰየሙ ተከራካሪ ወገኖችም ሆኑ ሌሎች ከወንበራቸው ሲነሱ አብረው መነሳት ግዴታ አለባቸው።ምክንያቱም መንግሥትም እንደአንድ ተከራካሪ ሆኖ ከሌሎቹ እኩል ስለሚቀርብ ነው።ግን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያዝ የሚያደርጉ ሰዎች እዚህም እዚያም አሉ።መስተካከል አለባቸው ብለን ከዳኞች ጋር በየጊዜው ውይይት እናደርጋለን።ከዐቅም በላይ ነገር ካጋጠማቸው ሕጋዊ እርምጃ ወይም የማስተካከያ ርምጃ እንዲወስዱ እንነግራቸዋለን።ይህንን እኛም ትልቅ ችግራችን ነው ብለን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እንዲህ ዓይነት ነገሮች እንዲስተካከሉ ጥረት እያደረግን ነው።ያ ማለት በዐቃቤ ሕግ ተጽእኖ ስር ሆኖ ሳይሆን ከእይታ ብንመለከት ችሎት ላይ ዳኛው ሲናገር ሌላው ተከራካሪ ቆሞ እያወራ ዐቃቤ ሕግ ተቀምጦ የሚናገር ከሆነ ዓቃቤ ሕጉ ዳኛውን እያዘዘው ነው ብሎ ሊያስቡ ይችላሉ።እንዲህ ዓይነት ነገሮች እንዳይኖሩ ለወደፊቱም እየጠራ እንዲሄድ እንፈልጋለን።እንደምናደርገውም ተስፋ አለኝ፡፡
አዲስ ዘመን፡- የዳኝነት አካሉን እያወኩ ያሉ ችግሮች ምንድን ናቸው?
አቶ ሰለሞን፡- አሁን በጀት ትልቁ ችግራችን ነው።የማስቻያ ቦታዎች እጥረት፣ የምንገለገልባቸው በቂ ሕንፃዎችና ምቹ የመስሪያ ቦታዎች አለመኖራቸው በዋናነት ይጠቀሳሉ። እንደአገር ታዳጊ ነን።ግን ከድህነታችንም ላይ ቆንጥረንም ቢሆን ለተቋሙ የሚገባውን በማድረግ በኩል ችግር እየገጠመን ነው።የአሠራር ሥርዓቶች እየዘረጋን፣ የሕግ ማሻሻያዎች እያደረግን እንገኛለን።በዘላቂነት ብዙ ነገር ያስፈልጉናል ብለን እናስባለን።የፍርድ ቤት ነፃነት ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤት ነገሮችን ሊሰራ የሚያስችልበት ሥልጣንም ሊኖረው ይገባል።ሕገ መንግሥታዊነት እንዲሰፍን የሚያደርግ፣ በመንግሥት አካላት መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ያንን ሊፈታ የሚያስችል መሆን አለበት።
በፌዴራል መንግሥታት አስተዳደር ውስጥ እንደመገኘታችን በፌዴራልና በክልሎች መካከል አለመግባባቶችን፣ ግጭቶች፣ አንዱ ሌላው ሥልጣኔ ውስጥ ገብቷል የሚሉትን ለመቅረፍ የሕገ መንግሥትና የሕግ ነፃነት እንዲጎናጸፍ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ የፍርድ ቤት ሥራው ምሉዕ አይሆንም። ካልሆነ ደግሞ ተአማኒነት ይጎድላል፣ መንግሥት ላይም እምነት ይታጣል። አሁንም እዚህና እዚያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከመቅረፍ አንጻርም ፍርድ ቤቶች ሚናቸውን ሊጫወቱ የሚያስችል ሥልጣን ሊኖራቸው ይገባል።
እዚያ አካባቢ ያሉትን ችግሮች መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ያለጠንካራ ፍርድ ቤት ዴሞክራሲን፣ ሕገ- መንግሥታዊነትን፣ የዜጎች መብት ጥበቃን፣ ዘላቂ ሰላም፣ ተከታታይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት፣ መረጋጋት ሊታሰብ አይችልም።መንግሥትና ኅብረተሰቡም መገንዘብ ይገባቸዋል።በተለመደው አካሄድ አገርን እንገነባለን፣ ዘላቂ ሰላም እናመጣለን፣ ሕገ-መንግሥታዊነት እንዲጎለብት እናደርጋለን የሚለው አያስኬድም።ዴሞክራሲን እናሰፍናለን፣ የሕግ የበላይነትን እናረጋግጣለን ብሎ ማሰብም አይቻልም።በፍርድ ቤት ላይ አለመተማመን አጠቃላይ አገዛዙ ላይ እምነት ማጣት ነው።ይህ እንደ አንድ ተግዳሮት ይታያል።በአገር ግንባታ ላይም ተጽእኖ ያስከትላል።በመሆኑም ሁሉም በጋራ መረባረብ ይገባዋል።ኃላፊነቱ የፍርድ ቤት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው።ስለዚህ ማህበረሰቡም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል።መንግሥትም ቁርጠኛ መሆን አለበት።
አዲስ ዘመን፡- ለሰጡን ቃለ ምልልስ በዝጅግት ክፍሉ ስም አመሰግናለሁ!
አቶ ሰለሞን፡-እኔም ለተሰጠኝ ዕድል አመሰግናለሁ!
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥር 9/2012
ዘላለም ግዛው