
አዲስ አበባ፡- ሐምሌ 22 ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የከተማ አስተዳደሩ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ጉድጓድ ማዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡
የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ዝግጅቱን አስመልክቶ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ወይዘሪት ፌቨን ተሾመ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት፤ በከተማ አስተዳደሩ 400 የመትከያ ሳይቶች የተለዩ ሲሆን፤ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቋል።

በዕለቱ 100ሺ ወጣቶች ዝግጅቱን ለማስ ተባበር መዘጋጀታቸውን የጠቀሱት ኃላፊዋ፤ ሥራዎችን የሚመራ ግብረ ኃይልም መቋቋሙን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡ ጨምረውም በአራዳ ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የመትከያ ስፍራ በሌላቸው ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በወረዳቸው በመገኘት ችግኞችን በመውሰድ በግቢያቸው እና ከግቢያቸው ቀረብ ባሉ አካባቢዎች መትከል ይችላሉ ብለዋል፡፡
በማስፋፊያ አካባቢ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በየአካባቢዎቻቸው በተዘጋጁ የመትከያ ጣቢያዎች በመገኘት መትከል እንደሚችሉ የገለጹት ወይዘሪት ፌቨን፤ በከተማዋ ያሉ ዲፕሎማቶችም የሚሳተፉበት ቦታ እንደተዘጋ ጀላቸው ተናግረዋል።
በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች በሙሉ የችግኝ ተከላ ላይ ስለሚሳተፉ የአገል ግሎት መስጫ ተቋማት ለአገልግሎት ዝግ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ ወይዘሪት ፌቨን የከተማው ነዋሪ ለከተ ማው ያለውን ፍቅር እና በጎ አመለካከት ችግኝ በመትከል በተግባር እንዲገልፅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
አዲስ ዘመን ሀምሌ 19/2019ምህረት ሞገስ