ቅዳሜ መስከረም 16 ቀን 1946 ዓ.ም የወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስራ ሶስተኛ አመት ቁጥር 23 እትም “አንድ ሬሳ በ5 ሚሊዮን ብር” በሚል ርዕስ ከውጭ አገር የተገኘ አስገራሚ ጉዳይን አስነብቦ ነበር፡፡
አንድ ሬሳ በ 5 ሚሊዮን ብር
በብራዚል ዋና ከተማ በሪዮዴጂኔይሮ የሚኖር ኮርዴይሮ ዴኖርማንዴስ የተባለ የ51 ዓመት ሰው በ200 አይነት ልዩ ልዩ በሽታ ስለተለከፈ ከነገ ዛሬ ይሞታል እየተባለ ይጠበቃል። ቢሆንም የዚህን ህመም ብዛት ሀኪሞች ካወቁት በኋላ የተለከፈበትን አይነተኛ ሁኔታ ለማወቅ ከሞተ በኋላ ሬሳውን በግዥ ወስደው ለመመርመር ይጠባበቁታል፡፡ ህመምተኛውን ግን ገና በህይወቱ ሳለ በ200 አይነት ህመም የተለከፍህበትን በሽታ ለመመርመር እንዲመቸን ሬሳህን ዘመዶችህ እንዲሸጡልን ተናዘዝ ቢባል፡፡ 5 ሚሊዮን ብር ጠይቋል፡፡
ዋናው የዓለም ጤና አጠባበቅ የህክምና ማህበር ይህንን የኮርዴይሮ ዴኖርማንዴስ /Cordeiro de Normandes/ን በድን ለመመርመር በህክምና ዘዴ በኩል በጣም የታወቁትን ሊቃውንቶች በማሰባሰብ 5 ሚሊዮን ብር ከፍለው ከሞተ በኋላ ሬሳው እንዲሰጣቸውና የሁለቱንም መቶ በሽታዎች እንዲመረምሩ ተስማምቷል፡፡
ከኢን ኮም የተገኘ
ሞ ’ ክፍሌ
******
ቅዳሜ ሚያዝያ 22 ቀን 1945 ዓ.ም የወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስራ ሶስተኛ አመት ቁጥር 4 እትም “የከተማ ውስጥ ወሬ” በሚል አምድ ስር የተለያዩ ወሬዎችን አስነብቧል፡፡
በጥይት ተመትቶ ቆስሎ ስለተያዘ ሌባ
ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘ፡፡
ሚያዝያ 19 ቀን 1945 ዓ.ም የ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ባልደረቦች ፖሊሶች በደጃዝማች ባልቻ ሰፈር የደፈጣ ስራ ሲሰሩ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን ወልደዮሐንስ ክብረት የተባለ ሌባ ሁለት የውሃ ቧንቧ ሰርቆ ተሸክሞ ሲሄድ እንዲቆም ቢጠይቁት ለማምለጥ ሲሞክር ግራ እጁን በጥይት አቁስለው ከያዙት በኋላ ወደ ሀኪም ቤት ተልኳል፡፡
ከአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘ
የብስክሌት አደጋ
ሚያዝያ 14 ቀን 1945 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ሲሆን ወደ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚወስደው መንገድ ውብሸት ተክሌ በብስክሌት ገጭቶ ጥሎ አቆሰለኝ ብላ ባዩሽ አበራ ስላመለከተች ሐኪም ቤት ተልካ ተከሳሹ ታስሯል፡፡
በጥይት ተመትቶ ስለተያዘ ሌባ
ከ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘ
ሚያዝያ 15 ቀን ሌሊት ከደጃዝማች ባልቻ ሰፈር ፖሊሶች የደፈጣ ስራ ሲሰሩ አንድ ሌባ ሳንቃ ተሸክሞ ሲሄድ ቁም ቢሉት ለማምለጥ ሲሞክር በጥይት ከታፋው ላይ መትተው አቁስለው ስለያዙት ወደ ሐኪም ቤት ተልኳል፡፡
******
ቅዳሜ መጋቢት 22 ቀን 1948 ዓ.ም የወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስራ አምስተኛ አመት ቁጥር 50 እትም “በሽተኛው ሞተ እንዴ ? “ በሚል አንድ አንባቢ የላኩትን ጽሑፍ አስነብቦ ነበር፡፡
አዲስ ዘመን ረቡዕ ሐምሌ 24/2011