ብዙ ሰዎች ነጻነት የሚለውን ቃል ከፖለቲካዊ አውድ ጋር ብቻ ያቆራኙታል:: ሲተነትኑትም የሚታየው ከዚሁ አኳያ ነው:: ይህ ትክክል አይደለም! ነጻነት የሚለውን ቃል ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ጭምር ነው:: እንደ አውዶቹ ገብቶ ጥምረቱን የሚያሳይም ነው:: ምክንያቱም ነጻነት የሚለው ቃል የሰው ልጅ ባለበት ሁሉ ሊነሳ የሚችል ጉዳይ ስለሆነ። ስለነጻነት ሲነሳ ከሰዎች አዕምሮ በርካታ ጥያቄዎች ይሰነዘራሉ:: ይኸውም ነጻነት ማለት ምን ማለት ነው? ፣ የት እና መቼ መተግበር ተጀመረ ? የሚሉት ጥያቄዎች መሰረታዊ ናቸው::
ከዚህ አንጻር ነጻነት ስለተባለው ጽንሰ ሃሳብ ማደግ እና መጎልበት ኢትዮጵያውያን ምንም አይነት አስተዋጾ እንደሌላቸው ሊናገሩ እና ሊጽፉ የሚዳዳቸው አሉ:: ነገር ግን በተለይም ከባህላዊ ክንዋኔዎች ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያዊያን ልክ ነጻነትን የሰበከ አለ ለማለት ያስቸግራል:: የአለም አገራት ጭምር ይህንን ይመሰክራሉም::
ኢትዮጵያዊያን ለልጆቻው ስለነጻነትን የሚያስተምሩት ገና ከልጅነት ጀምሮ መሆኑ ደግሞ አንዱ ነው። እንዴውም የኢትዮጵያ ህጻናት አፋቸውን የሚፈቱት ስለነጻነት እያወሩ እና እየተጫወቱ እንደሆነ የቡሔ በዓልን ብቻ በመጥቀስ መናገር ይቻላል:: ከዚያም በኋላ ለሴቶች የነጻነት ገጸ በረከትን ይዞ ብቅ ያለው የነሐሴ ወር ስጦታም አንዱ ነው:: እናም እነኝህ የደስታ በዓላትን ስናነሳቸው እንዲሁ ጨዋታ ብቻ አድርገን አይደለም! በባህላዊ ህግ እና በስርዓት የሚመሩ የነጻነት ቀን ማስተማሪያዎች እንጂ::
የሃገራችን ልጆች ነጻነትን «ሀ፣ሁ» ብለው የሚጀምሩበት ትምህርትቤት ሳይገቡ ነው:: የመጀመሪያው የነጻነት ትምህርት ቤታቸውም ‹‹ቡሔ በሉ፤ ልጆች ሁሉ ›› እያሉ በሚያዜሙት ጨዋታ ነው:: ይህ ሲሆን ደግሞ በሕግ እና ስርዓት ታጥረው ፤ የሃገራቸውን እሴትና ወግ ጠብቀውም ነው:: በዚህም በሕግ የጸና እሴታችን ልጆችን ብቻ በስፋት እንዲያሳትፍ ተደርጎ መልካሙን የልጅነት ጊዜ በመልካም ስብዕና እያጎለበቱቱ እንዲሄዱ በማሰብ ቡሄ በሉ እያልን ሺህ ዓመታት አስቆጥረናል::
በዚህ ወቅት በስራ የተጠመደ ልጅ እንኳን ቢሆን ከመጫወት አይከለከልም:: ምክንያቱም በዓሉ የእርሱ የነጻነት ቀን ነው:: እናም ብዙ ሥራ እንኳን ቢኖር ሌላ ሰው እንዲሰራው ተደርጎ ከእኩዮቹ ጋር በመሆን እንዲቦርቅ በነጻ ይለቀቃል:: ይህ እለት የደስታና የፌሽታ ቀን በመሆኑም የፈለገውን እያደረገ ይውላል:: ከትርጓሜው ብንነሳ ቡሔ ማለት በራ፣ ብርሃን ሆነ፤ ደማቅ ፣ ገላጣ ሆነ ማለት ነው:: እናም በዚህ ወቅት የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃ ወቅት ስለሚተካ ልጆች ችግር ይገጥማቸዋል ተብሎ አይታሰብምና ብሩሁን ቀን በለምለሙ ሜዳ ላይ እንዲያሳልፉ እድሉ ይሰጣቸዋል::
ቡሔ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ጊዜ ስለሆነ ብራ ተብሎም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ነጻነታቸውን የሚያውጁት ልጆች ብቻ ሳሆኑ ወላጆችም ናቸው:: ምክንያቱም ልጆችን ከመጠበቅ ያርፋሉ:: እናም ‹‹ቡሄ ከዋለ የለምት ክረምት ፤ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት ›› ለእናትም ለልጅም ነጻነትና እረፍት ይሆናል ማለት ነው::
የቡሔ ሌላው የነጻነት ተምሳሌነት (ሊጥ ቡኮ) ከሚለው ስያሜው ጋር በተያዘ የሚመጣው ባህሪው ነው:: በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ሙልሙል ተጋግሮ የሚታደልበት በዓል ነው:: እንደምታውቁት ዘመድም ሆነ አልሆነ የቡሔ ተብሎ በልጅ ልክ ዳቦ በየቤቱ ይወሰዳል:: ትኩሱን ዳቦ መግመጥ ደግሞ ለልጆች ደስታን ይሰጣል:: በእርግጥ የዚህ ስጦታ ምስጢር ሀይማኖታዊ ነው::
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር:: እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም:: በዚህ ጊዜ የልጆቹ መዘግየት ያሳሰባቸው ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ:: ታዲያ ያንን ማስታወሻ አሁን ላይ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ ይታደላል::
በዚህ የነጻነት ቀን ውስጥ ሌላዉ ልጆች እንዲተገብሩት የሚፈቀደውና ደስታን የሚፈጥረው ነገር ጅራፍ ማጮህ ነው:: ስለዚህም በዓሉን ለማክበር ሲያስቡ ብዙ ጊዜ ተሰጥቷቸው የበዓሉ ቀን ከመድረሱ በፊት ዝግጅት ያደርጋሉ:: ከመኖሪያ ቤታቸው ርቀውና በሜዳና በተራራማ አካባቢ ላይ ሆነው ጅራፍ ግርፊያ ጭምር ያደርጋሉ:: የመወዳደር አቅማቸውን ያዳብራሉም::
በቡሄ ዕለት ልጆች በየእድሜ ክልላቸው ሆነው ለበዓሉ የተዘጋጀውን ሙልሙል ዳቦ በአገልግል ቋጥረዉ ከብቶቻቸውን ይዘው ወደ ሜዳ ይሄዳሉ:: የያዙትን ሙልሙል ዳቦ በአንድ ላይ ተሰብስበው ይበላሉ:: ከዚያም በኋላ ” ቡሄ መጣ ያመላጣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ ” እያሉ የየራሳቸውን ጅራፍ ያጮሃሉ:: የጅራፍ ግርፊያም አንድ ለአንድ በመመራረጥ ያደርጋሉ:: የቀን ውሎአቸውን በዚህ ካሳለፉ በኋላ አመሻሽ ላይ ከብቶቻቸውን ይዘው ሁሉም ወደየቤታቸው ይመለሳሉ:: ማታ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ለበዓሉ የተዘጋጀው ዝግጅት ይታደማሉ::
ሁሉም የሰፈር ልጆችና አባቶች በአንድ ቦታ ተሰብስበው የችቦ ማብራት ስነ- ስርዓቱን ያከናውናሉ:: አባቶች እየመረቁ ከዓመት ዓመት ያድርሰን እያሉ ልጆቹ ደግሞ ጅራፍ እያጮሁ ይቆያሉ:: የችቦ ማብራት ስነ-ስርዓት ካበቃ በኋላ ተመራርቀው አባቶች ወደየቤታቸው ሲመለሱ ልጆች ግን በአንድ ላይ ተሰብስበው በየመንደሩ እየዞሩ” ሆያ ሆየ ” እያሉ ይጨፍራሉ:: ዳቦ ዋነኛ ስጦታ ሲሆን፤ አሁን አሁን ግን ነገሩ ተቀይሮ ብር ሆኗል:: ግን ነጻነትን የማክበሩ ጉዳይ ሳይቀንስ የቀጠለ ነው::
ሌላው የቡሔ በዓል ለልጆች ነጻነትን የሰጠ እንደሆነ የምናረጋግጠበት ጉዳይ ‹‹በቡሔ ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› አይነቱ ተግባር ነው:: ማለትም በጨዋታቸው ተደሰተም አልተደሰተም በሕግ የታሰረውን እሴት ያላከበረን ሰው በግጥሞቻቸው ይፌዝበታል:: መቆጣት ደግሞ በምንም መልኩ አይቻልም:: እናም ልጆች በነጻነት ትልቁ ሰው ጭምር ለምን አልሰጠኸንም በሚል ይሳለቁበታል:: በዚያው ልክ ምንም ይሁን ምን ከተሰጣቸው ያሞግሳሉ:: ያው በዛሬው ተቃራኒ ነገሮች ቢመጡም::
አባቶች ይህንን ቀን ሲመርጡት ሀይማኖታዊ ትርጉሙ እንዳለ ሁሉ ተፈጥሯዊም ግዳጅ አለው:: አንዱ እንደ አገራችን ያለው የአየር ጠባይ ሲሆን፤ ዕለቱ ብራ የሚውልበት ስለሚሆን ምስራች ለመንገር ጥሩ ጊዜ እንደሆነ ያምናሉና መርጠውት ለልጆች ጊዜውን ሰጥተውታል:: ተተኪነታቸውንም ለማብሰር የተጠቀሙበት እንደሆነም ይነገራል:: ምክንያቱም የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ ሲመጣ ደስተኛ ቤተሰብን ለመፍጠር ልጆችን ማስደሰት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው:: ስለዚህም በየአካባቢው በገላጣው፤ ወገግታ በተፈጠረበት በብርሃኑ ወቅት ቡሔን እንደፈለጋቸው እንዲያከብሩት ፈቅደውላቸዋል::
ቡሄ በአብነት ተማሪዎች ዘንድም ትልቅ የነጻነት በዓል ነው:: በዚህም ደብረ ታቦር ‘የተማሪዎች በዓል’ እየተባለ ይጠራል:: ምክንያቱም በዚህ ወቅት ተማሪዎቹ ቀደም ብለው “ስለ ደብረ ታቦር” እያሉ ይለምኑና ደግሰው ማህበረሰቡን በመሰብሰብ ያበላሉ:: ከቡሔ ወጣ ስንል የምናገኛቸው በነሃሴ ወር የሚከበሩ የሴቶች የነጻነት በዓላትን ነው::
ይህ በዓል በአማራ ክልል ሻደይ፤ አሸንድዬና ሶለን እንዲሁም እንግጫ ነቀላ እየተባለ ይከበራል:: በትግራይ ደግሞ አሸንዳና ‹‹ዓይኒ ዋሪ›› እያሉ ያከብሩታል:: በዳውሮ ዞን ደግሞ ወሩም ቢለይም ገዚያ እየተባለ በማህበረሰቡ ዘንድም ለሴቶች ነጻነት ክብር ተሰጥቶ በአደባባይ ያከብሩታል:: ክብረ በዓሉ ሴቶችን ማዕከል ያደረገ፤ ለሴቶችና በሴቶችም የሚዘጋጅም ነው:: እናም ነጻነት እንደ ኢትዮጵያዊያን ለልጆች ለሴቶች እየተባለ ጭምር የሚከፈልና የሚከበር እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል:: ለመሆኑ የሴቶች ነጻነት ቀንስ እንዴት ይከበራል ካላችሁ ትንሽ ሀሳብ እናንሳ::
በአማራ ክልል በየዓመቱ ከነሐሴ 14 ጀምሮ ይከበራል:: በተለይም በሰቆጣ፣ በዋግምራ፤ በላሊበላና በቆቦ የመሳሰሉት አካባቢዎች ላይ በስፋት በድምቀት የሚከበርም ነው:: ይህንን ሲያደርጉም ሴቶች በመንገዶችና አደባባዮች ላይ በመውጣት ነፃነታቸውን በማወጅ ሲሆን፤ ሴቶች ያለምንም ተፅእኖ ይጫወታሉም:: በእርግጥ ነጻነታቸው የሚጀምረው በዓሉ ከመድረሱ በፊት ለዝግጅታቸው ከሚሰጠው ጊዜ ጀምሮ ነው:: ከዚያ በተጨማሪም ቤተሰብ አልባሳትንና ጌጣጌጥን መግዛት አለያም ያላቸውን አጥበው መስጠት ይኖርበታል:: ለሴቶች ብቻ ተብሎ የተተወውን የቤት ሥራ እንኳን ሌሎች እንዲከውኑት ይደረጋል:: በቃ ሁሉ ነገር በእነርሱ ፍላጎት ብቻ ነው የሚከወነው::
ማንም መብታቸውን ሊጥስ ስለማይችል በዕለቱ ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው የፈለጉትን ያደርጋሉም:: የተነጠቀ ልጅነታቸው ጭምር የሚካሰው በዚህ ይሆናል:: ስለዚህም የነጻነት ቀናቸውን ለማክበር ከሳምንት በፊት ጀምረው ይዘጋጃሉ:: ይህ ሲሆንም የአንድ ሰፈር ሴቶች በመሰባሰብ፣ የሚለብሷቸውን አልባሳት በመምረጥ፣ ጌጣጌጦችን በመግዛትና በመጨረሻም ቡድኑን የሚያስተባብር አንድ ሰብሳቢም በመምረጥ ነው::
አከባበሩ የእድሜ እርከን የተቀመጠለት ሲሆን፤ እስከ 10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ልጆች፤ ከ10 እስከ 15 ዓመት ድረስና ከ15 ዓመት በላይ የሚል ነው:: መለያቸው ደግሞ ልዩ ልዩ ሲሆን፤ አለባበሳቸው፤ የጸጉር አሰራራቸውና መሰል ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ:: እንደውም በእዚህ ውስጥ የታጨችና ያልታጨች ጭምር ተብሎ ይታያል:: ያገባችም እንዲሁ::
በዓሉ የነጻነት ጊዜ ነው ሲባል አንዱና ሌላው ማሳያው የወደፊት ኑሯቸውን መመልከቻ መድረክ ስለሆነም ነው:: ማለትም ልጃገረዶቹ ለትዳራቸው የሚያጫቸው ሰው በግላጭ የሚያያቸው በዚህ የነጻነት በዓል ወቅት ነው። እንደውም በዚህ ጊዜ ሲጨፍሩ በቤተሰብ ባል ታጭቶላቸው ድፎ ዳቦና በግ ከአማቶቻቸው በእለቱ የሚመጣላቸውም አይጠፉም። ወንዶቹም የሚያጭዋትን ልጃገረድ በዚህ ጊዜ ይመርጣሉ ::
ሌላው ይህ ጊዜ የማመስገኛና ምርቃትን የመቀበያ ጊዜያቸው መሆኑም አንዱ ነው:: ማለትም የነጻነታቸውን ቀን ለማክበር ሲነሱ ጉዟቸውን የሚጀምሩት ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሲሆን፤ መልካሙን ሁሉ ከራሳቸው አልፈው ለአገር ለምድሩ ይለምናሉ:: እንደሚሆንላቸውም ያምናሉ:: ከዚያ በቀድሞው ጊዜ ወደ አካባቢው አስተዳደር ወይም አገረ ገዥው ነበር:: አሁን ደግሞ በአካባቢው ትልቅ የሚባለው ሰው ጋር ጉዟቸውን አድርገው ምርቃታቸውን ይሸምታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ሰው ሳይመርጡ የተሰጣቸውን የነጻነት በዓል ያከብራሉ::
ይህ ጊዜ የተሰጥኦ መለያ ወቅታቸውም ነው:: ምክንያቱም ድምጸ መረዋነታቸውን የሚሞክሩትና የሚያረጋግጡት በዚህ ቀን ነው:: ለመዝፈን ያላቸውንም አቅም በዚህ ዕለት ያውቁታል:: ስለዚህም የቀጣይ ሕልማቸውን ወደማመቻቸቱም ይገባሉ:: እናም ‹‹አስገባኝ በረኛ፣ አስገባኝ ከልካይ፤ እመቤቴን ላይ›› በማለት ማንጎራጎር ይጀምሩና በመቀጠል ‹‹ይሄ የማን አዳራሽ የጌታዬ የድርብ ለባሽ፤ ይሄ የማን ደጅ የእመቤቴ የቀጭን ለባሽ›› በማለት እያሞገሱ ይዘልቃሉ::
በዚህ የነጻነት በዓል ወቅት ሰው አይለይም:: ስለዚህም ለእነርሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ነጻነት የሚታገሉበት ቀን እንዲሆን አድርገው ያሳልፉታል:: ለዚህም ማሳያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖረውን ሰው ሳይለዩ ማሞገሳቸው ነው:: እንዲህ ሲሉም ያወድሱታል ‹‹አሽከር አበባዬ አሽከር አባብዩ (2) ይሙት፣ ይሙት ይላሉ የኔታ አሽከር አበባ አሽከር አይደለም ወይ የሚሆነው ጌታ››:: ይቀጥሉናም ‹‹ከፈረስ አፍንጫ ይወጣል ትንኝ፤ እሰይ የኔ ጌታ ጤና ይስጥልኝ››፤ ‹‹ምድር ጭሬ፣ ጭሬ አወጣሁ ማሰሮ እሰይ የኔ እመቤት ድልድል ወይዘሮ›› ።
ሌላው የሴቶች የነጻነት ቀን ሲከበር ራሳቸውን ማስከበራቸው ተጠቃሽ ነው:: እንዴት ከተባለ ዘፍነው ዘፍነው የሚሸልማቸው ካጡ ወይም ከዘገዩባቸው ዝም አለማለታቸው ሲሆን፤ በግጥማቸው መቃረናቸውን ያሳያሉ እንዲህ እያሉ ‹‹ አንቱን አይደለም የማወሳሳው፤ ቀና ብለው እዩኝ የሰው ጡር አለው››::
የሰሜን ኢትዮጵያ የልጃገረዶች ጨዋታ ወይም የአደባባይ ክብረ በዓል በተለያዩ ባህላዊ ልብሶች በደመቁ ሴቶች ትውፊቱን ጠብቆ ለዘመናት ሲከበር የቆየውም ያለምክንያት አይደለም:: ነጻነትን ለማለማመድ በሚደረገው ሩጫ ውስጥ የሴቶች ፍላጎት አይሎ በመውጣቱ ነው::
ከሰሜኑ ወጣ ስንል ደግሞ በደቡቡም የምናገኘው ነገር አለ:: ወሩንም ሆነ የአከባበሩን ሥርዓት በመጠኑ ለየት ቢልም ተመሳስሎሹ ግን የሰፋ ነው:: ምክንያቱም ይህ በዓል ጥቅምት ላይ የሚከበር ነው:: በዳውሮ ዞን አዲስ ዓመት በገባ በሰባተኛ ሳምንት ማክሰኞ ላይ ይከበራልም:: በሴቶች ብቻ በትልቅ ዛፍ ስር በድምቀት የሚከወንም ነው:: የ‹‹ገዚያ›› እየተባለ ይጠራል::
በዚህ በዓል በሰሜኑ ክፍል እንደሚከበረው የነጻነት ቀን ተደርጎ ቢወሰድምና ሴቶች የፈለጋቸውን እንዲያደርጉ ቢፈቀድም አንድ ታሪክ እንዲሰሩ ግን ይገደዳሉ:: ያው የውዴታ ግዴታ ማለት ነው:: ይህም ከጨዋታው ባሻገር አሻራን የማሳረፍ ጉዳይ ሲሆን፤ በበዓሉ ማጠናቀቂያ ላይ ዛፎችና መድሃኒትነት ያላቸው እጽዋት መትከል ነው:: ከዚያም አለፍ ብለው ቀደም ብለው የተተከሉ እጽዋትን የአካባቢን ስነ ምህዳር ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ያምናሉና እንክብካቤ ያደርጉላቸዋል:: ይህ ደግሞ የሴቶችን እኩልነትና ነፃነትን ከማክበር ባለፈ ሴቶች በአካባቢያቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ንቁ ተሳታፊ እንደሆኑ ያረጋግጣልና ደስተኛ ሆነው ያደርጉታል::
ይህ የነጻነት ጊዜ ለሴቶች የውበትን ማሳያም ጊዜ ነው:: በወቅቱ ሴቶች በፀጉር አሠራራቸው ከአልባሶ እስከ ግልብጭ፣ ከጋመ እስከ ድርብ፣ ጋሜ፣ ቁንጮ፣ ሳዱላና ቅርድድ ተሠርተው አደባባይ የሚውሉበት ነው:: እንደ ሕንቆ፣ አልቦ፣ ድሪ፣ ድኮት፣ ጉትቻ፣ ማርዳ ፤ መስቀል በሚባሉ ጌታጌጦች ተውበው አለባበሳቸውም በመልጉም /ጥልፍ ቀሚስ/፣ ሹፎን፣ ጃርሲ ተውበው በልዕልና የሚታዩበት፣ በነፃነት ነግሠው የሚጫወቱበት ነው።
በአጠቃላይ እነዚህ የነጻነት ቀናት በማሳረጊያቸው ጭምር የተለያዩና ልዩ ትዝታን የሚጭሩ ዘላለም ለነጻነት ያለንን ትግል የሚጨምሩ ሆነው ዛሬ ድረስ ዘልቀዋል::
አሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል እንግጫ ነቀላና አሸንዳና‹‹ዓይኒ ዋሪ›› ወዘተ እየተባለ የሚሰየመው በክረምት ወቅት ከሚበቅለው ተክል ጋር በማዛመድ የወጡ የመለምለም ምስጢራዊ ፍቺዎች በመሆናቸውም ለምድሪቱ ልምላሜ የሚሰጠው ክብርንም የሚያሳዩ መሆናቸውን ነጋሪ አያሻውም:: እናም ይህንን ስም ያወጡለትን ቅጠል በወገባቸው ላይ አድርገው ፍስሃቸውን በየአደባባዩ እየሰበኩ ቀናትን የሚያሳልፉት ሴቶቹ፤ እስከ ነሐሴ 21 ድረስ በሚዘልቀው ቀናቸው ብዙ ሕግጋትንና እሴቶቻችንን የሚያስተምሩና ሰነድ ሆነው የሚቀርቡ እንደሆኑ ሁሉም ሰው መገንዘብ ይኖርበታል::

አዲስ ዘመን ነሃሴ 13/2014