ቅድመ -ታሪክ
ጥቅምት 4 ቀን 2004 ዓ.ም
ቦታው አራት ኪሎ አካባቢ ነው። አንጀት ዘልቆ የሚገባው የጥቅምት ብርድ ምሽቱ ላይ ብሶበታል። ጎዳና ውሎ የሚያድረው ታዳጊ መሳይ ቅዝቃዜውን የተቋቋመው አይመስልም። ጥቂት ሙቀት ለመሻ ማት ጉልበቱን አጥፎ የተኛው ገና በጊዜ ነበር። መሀል አራት ኪሎ ከትልቁ ድልድይ ላይ ኩርምት ያለው የጎዳና ልጅ አይኖቹ ወደታች እያማተሩ ወጪ ወራጁን ይቃኛል።
ድልድዩ ቀን ላይ በርካታ እግረኞችን ያመላ ልሳል። ምሽት ደግሞ መሳይን ለመሰሉ የጎዳና ልጆች የጎናቸው ማረፊያ ነው። አስፓልቱን ለሁለት ከፍሎ መንገደኞችን የሚያሸጋግረው ይህ ድልድይ ከአራት ኪሎ ዩኒቨርስቲ፣ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ህንጻ ለማለፍ የቀና አማራጭ ሆኗል።
ምሽቱ እየገፋ ነው። የመንገድ ላይ መብራቶች ደምቀው የእግረኞች ኮቴ ቀንሷል። ከድልድዩ አንድ ጫፍ ኩርምት ብሎ የተኛው መሳይ ከላዩ የደረበውን አሮጌ ጨርቅ ወደ እግሩ እየጎተተ ሰውነቱን ለማሞቅ ይቁነጠነጣል። ከመንገዱ በታች «ሽው…» የሚሉትን መኪኖች በድልድዩ ቀዳዳ አጮልቆ ያያቸዋል። አልፎ አልፎ በአጠገቡ የሚያልፉ መንገደኞች ኮቴም እየተሰማው ነው።
መሳይ ከለመደው የእግር ኮቴ ጋር ድንገት የተለየ ኮሽታ የሰማ መሰለው። ይሄኔ ከተኛበት ነቃ ብሎ ጠበቀ። አይኖቹን ወደ አንድ አቅጣጫ ልኮም በተለየ ትኩረት አነጣጠረ። አልተሳሳተም። አንድ ጎልማሳ በትከሻው የተሸከመውን ትልቅ ቋጠሮ አስቀምጦ በደረጃው ሲመለስ ተመለከተው።
የጎዳናው ልጅ ያየውን እንደዋዛ ማለፍ አልተቻለውም። ቋጠሮው ቀልቡን ገዝቶታል። በማዳበሪያና አልጋ ልብስ ተጠቅልሎ በገመድ የተጠፈረውን ነገር ጠጋ ብሎ ሊያየው ፈለገ። ምንአልባትም ለእርሱ የሚበጅ አልባሳት ሊሆን ይችላል። እንዲህ ከሆነለት የምሽቱን ሲሳይ ያመ ሰግናል። ብርዱን በሙቀት አሸንፎ የነገዋን ጸሀይ በፈገግታ ይቀበላል።
መሳይ ከተኛበት ተስፈንጥሮ እንደተነሳ ከቋ ጠሮው አጠገብ ደረሰ። በገመድ ጠብቆ የታሰረውና በጨርቅ የተሸፈነው ነገር ፍራሽ ቢጤ መሆኑን የጠረጠረው ሳይዘገይ ነበር። ድንገት ቀድሞ የነበረው ስሜቱ ጥሎት ሸሸ።
ቋጠሮው እሱ እንዳሰበው አልመስል ቢለው ደጋግሞ ያስተውልው ያዘ። እንዲያ የጓጓለትን ጥቅል ቀርቦ መነካካት አልፈለገም። አይኖቹን ከድልድዩ በታች ልኮ አማራጭ ያለውን መላ ፈለገ። አጋጣሚ ሆነና ሁለት ትራፊኮች ከአይኑ ገቡ። ጊዜ አላጣፈም። ደረጃውን በፍጥነት ወርዶ ስለተመለከተው ጥቅል ነገር ዘረዘ ረላቸው።
ትራፊኮቹ መሳይ ያለውን ሰምተው ከኋላው ተከተሉት። የድልድዩን ደረጃ ወጥተውም «አየሁት» ያለውን ቋጠሮ ቀርበው አስተዋሉት። የጨለማው ማይል ምንነቱን በውል ለመለየት አላስቻላቸውም። በእጃቸው ሳይነኩ በርቀት የተመለከቱት ቋጠሮ በጨርቅ የተጠቀለለ ስጋ መሆኑን ገምተዋል። ግምታቸው ግን እንደነበረ ሆኖ አልዘለቀም። ትራ ፊኮቹ ጥርጣሬ ገባቸው። በጉዳዩ ጥቂት ሲመክሩ ቆይው ለአካባቢው ፖሊሶች በስልክ አሳወቁ።
የፖሊስ ምርመራ
በስልክ ጥሪው ከስፍራው የመጡት የተደራጁ ፖሊሶች የድልድዩን ደረጃ ወጥተው ከጥቅሉ አጠገብ ደረሱ። በፍራሽ ጨርቅ ተጠቅልሎ በአልጋ ልብስ የተሸፈነውን ቋጠሮ ከገመዱ ለይተውም ውስጡን በጥንቃቄ ፈተሹ። እጅግ አስደንጋጭ፣ ለአይን የሚከብድና ለመናገር የሚያዳግት እውነትን
ሊጋፈጡ ግድ ሆነ ።
ፖሊሶቹ ቋጠሮውን ሲፈቱት ከወገቡ በላይ ብቻ የሚታይ የሰው አካልን ተመለከቱ። በጥቅሉ ውስጥ ያገኙት ወንድ፣ በሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኝና አይኖቹ በትዝብት ያዩ የሚመስሉ ወጣትን ነበር። ፖሊሶቹ ምርመራቸውን በጥንቃቄ ቀጠሉ። ፊቱ በእጅጉ ተጎድቶ ጭንቅላቱ ክፉኛ የተመታው ሟች ከንፈሩን ይዞ መላ ገጽታው በስለት ተሸረካክቷል። ሁለት የፊት ጥርሶቹ ወልቀው አንደኛው ጥርሱ ካጠገቡ ወድቋል።
የምርመራ ቡድኑ መረጃዎችን በሙሉ በፎቶ ግራፍ ቀርጾ አስቀረ። የተገኘውን ግማሽ የሰው አካል አንስቶም የጎዳና ተዳዳሪውን ለምስክርነት አስከተለ። ቡድኑ የምርመራ ቆይታውን አጠናቆ ከአካባቢው ሲንቀሳቀስ የምሽቱ ወሳኝ ጥያቄዎች በበቂ ሁኔታ አልተመለሱለትም። የድርጊቱን ፈጻሚ ብቻ ሳይሆን የሟችን ቀሪ አካል የማግኘቱ ስራ ገና ይቀጥላል። ይህን አሰቃቂ ተግባር ማን ፈጸመው? ቀሪውስ አካል የት ደረሰ? ለቡድን አባላቱ ቀላል የሚባል ፈተና አልነበረም።
የጎዳና ተዳዳሪው መሳይ በዛን ምሽት ቋጠ ሮውን ተሸክሞ ከድልድዩ ላይ የጣለውን ግለሰብ ለማስታወስ ሞከረ። ሰውዬው አንድ እጁና አንድ እግሩ ጉዳተኛ ስለመሆኑ ትውስ አለው። ይህን መረጃም አንድ በአንድ ዘርዝሮ ለፖሊሶቹ አቀበለ። ለተጨማሪ ጥያቄዎች አዳሩን ከፖሊስ ጣቢያ ያደረገው መሳይ ብቸኛው የአይን ምስክርና ሁነኛ የመረጃ ምንጭ ሆነ።
ሲነጋ ፖሊስ በአካባቢው ጥልቅ የምርመራ ስራውን ጀመረ። በምክትል ሳጂን መንግስቱ ታደሰ የሚመራው ቡድን ለተጨማሪ መረጃዎች አቅጣጫውን አመቻቸ። ስራው ፈታኝና ጥንቃቄ የሚጠይቅ ቢሆንም ቡድኑ የሚታዩና የሚሰሙ መረጃዎችን ይዞ በአካባቢው መንቀሳቀስ ግድ ብሎ ታል።
የሟች አስከሬን በተገኘ ማግስት አራት ኪሎ «ዳብር» ከተባለው ህንጻ አጠገብ በአንድ ቢጫ ኩርቱ ፌስታል የተጠቀለለ ነገር ስለመገኘቱ ጥቆማ ደረሰ። ቡድኑ ፈጥኖ ወደ ስፍራው ሲያቀና በርካታው አላፊ አግዳሚ ቋጠሮውን ከቦ እየተነጋገረ ነበር። የምርመራ ቡድኑ አካባቢውን በሚገባ ፈትሾ በርካታውን ተመልካች ገለል አደረገ።
አሁን ጠብቆ የታሰረው የፌስታል ቋጠሮ ተፈቷል። የፖሊስ ጥርጣሬ አቅጣጫውን አልሳ ተም። ከፌስታሉ ውስጥ የሟች የቀኝ እግር ተጠቅልሎ ተጥሏል። የምርመራ ቡድኑ የተገኘውን አንድ እግር በጥንቃቄ አንስቶ አስፈላጊ የሚባሉ ማስረጃዎችን ወሰደ። የሆነውን ለማየት መንገዱን ካጨናነቁት መሀል ደረታቸውን የሚመቱ፣ በሀዘኔታ ከንፈራቸውን የሚመጡና በግርምታ አፋቸውን የያዙ በርክተዋል። ፖሊሶቹ እነዚህን ስሜቶች እየነጠሉ ይለያሉ። ከነዚህ መሀል ግን የፖሊሶቹ ጠርጣራ ዓይኖች በአንድ መንገደኛ ላይ አነጣጠረ።
ሰውዬው በትከሻው ላይ ስል መጥረቢያና የተጠቀለለ ወፍራም ገመድ ይዟል። ግለሰቡ ዛፍ ቆራጭ ሊሆን እንደሚችል የገመቱት ፖሊሶች በዚህ ብቻ ሊያልፉት አልፈለጉም። በጊዜው በቦታው ላይ መገኘቱና በጉልበቱ ላይ በግልጽ የሚታይ ደም መገኘቱ ጥርጣሬያቸውን አጉልቶታል። ዛፍ ቆራጩ በድንጋጤ መርበትበት ጀምሯል። ለጥያቄ እንደሚፈለግ ተነግሮትም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱት።
አሁን የሟቹ ከወገብ በላይ አካልና የቀኝ እግሩ በተለያዩ ስፍራዎች ተጥሎ ተገኝቷል። እስካሁን ግን የግራ እግሩ የት እንዳለ አልታወቀም። የሰውዬው ማንነትና የድርጊቱ ፈጻሚዎች መድረሻ አለመታወቅ ደግሞ ለምርመራ ቡድኑ ዕንቅልፍ የሚነሳ ሆኗል። በአካባቢው ይህ አሰቃቂ የሚባል ድርጊት መፈጸሙ የሰሙትን ሁሉ ሲያነጋግር ዋለ። ለፖሊስ ግን
፱
ሁኔታው ከግርምታ በላይ ሆኗል። ቀሪውን አካል ማፈላለግና የሟችና ገዳይን ማንነት መለየት ጊዜ የሚሰጠው አልሆነም።
በየአቅጣጫው የሚደረገው ፍለጋ ቀጥሏል። ክቡር የሆነው የሰው ልጅ አካል በአልባሌ ቦታ ተጥሎ ሲገኝ የሌት አውሬና የተልካስካሽ ውሾች ሲሳይ ሊሆን ይችላል። ይህ ስጋት ደግሞ የሁሉን ስሜት የሚነካ መሆኑ አያጠራጥርም። የዛን ለታዋ ጀንበር ከመጥለቋ በፊት ግን ለፖሊስ አንድ ጥቆማ ደረሰው። በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 አካባቢ አንድ ቋጠሮ ወድቆ መገኘቱን ሰማ።
ፖሊስ የሰማውን ለማረጋገጥ ወደስፍራው ፈጥኖ ተንቀሳቀሰ። በተባለው ቦታ ደርሶ ቋጠሮውን ሲፈታም ሲፈልገው የነበረው የሟች የግራ እግር ስለመሆኑ አረጋገጠ። ከፌስታሉ ውስጥ የተገኘው አንድ እግር ጫማና ካልሲው ያልወለቀና ከብሽሽቱ ጀምሮ ተገዝግዞ የተቆረጠ ነው። ፖሊስ ይህን ሲመለከት ድርጊቱ ሆን ተብሎ በጥንቃቄ የተፈጸመ ስለመሆኑ ገመተ። በፌስታሉ የተገኘውን ተጨማሪ የሟች ቁርጥራጭ አካልና ሌሎችንም ማስረጃዎች በፎቶግራፍ ቀርጾም ለፎረንሲክ የምርመራ ክፍል ላከ ።
የምርመራ ቡድኑ በየስፍራው ሲያስሰው የዋለውን የሟች አካላት በተሟላ ሁኔታ አግኝቷል። ቀጥሎ የሚቀረው ነገር ቢኖር የሟችን ማንነት መለየትና ለድርጊቱ መፈጸም ምክንያት የሚሆኑ ጉዳዮችን መመርመር ይሆናል። አሁንም ቡድኑ በጥርጣሬ የያዘውን ዛፍ ቆራጭ ጉዳይ ሳይዘነጋ መረጃ ማሰባሰቡን ቀጥሏል። በማግስቱ ለምርመራ ቡድኑ ከአካባቢው ፖሊስ የደረሰው አንድ መረጃ ደግሞ በይደር የሚተው አልሆነም።
ከፖሊስ ጣቢያው ተገኝተው ሀሳባቸውን መግለጽ የጀመሩት ሰው ለዕለቱ ተረኛ ፖሊስ ሪፖርት እያደረጉ ነው። ግለሰቡ በአካባቢው የሚገኝ አንድ የግል ኮሌጅ ባለቤት ናቸው። ከጥበቃ ሰራተኞቻቸው አንዱ ትላንት ምሽት እንደወጣ ሳይመለስ መቅረቱን አስመዝግበዋል። የምሽት ተረኛው በጊዜ ኳስ ለማየት በሚል በመሄዱና ባለመመለሱ ጓደኛው ስራውን ሸፍኖለት እንዳደረ ተናገሩ።
ፖሊስ ይህን መረጃ በአግባቡ ሰንዶ ወደተባለው የግል ኮሌጅ ተንቀሳቀሰ። በግቢው ደርሶም የጥበቃ ሰራተኞቹን ለማነጋገር ሞከረ። በተለይም መረጃውን ለኮሌጁ ባለቤት ያደረሰውንና ስራውን ሸፍኖለት አድሯል ከተባለው ጥበቃ አንድ ጠቋሚ ፍንጭ እንደሚገኝ ተገምቷል። ግለሰቡ ለምርመራ ሲቀርብ የፖሊስ አይኖች ቁመናው ላይ ተመላለሱ።
የጎዳና ተዳዳሪው ታዳጊ ስለሰውዬው አካል ጉዳተኝነት የተናገረው የሚረሳ አይደለም። ከፖሊስ ፊት የቆመው ግለሰብ ደግሞ በአንድ እጁና እግሩ ላይ በግልጽ የሚስተዋል ጉዳት አለበት። አሁን የፖሊሶች አይን ይበልጥ ነቅተዋል። ሰውዬው ጠፍቷል የተባለው ጥበቃ ባልንጀራ መሆኑና የጎዳናው ልጅ የሰጠው ምልክት መገጣጠማቸው ጉዳዩን ያለጥርጣሬ ለማለፍ የሚያስችል አልሆነም።
ምርመራው ቀጥሏል። ፖሊስ በተለየ ስልት ይጠይቃል፣አካል ጉዳተኛው ተጠርጣሪም በአግባቡ ይመልሳል። ሰውዬው ላይ የተለየ ገጽታና ድንጋጤ እየተነበበ አይደለም። ጥቂት ቆይቶ ግን ግለሰቡ ለፖሊሶች ጥያቄ አመቺ ሆኖ ተገኘ። የሆነውን ሁሉ ለመናገር ፈቅዶም ታሪኩን አንድ በአንድ ማስረዳት ጀመረ።
ደሳለኝ ብሩና መንግስቱ ተካ በባልንጀርነት ህይወትን ሲጋሩ ቆይተዋል። ደሳለኝ መንግስቱን ሲያገኘው በቂ የሚባል መተዳደሪያ እንዳልነበረው ይናገራል። ውሎ አድሮ ግን እርሱ ከሚሰራበት የግል ኮሌጅ በጥበቃ ስራ አስቀጥሮት አብረው መኖር ጀመሩ። ውሎና አዳራቸው በአንድ መሆን ሲጀምር ግን የቀድሞ መግባባታቸው ጠፍቶ በትንሽ በትልቁ መነታረክ ጀመሩ።
መንግስቱ ከደሳለኝ ጋር በተጋጨ ቁጥር ሁሌም አካል ጉዳተኝነቱን እያስታወሰ ይሰድበዋል። ደሳለኝ ይህን በሚሰማ ጊዜ ውስጡ በንዴት እየጋለ ጥርሱን ሲነክስ ይውላል። የትናንት ማንነቱንና የዛሬ ለውጡን እያነጻጸረም አሁን ለሚገኝበት ህይወት ባለውለታው መሆኑን ሊነግረው ይሞክራል። ይህ ምልልስ ግን እያደር በቂምና ጥላቻ መዋዛት ያዘ ። ሁለቱ ባልንጀሮችም ሳይለያዩና ሳይግባቡ አብረው መኖራቸውን ቀጠሉ።
ጥቅምት 4 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት ግን በሁ ለቱ መሀል የነበረው ቂምና በቀል መልኩን ቀየረ። መንግስቱ ገና በጊዜ በተለመደው ስድቡ ሸንቆጥ አድርጎት መውጣቱ ደሳለኝን ሲያብከነክነው ቆይቷል። ሁሌም ባልንጀራው አካል ጉዳተኝነቱን እያሳበበ የሚያሳርፍበት ስድብ ስሜቱን እንደጎዳው ነው። ይህን እያብሰለሰለ ባለበት አጋጣሚ ድንገት በር መንኳኳቱ ደሳለኝን ከነበረበት ሀሳብ አነቃው። ከመቀመጫው ተነስቶም በሩን በፍጥነት ከፈተ። ኳስ ለማየት ውጭ ያመሸው ጓደኛው መንግስቱ ነበር።
መንግስቱ ወደውስጥ ከመዝለቁ ደሳለኝ በያ ዘው ወፍራም ብረት ግንባሩ ላይ ክፉኛ መታው። ለመውደቅ ሲንገዳገድም ለኮሌጁ አጥርና ለቤቱ ግድግዳ የሆነው ግንብ ተቀበለው። የትንፋሹን መጥፋት እንዳረጋገጠ ደሳለኝ ከግቢው እንዴት አውጥቶ እንደሚጥለው አሰበ። በወቅቱ ወደ አዕምሮው የመጣለት ብቸኛ መላ አካሉን እየ ቆራረጠ ማስወገድ ነበር።
ደሳለኝ ጊዜ አላጠፋም። አስቀድሞ ያዘጋጀውን መጥረቢያ አንስቶ በጓደኛው በድን ላይ አነጣጠረ። መጥረቢያው አስከሬኑን ከሁለት ከፍሎ ሲጥለው ወለሉና ግርግዳው በትኩስ ደም ጨቀየ። ደሳለኝ የያዘውን መጥረቢያ አለቀቀም። ከወገቡ በላይ ያለውን አካል አለያይቶ ሲጨርስ በጨርቅና በማዳበሪያ ጠቀለለው። በቀሪ አካሉ ላይ በሩን ዘግቶና የያዘውን ተሸክሞም ወደ አራት ኪሎ ድልድይ ገሰገሰ። ያሰበውን ፈጽሞ ሲመለስ ሁለቱ እግሮች እንደተጋጠሙ አገኛቸው። እግሮቹን እንደሚያመቸው ለያይቶ በተለያየ ፌስታል እየ ቋጠረ ከተለያዩ ስፍራዎች ጥሎ ተመለሰ። ቀሪውን ምሽት የግርግዳውንና የወለሉን ደም ሲያጥብና ሲያጸዳዳ አሳለፈ ።
ደሳለኝ ለፖሊስ ቃሉን ሰጥቶ ሲጨርስ ድርጊቱን የፈጸመው ባልንጀራው «ሽባ» እያለ ለሚሰድበው ድርጊት አጸፋ እንደሆነ በማረጋገጥ መፀፀቱን ተናገረ። አራት ኪሎ ከመሸጋገሪያው ድልድይ ላይ ተገኝቶም ያደረገውን ሁሉ መርቶ አሳየ ። የጎዳናው ታዳጊ መሳይ ግለሰቡን ባየ ጊዜ ስለማንንቱ ትክክለኛውን ምስክርነት ሰጠ።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሚያዝያ 12/2011
በመልካምስራ አፈወርቅ