
ሐዋሳ:- ሐምሌ 18 ቀን 2011 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህ ዴን) አመራሮችን ከኃላፊነትና ከድርጅት ማገዱን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግበዋል ፡፡
ንቅናቄው ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳስ ታወቀው፤ ካገዳቸው መካከል የሐዋሳ ከተማና የሲዳማ ዞን አመራሮች ይገኙበታል። አመራሮቹ የታገዱት ሰሞኑን በከተማውና በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተው ግጭት ሚና ነበራቸው በሚል ነው።
በተጨማሪ የሐድያ ዞን አመራሮች በዞኑ የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ በመጣ ላቸው እገዳ እንደተደረገባቸው ተገልጿል። በከፋና በወላይታ ዞኖች የተስተዋሉት ተመሳሳይ ደርጊቶችም የሕግ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትሉ ድርጅቱ ጠቁሟል ።
ድርጅቱ ከመንግሥት ኃላፊነትና ከድርጅት ያገዳቸው የሲዳማና የሐድያ ዞን ባለስልጣናት ‹‹ የፊት አመራሮች ›› ናቸው ከማለት ውጪ ቁጥራቸውንና ስማቸውን አልገለጸም፡፡
ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በመግለጫው በክልሉ የሚነሱትን የክልልነት ጥያቄ የሚመ ለስበት አግባብ ላይ ግልጽ አቅጣጫ በድርጅቱ ጉባዔ መቀመጡን አስታውሶ፥ ይሁን እንጂ ከድርጅት አቅጣጫና ከመንግሥት ውሳኔ በተቃ ራኒ የተፈጸሙ ኢ-ህገ መንግሥታዊ ድርጊት እና ይህንን ተከትሎ በሲዳማ ዞን በሰው ህይወት፣ አካል እና ስነ ልቦና እንዲሁም በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እጅግ አሳዛኝ እና ኢ ሰብአዊ በመሆኑ በጽኑ አውግዟል።
የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ዜጎች መጽናናትን የተመ ኘው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው፤ በጥቃቱ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በአስቸኳይ እንዲ ሰራም ወስኗል። ከዚህ ጎን ለጎንም በጥፋቱ የተሳተፉ እንዲሁም ያስተባበሩ እና የመሩ አካላትን ከህዝቡ ጋር በመተባበርና በመለየት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩት ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ለፍጻሜ እንዲደርሱ በጥብቅ እንደሚሰራም አስታውቋል።
በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ያሉ የሥርዓተ አልበኝነት አዝማሚያዎች በክልሉ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ያደረጉ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆሙና የህግ የበላይነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቋም መወሰዱን በመግለጫው ተመልክቷል።
በዚህም የተነሳ በአካባቢው የሚታዩ የሥርዓተ አልበኝነት በህዝብ ጥያቄ ሽፋን ህገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ለመናድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሙሉ የክልሉን ህዝቦች ደህንነት ስጋት ላይ የጣሉ በመሆናቸው በመደበኛው የፀጥታ ሥራ መቆጣጠር ወደማያስችልበት ደረጃ በመድረሱ የፀጥታው ሥራ በፌዴራል ኮማንድ ፖስት እንዲመራ መደረጉንም አስታውቋል።
በክልሉ የሚከሰቱ ችግሮች በዋናነት ከአመራር ስርዓቱ ጋር የተያያዙ መሆኑን አስቀድሞ መገምገሙን በማስታወስ፤ አሁንም ለተፈጠረው ችግር የአመራር ሚና የጎላ መሆኑን ተመልክቷል። በቀጣይም ይህንን ለማረም ከድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ ጀምሮ እስከታችኛው የአመራር እርከን ድረስ ፈትሾ እርምት በመውሰድ ውጤቱን ለአባላቱና ለህዝቡ እንደሚያሳውቅ ውሳኔ አሳልፏል።
አሁን ችግሩ በተከሰተባቸው እና ህዝቡን ስጋት ውስጥ ያስገቡ እንቅስቃሴዎች ጎልተው እየታዩ መሆናቸውን በገመገመባቸው አካባቢዎች ካለፈው ጉድለቶች ትምህርት በመውሰድ በፍጥነት የአመራር ስርዓቱን ለማስተካከል የፖለቲካ ተጠያቂነቱን ማረጋገጥ መጀመሩን አስታውቋል።
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ቀናት ተወያይተው በነበሩ ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ የፖለቲካ፣ የጸጥታ እና የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በተመለከተ ከትናንት ሐምሌ 18ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ክልል አቀፍ የአመራር መድረክ በሀዋሳ መጀመሩም ታውቋል።
አዲስ ዘመን ሀምሌ 19/2019
ኢዜአ እና ፋና