የ82 አመቱ አዛውንት የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ህዝባዊ ተቃውሞ ከበረታባቸውና የሠራዊታቸውን ድጋፍ ካጡ በኋላ ስልጣን በመልቀቅ የአገሪቱን ዜጎች በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። ላለፉት 20 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩት ቡተፍሊካ ተቃውሞ ቢበረታባቸውም ለአምስተኛ ጊዜ ለመመረጥ ያላቸውን እቅድ ይፋ አድርገው ነበር።
ፕሬዚዳንቱ የዛሬ ስድስት ዓመት ካጋጠማቸው ስትሮክ በኋላ ለሕዝብ የሚታዩት አልፎ አልፎ ነበር። የፕሬዚዳንቱን ከስልጣን የመውረድ ዜና ተከትሎ በአልጄሪያ ዋና ከተማ አልጀርስ በደስታ የፈነጠዙ አልጄሪያውያን የሀገራቸውን ባንዲራ እያውለበለቡ መንገ ዶችን በመኪና ጥሩምባ አድምቀው ታይተዋል።
ቡተፍሊካ እንደ እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2014 በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ አሸንፈው በ1999 የተረከቡትን ስልጣን ሲያስቀጥሉ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው መልዕክት አስተላልፈው አንድም ቀን ለህዝብ አልታዩም ነበር። በዚህ ምክንያትም አገሪቱ በማይታይ ፕሬዚዳንት መመራት ከጀመረች ስድስት አመታትን አስቆጥራለች።
ዛሬ ቡተፍሊካ በኤ.ፒ.አስ. ዜና ተቋም በተሰራጨ መግለጫ ተናገሩ እንደተባለው ለአገራቸው ባደረጉት አስተዋፅዖ እንደሚኮሩና አልጄሪያውያን አንድነታቸውን እንዲጠብቁ እንደሚፈልጉ፣ ከዚህ በፊት ላጋጠመው ውድቀት ይቅርታ እንደሚጠይቁ፣ለአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፋንታ ሲሉ ካለምንም ሀዘኔታ የፖለቲካውን ምህዳር እንደሚተው አሳውቀዋል። “ይህ የፈጣሪ ፍቃድ ነው። መቶ በመቶ የዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንደሚኖር እተማመናለሁ።
ይህ በጣም ወሳኝ ነው። የከዚህ ቀደም የስርዓቱ አገልጋዮች የነበሩትን በአጠቃላይ ከስልጣን ማውረድ አለብን፤ ያ ነው ፈታኙ ነገር” ሲል አንድ ግለሰብ ለሮይተርስ ተናግሯል። የተቃውሞው መሪ ከሆኑት መካከል አንዱ «የፕሬዚዳንቱ ከስል ጣን የመልቀቅ ዜና ከመሰማቱ በፊት ቡተፍሊካ የሚያደርጉት ማንኛውም ውሳኔ ለውጥ አያመጣም በተቃው ሟችን እንገፋበታለን ሲል» ተደ ምጦ ነበር።
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተሳ ተፉት አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ አዲስ መንግሥት ተመስርቶ ማየት እንደሚፈልጉ ሲናገሩ ተደም ጠዋል። ቡተፍሊካ ከሥልጣን የመው ረዳቸው ዜና ከተሰማ በኋላ ውሳኔው ወዲያውኑ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጧል። በአልጀ ሪያ ህገ መንግሥት መሰረት ቀጣይ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ፕሬዚዳንቱን የሚተኳቸው የሴኔቱ አፈጉባኤ ይሆናሉ።
አዲስ ዘመን መጋቢት 27/2011
በጋዜጣው ሪፖርተር