
አዲስ አበባ ፦ አሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ በአደባባይ ህብረት ፈጥረናል ማለታቸው ምንም አይነት የፖለቲካ ዓላማ እና መርህ እንደሌላቸው በተጨባጭ ያሳየ መሆኑን የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበርና የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አስታወቁ። ቡድኖቹ ቆምንለት ለሚሏቸውህዝቦች ደንታ ቢስ መሆናቸውን ያመላከተ መሆኑን ገለጹ።
ዶክተር አረጋዊ በርሄ በአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ መካከል የተፈጠረውን ህብረት አስመልክተው በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ ሁለቱም አሸባሪ ቡድኖች ምንም የሚወክሉት ህዝብ የሌላቸው ፣ ለሚሰሩት ሥራ ምንም አይነት የፖለቲካ ዓላማ እና መርህ የሌላቸው ናቸው። ህዝቦች ደንታ ቢስ መሆናቸውን ያመላከተ መሆኑን ገለጹ።
ዶክተር አረጋዊ በርሄ በአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ መካከል የተፈጠረውን ህብረት አስመልክተው በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ ሁለቱም አሸባሪ ቡድኖች ምንም የሚወክሉት ህዝብ የሌላቸው ፣ ለሚሰሩት ሥራ ምንም አይነት የፖለቲካ ዓላማ እና መርህ የሌላቸው ናቸው።
ቀደም ባለው ወቅት አንዱ አዳኝ ሌላው ታዳኝ ሆነው ይንቀሳቀሱ እንደነበር ያመለከቱት ዶክተር አረጋዊ ፣ አሁን ላይ ህብረት የፈጠሩት ሀገር ለማፍረስ ካላቸው ጽኑ ፍላጎት እንደሆነ አስታውቀዋል።
አሸባሪ ቡድኖቹ እንደ አይጥና ድመት የሚጠባበቁ አንዱ አንዱን ጠላት አድርጎ የኖረ በተለይም አሸባሪው ህወሓት በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ሽብርተኛ ብሎ ፈርጆት ሲያሳድደው ደጋፊዎቹን በገፍ ሲያስርና ሲያሰቃይ እንደነበር ይታወሳል ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፣ አሁን ላይ ይህንን ሁሉ ነገር ወደጎን በማለትና አገር የማፍረስ ፍላጎታቸውን ከግብ ለማድረስ ተጣመርን ማለታቸው አሳፋሪ ብሎም ቆምንለት የሚሉትን ህዝብ የናቀ ተግባር ነው ብለዋል።
ሸኔ ላለፉት በርካታ ዓመታት አሸባሪው ህወሓት የሰራኝን ሥራ ለማወራረድ ገና ብዙ ይቀረኛል እያለ ሲፎክር እንደነበር ያመለከቱት ዶክተር አረጋዊ፣ አሁን ደግሞ አገር የማፍረስ ራዕይውን ለማሳካት ተጣምሯል፤ ይህም እስከ ዛሬም ጫካ ኖሮ ህልሙን ማሳካት ሳይችል የቀረው በዚህ ልክስክስ ባህርይው መሆኑን እንደሚያሳ አስታውቀዋል።
ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች ቆምንለት ለሚሉት ህዝብ ደንታ የሌላቸው ናቸው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፣ እነሱ የሚያስቡት አልያም የሚፈልጉት ስልጣንና ስልጣን እንዲሁም ጥቅም ብቻ ነው። ለዚህ ማሳያው ደግሞ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ህጻናትን ለዛሬ ስግብግብ ፍላጎታቸው እሳት ውስጥ መማገዳቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
ከራሳቸው ጥቅምና የስልጣን ጥማት ውጪ ለአገርና ለህዝብ የማይቆሙ ቡድኖች በሆነ ወቅት ላይ አንዲት የምታስማማቸውን ነገር ከውስጥ ለይተው በማውጣት ለጊዜው መስማማት ላይ ለመድረስ ወደኋላ አይሉም። ይህ ሁኔታም የስግብግቦች የተለመደ አካሄድ ነው ብለዋል።
እንደነዚህ አይነት ቡድኖች ጥቅመኛና የራሳቸውን ምቾት ብቻ የሚያስቀድሙ ከመሆናቸው አንጻር አንዳንድ ጊዜ ሲሄዱበት ወይም ሲከተሉት የነበረውን አካሄድ ሁሉ በመርሳትና እንዳልነበር በመቁጠር ለጥቅማቸው ሲሉ ይጣመራሉ ፤ አሁንም እየታየ ያለው ይህ ነው፤ ይሁን እንጂ ተመልሰው በመወነጃጀልና አንዱ የአንዱ ጠላት በመሆን ሲሰለፉ የምናይበትር ጊዜ ሩቅ እንደማሆን አመልክተዋል።
ሁለቱም ዓላማቸው መገንጠልና አገርን ማፍረስ ነው፤ ይህ ሁኔታ ደግሞ በተለይም ደጋፊዎቻቸው እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ በአግባቡ ሊረዳው ይገባል ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ አሸባሪው ሸኔ ኦሮሞ ተበድሏል ተጠቃሚ አልሆነም ብሎ ነፍጥ አንግቦ ጫካ ከገባ አርባ ዓመት ይበልጠዋል ግን ደግሞ የኦሮሞን ህዝብ ከመግደል እንዲንገላታ ከማድረግ ባለፈ ምንም የሰራው ሥራ የለም ብለዋል።
በተመሳሳይ አሸባሪው ህወሓትም ቢሆን ህዝቤ በሚለው የትግራይ ህዝብ ይነግድ እንጂ ህዝቡ ከተረጂነት እንዲወጣ አላደረገም፤ በዚህ ዘመን እንኳን የሚጠጣው ንጹህ ውሃ የለውም ። ይህ የሚያሳየው ሁለቱም ቡድኖች ለራሳቸውና ለጥቅም አጋሮቻቸው የቆሙ የእኩይ ምግባር ባለቤቶች መሆናቸውን እንደሆነ አብራርተዋል።
አሁን ተጣመሩ አልተጣመሩ የሚያመጡት ለውጥ የለም ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ ምክንያቱም ህዝቡ በተለይም ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያዊነቱን እያስቀደመ አንድ ወደ መሆን እየመጣ ነው፤ ስለዚህ እነዚህ ሃይላት የጀመሩት አካሄድ የማይሆን ከመሆኑም በላይ በግሌ እንደማይሳካላቸው እርግጠኛ ነኝ ብለዋል።
እፀገነት አክሊሉ
አዲስ ዘመን ነሃሴ 10/2013