‹‹የጉልበት ገዥዎች ትራጄዲያዊ አወዳደቅ እያሳዩን ነው። ›› አሌክሳንደር ፑሽኪን የዘንድሮ ክረምት ብዙ ተስፋ እና የሚያደናግሩ ስጋቶች ግን በትግላችን የምንቀይራቸው ተግዳሮቶችን እያሳየን ነው። አምና ሐምሌ 14 ስንመኘው የነበረውን የህዳሴ ግድባችን በጥቂት ቀናት ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ ተትረፍርፎ የኢትዮጵያዊያንን አንጀት ሲያርስ የግብጾች እና የእነሱ ቢጤዎችን ክፉኛ አስደንግጧቸው ነበር።
ግብጾች እና ሱዳኖች በልባቸው እውነቱን እነሱንም እንደሚጠቅማቸው እያወቁ ሀበሻን ያበሳጩ እየመሰላቸው አልተማሩበትም ያው መከራ እስኪመክራቸው ለሀበሾች ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ግን ከ50 ዓመታት የመከራ ጉዞ በኋላ ከሰኔ 14 / 2013 ጀምሮ በምርጫው በጨዋነታችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰከን ብለን ነጮችን ለሁለተኛ ጊዜ በዳግማዊ አድዋ የእኛ የእውነተኛ አስተሳሰብ የበላይነት አስበርግጎ እንዳበደ ውሻ እያክለፈለፋቸው ነው።
የጥንታዊው የጎንደር እና የላሊበላ በመንፈሳዊ ጥብብ እስከ 16ኛው ክ/ዘመን የመሩን መሪዎች አንድ መርህ ነበራቸው ይኸውም በማቴዎስ ወንጌል እና በቁርዓንም ተጽፎ ይገኛል። ፈረንጆቹን በሀይል ያስገረመ በግዕዝም በአረብኛም ተጽፎ በየቤተ መጸሀፍቶቻቸው አስቀምጠው አጥንተውታል። ተምረው የእኛ እያሉ እንደገና እንደ አዲስ በእንግሊዘኛ እያራቡት ነው።
‹‹ በህይወት ጎዳናህ ላይ ባላንጋራህን እወቅበት›› ይላል ማቴዎስ እኛ ግን ከ50 ዓመታት ርኩስ የመርዝ ዘር ብዙ አረም እያበቀለ አረም ማጥፋት አቅቶን ጥቅምት 24 እጃችን አመድ አፋሽ ሆነ። በሬ ካራጁ እንዲሉ ጉድ ተሰራን …ለምን ? ካለፈው ያለመማር አባዜ ተጠናውቶን እንጂ የአሁኑ በህዳሴው ግድብ 10 ዓመት የፈጀው ድርድር ማደናገሪያነቱ እና እጅን ጠምዝዞ በአንቀጽ ሸብቦ ለዘለዓለም ኢትዮጵያን ለመበዝበዝ / የባትጋሩኝ የግብጽ ፖሊሲ / ከእንግሊዞች እና አሜሪካኖች ጋር በመተባበር ሀገራችንን ለመበታተን ተግቶ መስራታቸውን ዝም ብለን እያን ነበርን።
እነሱ ምዕራባዊያን እና አሸባሪው ህውሓት / ተግተው ሲሰሩ እኛ ምን እየሰራን ነበር ?። እኛ ደግሞ ሁልጊዜ ከስህተታችን አለመማራችን ደጋግሞ ዋጋ አስከፍሎናል። እንዴት ከተባለ በብዙ አብነቶች ማስረዳት ይቻላል። አንደኛ ርእሱ ኢትዮጵያ ሐሊብ ናት የሚለውን ትርጉም ለማብራራት ሲሆን በተደጋጋሚ ለብዙ ጊዜያት ስህተታችን ያሰከፈለንን ዋጋ አውቀን ‹ ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን › የሚለው አባባል እንዴት እንደምንተረጉመው ለማሳየት ነው። በግዕዝ ‹ ሐሊብ › ማለት በእጃችን አሁን ያለን ነገር በቂያችን መሆኑን ለማሳየት እና የሌላ ተጨማሪ እንደማያስፈልገን ለማሳየት ነው። ይህ ማለት ከእኛ ኮርጀው ካሰለጠኑት ዘመነኞቹ ዓለም ምንም ነገር አንማርም ለማለት አይደለም። ይህማ globalization አይመለከተንም ብለን ተጨባጩን መካድ ይሆናል።
እውቀቱ እና ጥበብ እያለን ሁልጊዜ ከውጭ መፍትሄ ፍለጋ እንሯሯጥ ነበር። ለምሳሌ ምንም እንኳ በመጸሀፍ ቅዱስ እና በቁርዓን ያለው የህይወት መርህ ‹‹ በህይወት ለባላንጋራህ እወቅበት ›› ቢልም አልተገበርነውም አልተማርንም … በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የጥሞና ጊዜ ብሎ የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ላይ ቢደርስም ምዕራባውያን ለጉዳዩ ቁብ አልሰጡም። እንደውም አሸባሪው ህውሓት ለሀገሬው ቢያስብ ኖሮ ይህንን እድል ይጠቀምበት ነበር።ምዕራባውያኑም ይኸን አይነት የዓብይን መንግስት በመረጡ ነበር ነገር ግን ፍጡር ከባህርዩ በላይ መሆን ስለማይቻል በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለሰብዓዊ መብት ተቆርቁረን ነው ቢሉም የልቡና ውቅራቸው / mind set / ግን ተቃራኒ ስለሆነ ህጻናት እንኳ በግዳጅ የጦር ተሳታፊ ሆነው ዓይናቸው እያየ እንዳላዩ እንዳለሰሙ ሆኗል። የጉልበት ገዢዎች ትራጄዲያዊ አወዳደቅ እንደሚወድቁ ፑሽኪን በድርሰቱ አስተምሮናል በፑሽኪን እምነት ህዝብ በታሪክ ውስጥ የማይደፈር ታላቅ ኃይል እንደሆነ በሚገባ ገልጾታል።
ሌላው የዘመኑ Imperialism ፈጣጣነት ማሳያ ሰሞኑን አሸባሪው የህውሓት ቡድን በጣረ ሞቱ ወቅት የመንግስቱን የጥሞና ጊዜ አስብላቸዋለሁ ለሚለው ህዝቡ እንኳ ቆርቁሮት ከመተግበር ይልቅ ባጎረስኩኝ እጄን ተነከስኩኝ ሆነና የአማራን እና የአፋርን ህዝብ በተራረፉት ከባድ መሳሪያዎች ህጻናት ጨምሮ ንጹሃን እና ዜጎችን በብዛት ጨፍጭፋል: አረጋዊያንን እያረደ እየፈጀ ነው።
ይህን በተመለከተ እነ unicef በሌላ ሀገር ቢሆን ብዙ አቃቂር ሊያወጡበት ሲችሉ የአሜሪካን እና የምዕራባዊያን ተጽዕኖ በርትቶባቸው በግልጽ አሸባሪው ህውሓት እንዳይገልጥባቸው በዝምታ አልፈውታል። ባለጌ ባያፍር ዘመዱ ያፍር እንዲሉ ሌሎች ሀቀኛ አሜሪካውያን ምሁራን እና መልካም አሳቢ አውሮፓውያን የጉዳዩንአሳፋሪነት በገደምዳሜ ከመግለጽ አልተቆጠቡም።
እነ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችሁን ገምግሙ ፈትሹ አለበለዚያዘቀ እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ እያሉ ጀግኖቹ የአባቶቻቸው ልጆች ዲያስፖራዎች በኒውዮርክ እና በሁሉም ግዛቶች ያሳዩዋችሁን ተቃውሞ እንደ ጥሩ እድል ተጠቅማችሁ እንደ ቀደመው ጊዜ ከኢትዮጵያዊያን ጋር በመቀራረብ ጥሩ ግንኙነት ብትፈጥሩ ተጠቃሚው የአሜሪካን የባይደን መንግስት ይሆናል እያሉ የሰላም ጥሪያቸውን አሰምተዋል።
የአሁኖቹ ፈረንጆች አሜሪካኖች እና ምዕራባዊያን የፈሩትን ከአድዋ የተማሩት በአስተሳሰብ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ አንድ የሆነች ኢትዮጵያ በክረምቱ በወልቃይት እና በወሎው ራያ የተፈጠሩት ወጣቶች አሸባሪውን ከጠራረጉ በኋላ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አማካይነት ተሳስረው በልጽገው በምስራቅ አፍሪካ መሪ አርዓያ የኢትዮጵያ ባንዲራ እንደገና ለአፍሪካውያን የመሪነት ሚና ሊፈጥርብን ነው የሚል ነው። የአባይ ግድብ ጎርፍና የወጣቶች ቱግ ብሎ በአንድነት ገመድ መተሳሰር ከመስከረሙ የህዝባዊ መንግስት ምስረታ ጋር ሌሎቹን መጥፎ ያስተምርብናል ብለው ይሐውም ከእኛ የበለጠ የኢትዮጵያ ባህል እንደ ጥቁር ቀለም አደገኛ መሆኑን ያውቃሉ። ጥቁር ቀለምን ለመለወጥ ብዙ ቀለም መጨመር ያስፈልጋል፤ እሱም ከባድ ነው ብዙም ቀለም ብርዝ ያደርገዋል።
ሰዎች በአንድ ጊዜ የአንተን ብዙ ቀለም ማየት ይጀምራሉ። ያ ደግሞ ብዙ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ ሰንደቅአላማ እንደተማሩ ከመስከረም 2014 በኋላ ደግሞ ምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካ በአንድነት ይበለጽግባቸዋል። ይህንን ደግሞ ከሩሲያው የኢትዮጵያ ደም ካለው ፑሽኪን ተምረነዋል። በፑሽኪን እምነት ህዝብ በታሪክ ውስጥ የማይደፈር ታላቅ ሀይል ነው የጉልበት ገዢዎች ትራጄዲያዊ አወዳደቅ ይወድቃሉ።
‹ሐሊብ› የግዕዝ ቃል ነው የበለጠ ግልጽ ለማድረግ ኢትዮጵያም የህዳሴው ግድባችንም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደምንላቸው ናቸው። የህዳሴ ግድባችን ‹ ሐሊብ › ነው ብለን እንየው። ህዝባችን ራሳችን በራሳችን አቅም እና ገንዘብ ገድበን እንጨርሰዋለን እንዳለው በግዕዝ ‹ ሐሊብ › ማለት ከራስ ወይንም ከእኛ በስተቀር ሌላ ተጨማሪ የማያስፈልገው ለማለት ነው ሀሳብም እውቀትም ገንዘብም የእኛው ማለታችን ነው።
ነገር ግን በዘመነ globalization የሆነ አንድ ነገር ለምሳሌ ቴክኖሎጂ ወይም ሌላ ነገር አያስፈልገንም ለማለት አይደለም ለጸጉር ሰንጣቂዎች ሆኖም ግን ቴክኖሎጂውም ለምሳሌ የጎንደር ህንጻዎች እና ከላሊበላ እስከ አክሱም ምዕራባዊው ዓለም መኮረጁ የሚታወቅነው። የአውሮፓ ተሀድሶ በ16ኛው ክ/ ዘመን ከኢትዮጵያ ከሀበሻ ምድር የተወሰደ ነው። ጸባችን ማለትም እኛ ሀበሾች ይህ ሐቅ አይዋጥልንም እኮ እንዴት ተደርጎ ከእኛ ይኮረጃል ነው ክርክሩ ሐቁ ግን እነ አሜሪካ ያኔ አልነበሩም አሜሪካንን በአሰሳ ያገኝዋት የአውሮፓውያን ነጮችም ያኔ ስልጣኔያቸው አላደጉም ነበር ።
እነ ጀርመን ሩሲያ እንግሊዝ ኃያላን አልነበሩም ያደጉት እነ ፖርቹጋል ነበሩ ለዚህም ነው የአባይን ወንዝ ለማጥናት ምንጩን ለማወቅ የተንቀሳሱትና ጎጃም እና ጎንደር ውስጥ አማርኛን እና ግዕዝን የኢትዮጵያ ታሪክን እያጠኑ ሰከላ ወረዳ የደረሱት። ከዚያም በኢትዮጵያ የግዕዝ ብራናዎች እየተመራመሩ የህክምና የጠፈር የክዋክብት ጥናት አንጋጠን በምናየው ሰማይ ያለውን የጸሐይ የክዋክብት የፕላኔቶች ህልውናና ስም ያጠኑት። ሌላው ቀርቶ አለም አሁን የሚጠቀምበትን ቀን መቁጠሪያ ስሙ ይቀያየር እንጂ ምንጩ ወይም መረጃው የተወሰደው ከግዕዝ ብራናዎች ነበር። ይህን ሁሉ ቅርስ ለምሳሌ በጎንደር ህንጻዎች ውስጥ እንደ ቀልድ በአግባቡ ሳንጠቀምባቸው በመጋዘን ተቆልፎባቸው ከነበሩት ነገር ግን ንጉሶቹ በወቅቱ በጊዜያቸው አሁን library እንደምንለው ቤተመዘክር ማስታወስ ይበቃል።
‹ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን› ለቀልድ የተባለ አይደለም። የግዕዝ ፊደላት አስቀምጠውት ነበር ግን አልተማርንበትም ጥንታዊነታቸው ብቻ ለሀይማኖት ብቻ የሚያገለግሉ የሚመስለን ካለን ተሳስተናል። እነ ፍትሃ ነገስት ፣ ስንክሳር የእጸዋት ጥናትን የሚያስተምሩ ወይንም አሁን በባዮሎጂ Taxonomy , Botany እያልን የምንማራቸው ከግዕዝ library የተወሰዱ ናቸው።
ስለዚህ ማርክስ ጋርቬይ እንዳለው ‹‹ ታሪኩን ምንጩን እና ባህሉን የማያውቅ ህዝብ ስር እንደሌለው ዛፍ ነውና ›› የእነ መጋቢ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰን አስተምህሮን በትክክል እናጥናውና እንመርምረው። ለዚህ ማሳያ እና ምስክር የሚሆነን የእነ መጋቢ ሀዲስ ዶክተር ሮዳስ እና ዶክተር ጌትነት የጻፉዋቸው መጸሀፍት እና ለረዥም ጊዜ በተለያዩ ቻናሎች ያስተማሩትን ረቂቅ ኢትዮጵያዊ የእውቀት መነሻዎች እና ሚስጥሮች በአሜሪካም በአውሮፓም የምናያቸው ረቂቅ ፊልሞች መነሻዎች እና ሚስጥሮች የሀበሻ ምድር ኢትዮጵያ ነች። ሌላው ቀርቶ ታችአምና ያሳየን ግርምት ያጫረብን Eclipse በላስታ በወርሃ ሰኔ እንደሚታይ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ተተንብዮ በግዕዝ በብራናዎቻችን ተመዝግቦ የነበረ ነው። ይህን አውሮፓውያን በ16ኛው ክ/ዘመን ከወሰዱት የተማሩት እና ያወቁት ነው። አሁን ያሉት የቀድሞይቱ USSR ወይም Leningrad ውስጥ አዲስ አበባ ያለውን የመርካቶን ያህል የገዘፈ 12 የኦርቶዶክስ ገዳማት በአንድ ግቢ ውስጥ የሰፈነበት ባለው ግዙፍ library ውስጥ በክብር ተቀምጠው እውቁን አንጋፋው የ Leningrad University የምርምር ማዕከል ውስጥ ብራናዎቻችን ይገኛሉ። የሩሲያ ፕሮፌሰሮች እንደ እኛ ሀገር ቀሳውስቶች ቅኔ በግዕዝ ይዘርፋሉ። እኛ ግን አምና 2012 የቡሄ በዓል በደብረታቦር ከተማ ሲከበር እና በተጓዳኝ የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ መምህራን PHD ያለቸው በግዕዝ ቅኔ ሲዘርፉ ሳለ ቡሄ በዓል ምንንት ከእየሩሳሌም ጋር እያቀናጁ ትምህርት ሲሰጡ ዩኒቨርስቲው ወደ አብነት ት/ቤት የተቀየረ መስሎን በዝናኛው የአማራ ቴሌቪዥን አሚኮ ሲተላለፍ ከቁብ አልቆጠርነውም። ምክኒያቱም የአብነት ት/ቤትን ጥቅም እና ከፍታ አናውቅምና ነው።
በዚያን እለት አዲስ አበባ ያሉት የሩሲያ አምባሳደር ደብረታቦር ከተማ አንድ ወዳጃቸውን ለማየት መጥተው ሄደው ነበርና ደብረታቦር ተወልዶ አማርኛውን ጥርት ባለ የጎንደርኛ ዘየ አሳምሮ ከሚናገረው ነጩ የኖርዌይ ተወላጅ አዛውንት ግን እኔ የጠራሁ ጎንደሬ ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚለው ወዳጃቸው ጋር ስለሚዘረፈው ቅኔ መግለጫ ለተማሩ ሀበሾች ያስተረጉሙ ነበር። የተገላቢጦሽ ይህ ነው እንግዲህ ኢትዮጵያ ‹ ሐሊብ › ናቸው ሲባል። የጥንት ጥበብም የአሁኑ ዘመናዊ science ወይም civilization የሚባለውን ሁሉንም ጠንቅቃ ታውቃለች ማለታችን። ‹‹ ምድር ቀደምት ›› መበሏ እኮ የቀልድ አይደልም። Dagu communication የአፋር ህዝብ የጥንት ሀብት ነው ሰክኖ መናገር እና መደማመጥ የአፋር ባህል ነው። የአሁን ተጨባጭ ችግራችንኮ አለመደማመጥ ነው። ይህን በየቤታችን በየቀያችን እያየነው ነው እና ችግር ፈቺ ሀሳብ እንዴት ይፈጠር ? እናም ከንጉስ አሊሚራህ ስለ ሰንደቅአላማ የተነጋረው ድንቅ ንግግር እንማር ብዙ ያልተማርነው አለ።
በግስላይቱ እቴጌ ጣይቱ ጊዜ በአንቀጽ 17 ውጫሌው የተመከረና ከ5 ዓመታት በላይ ጣሊያኖች እና ግብጾች በመሪያቸው የበርሊን ጉባዔ እንደ አሁኗ አሜሪካን ብዙ ተለፍቶበት በአድዋ ድል ቅስማቸው አስተሳሰባቸው እንዲሰበር ተደርገዋል። ግና ከጣይቱ ከእምየ ሚኒሊክ አመራር አልተማርንም። አሁን ገና ከሐምሌ 14ቱ ዳግም የውሀ ሙሊታችን በኋላ ልንማር እየተውተረተርን እንገኛለን። ግን ጥሩ ጅማሮ ነው ! ማን ይሆን ትልቅ ሰው ? ጨዋው ህዝብ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እየፈለገ ነበር ዶክተር አብይን አግኝቷል ዶክተር አብይ ካየናቸው መሪዎቻችን ህዝብን ምሁራንን በንግግሬ ተሳስቼያለሁ ብሎ ይቅርታ የጠየቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው።ደራሲ እንደመሆኑ መጠን ከህዝብ ከምሁራን በትክክል ስህተት ሲነገረው ምንግዜም ለመማር የተዘጋጀ አዕምሮ አለው።
በምርጫው ኢትዮጵያ አሸንፋለች! በአድዋ ድል የግዳቸውን ድሉን ፈረንጆች እንደተቀበሉት ቂም ለዘለዓለም እንደቋጠሩት አሁንም ኢትዮጵያ በአሸነፈችው ምርጫ እየተንጨረጨሩ ገና አልተዋጠላቸውም። ነገር ግን ግብጾችም ቀዝቃዛ በቀላቸውን ሌሎች አጋሮቻቸውም ዓይናቸውን ሳያፍሩ በጨው አጥበው ለጁንታው አለአግባብ ይብሰከሰካሉ። ግን የኢትዮጵያ የአሸናፊነት መንፈስ እንደገና እየጎመራ እያበበ ስለሆነ ድል ያደርጋቸዋል።
ምዕራባዊያን የተልፈሰፈሰና በቅዠት ካሉት መንጋ ልበ ቢስ ጁንታዎች ቢፈልጉም ታዛዥ ውሻ ማግኘት ከብዷቸዋል አሁንም እንደነሊቢያ ሀገር ካፈረሱ በኋላ ጥፋቱ የእኛ ፖሊሲ ነው ለማለት እየተዘጋጁ ነው።ግን ውሻውን ማንገስ አቃታቸው። በዩጎዝላቪያ እንዳደረጉት ውሸታም ግን አሳፋሪውን የእናት ጡት ነካሽ ጄኔራል ጻድቃን ገ/ተንሳይን ቢክቡትም ድሮ አስተምረውት ከጥልቁ ቆሼ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ አውጥተው በ recycling ሊያጥቡት ቢሞክሩም አልተቻላቸውም። የድሃ እንባ በተለይ የጨዋ ህዝብ እንባ እና እርግማን የማይካድራው ሰቆቃ በጥቅምት 24 እልቂት ከሲኦል ያመለጠ ሰይጣንነቱን አውሬነቱን እንጂ ሌላ ነገር አያሳብቅም።
እንደ ማጠቃለያ እና መፍትሄ ሀሳቦች – ፡
የ2013 የሐምሌ 14 የመጀመሪያው የግድባችን ሙሊት እና የ2013ቱ ዳግማይ ሙሊታን ብዙ የናፈቅነውን ኢትዮጵያዊነታችን ና አንድነታችን በብርሃን ፍጥነት ጠላቶቻችንን እንደ ማዕበል ሀሳባቸውን ጉልበታቸውን ቄጤማ አድርጎ እያወዛወዘ የእኛን ብሩህ ተስፋ እያፈካው ነው። የኢትዮጵያን ‹ሐሊብ› መሆን በተግባር እያሳየን ነው። እባክህ ወጣት ድሮ ቀረ ምን ልጅ አለና ሀገራቸውን የማይወዱ እያልን ሳናስተምር ስናሽሟጥጥ እነሱ ግን በራሳቸው ተነሳሽነት ወጣቶችን ከቴወድሮስ በደማቸው የተዛወረውን patriotism ከእነ ጀግናው በላይ የወረሱትን እልኸኝነትና አይበገሬነት ከወልይት ግንባር በራያ አድርገው የምድረ ቀደምትዋ የአፋር ህዝብ ጋር በመቀናጀት እያርበደበዱ በ50 ዓመታት የተዘራውን መርዝ ያፈራውን አረም እየጠራረጉት ነው።የድልቀንም ሩቅ አይደለም።
በመምህር አሸብር ውርጌሳ – ከደቡብ ወሎ ሐይቅ
አዲስ ዘመን ነሐሴ 25/2013