ኢትዮጵያውያን የአገራቸውን ሉአላዊነትና በፍቃዳቸው የመሰረቱትን መንግሥት ከውስጥና ከውጭ የሚቃጣበትን ጥቃት ለመከላከል በአንድነት ቆመዋል። ትግሉ በጦር ሜዳ ግንባር የተወሰነ ሳይሆን ሁሉን አቀፍ ነው። ጠላቶቻችን አገራችንን በመሳሪያ አፈሙዝ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ ማሕበራዊና መሰል ዋልታዎቻችንን በተቀናጀ ሁኔታ በመናድ ዳግም እንዳናገግም አድርገው ለመበታተን ቃል ገብተው ውጊያውን ከከፈቱብን ሰነባብተዋል።
ዳሩ ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ (በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያለ) ቀፎው እንደተነካ ንብ ከዳር እስከ ዳር ተነስቶ ኢትዮጵያዊነትንና አገረ መንግሥቱን ሊያጠቁ የተነሱትን በሚገባቸው ቋንቋ እያናገራቸው ይገኛል።
በተለያየ መልኩ ከተከፈቱብን የጦርነት አውዶች መካከል በቴክኖሎጂው ዘርፍ “የሳይበር ጥቃት” አንዱ ነው። በታላላቆቹ የማሕበራዊ ሚዲያዎች ድጋፍና ቀጥተኛ ተሳትፎ “በዲጂታል” ፕሮፓጋንዳው የሚመራው ይህን የሥነ ልቦና ውጊያም ቢሆን በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እየተመከተና ጠላቶቻችን እንዳሰቡት እንዳይሆን በአግባቡ እየተሰራ መሆኑን መመልከት ይቻላል።
ይሁን እንጂ አሁንም ቀሪ ሥራዎች መኖራቸው እሙን ነው። በኢትዮጵያ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ የሽብር ቡድን የተከፈቱ መሆናቸው በቅርቡ የኢንፎርሜሽን ደሕንነት መረብ ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ከነበሩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ የሽብር ቡድን የተከፈቱ አካውንቶች መሆናቸውን ነው ተቋሙ ይፋ ያደረገው። በኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት ኤጀንሲ የግልጽ ምንጭ መረጃ ኦፕሬሽን ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኃይሉ እንደሚናገሩት፤ 122 ሺህ ሐሰተኛ የማሕበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
ከእነዚህ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ ናቸው ። ከዚህ ባለፈም የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ኅዳር ወር ብቻ 17 ሺህ የሚሆኑ ሐሰተኛ የትዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ የጥፋት ቡድን ተከፍተው ነበር። በአሸባሪው ቡድን በተከፈቱ ሐሰተኛ አካውንቶች በአንድ ቀን ብቻ 25ሺህ የሚደርሱ መልዕክቶች በትዊተር ምህዳሩ ላይ ይሰራጩ እንደነበርም ነው ሃላፊው የገለጹት።
የጥፋት ቡድኑ እነዚህን ሁሉ ዘመቻዎች አድርጎ አልሳካ ሲለው ዲጂታል ፕሮፓጋንዳ- 122 ሺህ ሐሰተኛ የማሕበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ለሽብር ተግባር ተባባሪ ከሆኑ አገራት እገዛ በማግኘት እንዲሁም አስቀድመው አስርገው ያስገቧቸውን ሰዎች በመጠቀም ከእውነታ ውጪ የሆኑ ዘገባዎችን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ታዋቂዎቹ የማሕበራዊ ሚዲያ አማራጮችም ከጥፋት ቡድኑ ጋር የተያያዙ ወይም ለቡድኑ ይጠቅማሉ ያሏቸውን ይዘቶች በፕላትፎርማቸው ላይ እንዲኖሩ ወይም እንዲቆዩ ከመፍቀድ ባለፈ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆኑ ለሌሎች አካላት በስፋት ያሰራጩላቸው / Suggest/ ያደርጉላቸው እንደነበረም አቶ አሸናፊ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል የአገርን አንድነት ወይም ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ አካውንቶችን የመዝጋትና መረጃዎቻቸው እንዳይሰራጩ የማድረግ እንዲሁም አንዳንድ አካውንቶችን መረጃ እንዳይለጥፉ ከማድረግም ባለፈ ለተለያየ ጊዜ ሲዘጓቸው እንደነበር አቶ አሸናፊ አብራርተዋል።
እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች የሚያሳዩት በጦር መሣሪያ ከሚደረገው ጦርነት በተጨማሪ በመረጃ ጦርነቱ መስክ አስቀድሞ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ አሸባሪው ቡድን ጉልበት ያለው በማስመሰል ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳ ስራ ሲሰራባቸው እንደነበረ የሚያመለክቱ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል። ከተቋሙ መረጃ እንደምንረዳው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጅ በዲጂታል የማሕበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎችን በጥንቃቄ መከታተልና ጥቃቶቹን በተመሳሳይ አግባብ መከላከል እንዳለበት ነው።
ይህን ለማድረግ ደግሞ የዲጂታል ፕሮፓጋንዳ ምንነትና እንዴት መለየት እንደምንችል የሚከተለው ከመረጃ መረብ ደሕንነት ያገኘነው ትንታኔ ጠቃሚ ግብአት ነው። ዲጂታል ፕሮፓጋንዳ ምንድ ነው? ዲጂታል ፕሮፓጋንዳ ስንል ከበይነ መረብ ግኝትና መስፋፋት ጋር ተያይዞ የግለሰቦች፣ ድርጅቶች እንዲሁም አገራት የዕለት ከዕለት ነባራዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ሳይበር ምህዳሩ የመግባታቸውን እውነታ ተከትሎ የሳይበር ምህዳሩ ተሳታፊዎችና ተጠቃሚዎች የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን የሚያስከብሩበት መንገድ ነው። የዲጂታል ፕሮፓጋንዳ ባህሪውን ከዲጂታል ምህዳሩ ጋር በማላመድ ማስተላለፍ እንደሚፈለጉት ጉዳይ ክብደትና ቅለት ሆን ተብሎ የሚሰራጩ መጠነ ሰፊ ሐሰተኛ መረጃዎችንና ምስሎችን እንዲሁም መልዕክቶችን በማስተላለፍ የተለያዩ ጫናዎችን በጦርነት ወቅት፣ ከጦርነት በፊት እንዲሁም በድህረ ጦርነት ጊዜ የኃይል ሚዛን የበላይነትን ለመቀዳጀትና ለማስጠበቅ የሚታለም የዘመኑ የመረጃ ጦርነት (in[1]formation warfare) አካል ነው።
የዲጂታል ፕሮፓጋንዳ ዓላማ ምንድን ነው? ከላይ በትርጓሜ ደረጃ እንደተመላከተው የዲጂታል 122 ሺህ ሀሰተኛ የማሕበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ።
ከእነዚህ ሐሰት ፕሮፓጋንዳ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ ናቸው ። ከዚህ ባለፈም የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ህዳር ወር ብቻ 17 ሺ የሚሆኑ ሐሰተኛ የቲዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ የጥፋት ቡድን ተከፍተው ነበር ምህዳሩ ተዋንያኖች በሳይበር ቴክኖሎጂው ውስጥ መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳዎችን የሚያሰራጩበት የተለያዩ ዓላማዎች አሏቸው፤ ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
በመጀመሪያ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ተቀባይነትን ለማግኘት፤ የመረጃ የበላይነትን ለማስጠበቅ፤ ኃይልን ለማጠናከርና የእፎይታ ጊዜን ለመግዛት፤ የተቀናቃኞችን ስም በማጥፋት በሐሰት መወንጀል እንዲሁም በተከታዮቻቸው ዘንድ አመኔታን ማሳጣት፤ ለአካላዊ ጦርነት ቅድመ-ዝግጅት ድጋፍን ለማሰባሰብና ተጨማሪ ኃይል ወይም ተከታይ ለማግኘት፤ የሥነ[1]ልቦና፣ ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫናዎችን በመፍጠር ጦርነትን ማሸነፍ ናቸው።
የመረጃ ጦርነት የሚከናወንባቸው መንገዶች የመረጃ ጦርነት በተለያዩ መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፤ ከነዚህም መካከል ዋነኞቹን ፤በመረጃ ጦርነት ውስጥ እንደዋነኛ የመቀናቀኛ መንገድ የሚቆጠረው የተቃራኒ ወገንን ስም በመጥፎ ማንሳት፣ ማጠልሸት እና ብዙኃኑም እንዲያምን እና ተፅእኖ እንዲፈጥር ማስቻል ነው። ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት፡- ሐሰተኛ መረጃዎችን እና ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን በመፍጠር የተከሰቱ ሁነቶችን በማጋነን ወይም የተበዳይነት ስሜትን እጅግ በማጋነን የሚፈጠሩ እጅግ የተጠኑ እና የተቀነባበሩ እውነተኛ መስለው እንዲታመኑ ተደርገው በምስል፣ በተንቀሳቃሽ ምስል አሊያም በድምጽ የታገዙ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት በተቃራኒ ወገን ላይ የመረጃ የበላይነት መውሰድ እና የብዙኃንን ድጋፍ ለማግኘት ትልቅ ጥረት ማድረግን ያጠቃልላል።
የተቃራኒ ወገንን መረጃ ማጣጣል እና ማስተባበል የፈጠራ ውዥንብሮችን መፍጠር (hoax[1]ing):- ያልተፈጠሩ ሐሰተኛ ውዥንብሮችን በብዙኃኑ ዘንድ በተለያዩ መንገዶች በመንዛት የሰዎችን ትኩረት ማስቀየር፣ ሥነልቦናዊ ጉዳት ማድረስ እና የሰዎችን እሳቤ መበዝበዝ እንዲሁም በዚህ ክፍተት ተቃራኒ ወገንን ማጥቃት። የሳይበር ጥቃቶችን መፈፀም፡- የመንግሥት ተቋማትንና የታዋቂ ግለሰቦችን የማሕበራዊ ትስስር ገጽ አካውንቶችንና ድረ ገጾችን በመጥለፍ የፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን መለጠፍ በዋናነት ሚጠቀሱ የመረጃ ጦርነት የሚከናወንባቸው መንገዶች ናቸው። 122 ሺህ ሀሰተኛ የማሕበራዊ ሚዲያ አካውንቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ።
ከእነዚህ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ከሚያሰራጩ አካውንቶች ውስጥ 49 በመቶ የሚሆኑት በዲጂታል ወያኔ ቡድን የተከፈቱ ናቸው ። ከዚህ ባለፈም የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በ2013 ዓ.ም ጦርነት በከፈተበት ኅዳር ወር ብቻ 17 ሺህ የሚሆኑ ሐሰተኛ የትዊተር አካውንቶችም በዲጂታል ወያኔ የጥፋት ቡድን ተከፍተው ነበር።
ዳግም ከበደ
አዲስ ዘመን ኀዳር 28 / 2014