ጤናማ ሕፃን ያለችግር መተንፈስ ይችላል። ሕፃኑ ጡት በየ2 እስከ 4 ሰዓት መጥባት አለበት እና ሲርበው ወይንም ጨርቁን ሲያረጥብ በራሱ መነሳት መቻል አለበት። የተወለደ ሕፃን ቆዳው ንጹህ ወይንም ትንሽ ቅላት ወይንም ከትንሽ ቀን በኋላ የሚጠፋ መንደብደብ ሊኖረው ይችላል። እነዚህን ምልክቶች ካልታዩ ቶሎ ሕፃኑ እርዳታ ያስፈ ልገዋል።
ኢንፌክሽን
ለተወለደ ሕፃን ኢንፌክሽን አደገኛ ስለሆነ ወድያውኑ በአንቲባ ዮቲክ (antibiotics) መታከም አለበት። አካባቢያችሁ የጤና ጣቢያ ካለ እዚያ ቶሎ መሄድ። ካለዚያ የጤና ጣቢያውን ርቀት እና ያላችሁን መድኃኒት በማመዛዘን ቶሎ ዕርዳታ ማግኘት ወይንም መድኃኒት እናንተው መስጠት ምንም እንኳን በመንገድ እርዳታ ለማግኘት እየሄዳችሁም ቢሆን ያስፈልጋል።
እትብት
እትብቱ ከተቆረጠ በኋላ የቀረውን ትርፍ እትብት አትነካኩት ወይንም አትሸፍኑ። የሽንት ጨርቅ እና ዳይፐር እንዳይነካው። የግድ መንካት ካስፈለገ እጅን በሳሙና እና በውሃ መታጠብ የግድ ነው። እንብርቱ ወይንም አካባቢው ከቆሸሸ ወይንም የደረቀ ደም ካለ በሳሙና እና በውሃ በንጹሕ ጨርቅ መፀዳት አለበት። እናት እንብርቱን ከሸፈነች ሳይጠብቅ በንጹሕ ጨርቅ መሆን ይገባዋል። ጨርቁን በቀን ውስጥ በተጋጋሚ መቀየር ያስፈልጋል። ከአንድ ሳምንት በኋላ እትብቱ ደርቆ ይወድቃል። እትብት አካባቢው ቀይ ከሆነ፣ እና ኢንፌክሽን ከያዘ አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ሊያገኝ ይገባዋል።
ምንጭ፡–www.am.hesperian.org
አዲስ ዘመን ሐምሌ 27/2011