ከወር በፊት በኢትዮጵያ ምድር በደረሰ አስቃቂ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወት በማለፉ የብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ በሃ ዘን ተሰብሯል። የአውሮፕላኑ የመረጃ ቋት ከተገኘ በኋላ ይፋ በተደረገው የመ ጀመሪያ ደረጃ ውጤትም የአደጋው መን ስኤ በአውሮፕላኑ አብራሪዎቹ ስህተት እንዳልሆነ በቅርቡ ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ የጉዳዩ ዋነኛ ማጠንጠኛ ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ሆኖ ቆይቷል። በሂደትም ኩባንያው ያመረታቸው ማክስ 8 አውሮፕላኖች የሶፍ ትዌር ችግር እንዳለባቸው ተረጋግ ጧል፤ ለደረሰው አደጋም ይቅርታ ጠይቋል።
ሰዎች በእግራቸው አልያም የተለያዩ የመጓጓዣ መንገዶችን በመጠቀም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ይጓዛሉ። ያሰቡት ቦታ ላይ በሰላም እንዲደርሱም በየእምነታቸው ፀሎት ያደርሳሉ፤ መልካም እድል እንዲገጥ ማቸውም ይመኛሉ። ኦዲቲ ሴንትራል የተሰኘው ድረገፅ ከሰሞኑ ባወጣው ዘገባ መሰረት የሰው ልጅ ጉዞው ቀና እንዲሆንለት እንዲህም ይመኛል ይለናል።
እንደ ዘገባው ከሆነ፤ ዋንግ የተሰኙት የ66 ዓመት ቻይናዊ ወይዘሮ በቲያንጂን አየር መንገድ በረራቸውን ለማካሄድ ይገኛሉ። በረራቸው ቀና ይሆንላቸው ዘንድ አውሮፕላኑ ለመነሳት ከማኮብኮቡ በፊት ስድስት ሳንቲሞችን ወደ አውሮ ፕላኑ ሞተር ውስጥ ለመወርወር ሙከራ ያደርጋሉ። ይሁንና ወይዘሮዋ በአየር መንገዱ ሰራተኞች በመታየታቸው ሳንቲ ሞቹን በአውሮፕላኑ ግዙፍ ሞተሮች ውስጥ ከመወርወራቸው በፊት በቁጥጥር ስር ይውላሉ።
ወይዘሮዋ ለምን ሳንቲሞቹን ወደ አውሮፕላኑ ሞተሮች ለመወርወር እንደፈ ለጉ በአውሮፕላኑ ሰራተኞች ቢጠየቁም ‹‹አሻፈረኝ እኔ አይደለሁም።›› ይላሉ። የኋላ ኋላ ግን በአየር መንገዱ የደህንነት ካሜራዎች አማካኝነት እርሳቸው መሆና ቸው በመረጋገጡ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ተጠርጣሪዋ ወይዘሮ ለተጨ ማሪ ምርመራ በአየር መንገዱ ለአስር ቀናት እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን፣ በእርሳቸው ምክንያት በአውሮፕላኑ ሊጓዙ የነበሩ
መንገደኞች ሁለት ሰአት ከዘገዩ በኋላ በሌላ አውሮፕላን ተሳፍረው ሺፌንግ ወደተሰኘችው ከተማ ለመብረር ተገደዋል።
በወቅቱ በወይዘሮዋ የተፈፀመው ድርጊቱ ሁሉንም ያስገረመና ግራ የሚያጋባ መሆኑን መረጃው የጠቀሰ ሲሆን፤ ድርጊቱ ከተፈፀመ ከአንድ ወር በኋላ የ31 አመቱ ሌላኛው ቻይናዊ በሃይናን አየር መንገድ ለመጓዝ ለእርሱም ሆነ ለቤተሰቦቹ መልካም እድል እንዲገጥመው በማሰብ ወደ አውሮፕላኑ ሞተር ሳንቲም ለመወርወር ሙከራ በማድረጉ እርሱም ‹‹በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል›› ብሏል።
እንደእድል ሆነና ቻይናዊው ወጣት የወረወራቸው ሶስት ሳንቲሞች ኢላማቸውን ሳይመቱ በመቅረታቸው ወደ አውሮፕላኑ ሞተር ውስጥ ሳይገቡ ቀርተዋል። ይሁንና ወጣቱ ይህን ድርጊት ሲፈፅም በመታየቱ በአየር መንገዱ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ፍርድ ቤት የአስር አመት ቅጣት አከናንቦታል። በጥር ወር በሃያዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ቻይናውያን ወጣት ሴቶች በጂናን ያዎኪያንግ አየር መንገድ ተመሳሳይ ድርጊት በመፈፃማቸው
በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቻይና ሚዲያዎች መዘገባቸውንም መረጃው አስታውሷል።
በዚህ አመት ብቻ ሰባት የሚሆኑ ሰዎች ለመልካም ምኞት ይሆናቸው ዘንድ በአውሮፕላን ሞተሮች ውስጥ ሳንቲሞችን ለመክተት ጥረት ሲያደርጉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም መረጃው ያስታወሰ ሲሆን፤ እንደዚህ አይነት ሙከራዎች በተለይ ከ2017 ጀምሮ ትልቅ የዜና ርዕስ ሆነው እንደነበርና የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያም እንደነበሩ ጠቅሷል።
መጀመሪያ አካባቢ አየር መንገዶቹ ለድርጊቱ ቸልተኞች የነበሩ ሲሆን ነገሩ እየተደጋጋመ ሲመጣ ግን ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ መጀመራቸውን መረጃው ገልጿል። በየካቲት ወር አንድ የቻይና አየር መንገድ ለመልካም እድል ምኞት በሚል በአውሮፕላን ሞተር ውስጥ ግለሰቦች ሳንቲሞችን ለመወርወር ባደረጉት ሙከራ አውሮፕላኑ ዘግይቶ ላጋጠመው የ20 ሺ ዶላር ኪሳራ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን አስታውሷል።
እንደአጋጣሚ ሆኖ እስካሁን ድረስ ለመልካም እድል ምኞት በሚል ወደ አውሮፕላን ሞተሮች ውስጥ የተወረወሩ ሳንቲሞች አንዳቸውም ያልገቡ ሲሆን ምናልባትም ከነዚህ ሙከራዎች ውስጥ አንዱ ቢሳካ ኖሮ ሊከሰት የሚችለው አደጋ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል በመረጃው ተጠቅሷል። በቻይና ሲቪል አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አውያንግ ጂ ሳንቲሙ የአውሮፕላኑ ሞተር የመሀል ክፍል ቢደርስ የሞተሩን ስራ ሊያስቆመው እንደሚችል ገልፀዋል።
የዘመናዊ የአውሮፕላን ሞተሮች ከውጪ ሊገቡ የሚችሉ ቆሻሻዎች፣ በረዶ ዎችንና ወፎችን ለመቋቋም እንዲችሉ ተደርገው የሚነደፉ ቢሆንም ስለ ሳንቲ ሞች ግን የተጠቀሰ ነገር እንደሌለ መረጃው ገልፆ፤ የሆነው ሆኖ ሳንቲሞቹ ወደ አውሮ ፕላኑ ሞተር ቢገቡ ኖሮ በሞተሩ ላይ ጉዳት በማስከተል ከባድ የአውሮፕላን አደጋ ሊያስክ ትሉ ይችሉ እንደነበር ጠቁሟል። አብዛኛዎቹ አየር መንገዶች በረራቸውን የሚያዘገዩትም እንደነዚህ አይነት ችግሮችን አስቀድሞ ለመቆጣጠር እንደሆነም ገልጿል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 15/2011
በአስናቀ ፀጋዬ