ዋቅሹም ፍቃዱ
አዲስ አበባ፡- ከአየር ንብረት ጋር ተያይዞ በዓይነቱ ከባድ የሆነው በሱዳን የተከሰተው የጎፍር መጥለቅለቅ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝቦቿን ለወራት ያህል ከቀዬአቸው አፈናቅሏል። ረሃብና በሽታ በአገሪቱ እየተስፋፋ በመምጣቱ አገሪቱ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆኗ አልጀዚራ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የውሃ መጠን ከሰኔ ወር ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በተከሰተ ጎርፍ በአንዳንድ አከባቢ ማሳ ላይ ያሉ ሰብሎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢ በጎርፍ ክፉኛ የተመታው የጆንግሌይ ግዛት በጎበኘበት ወቅት የአከባቢው ህብረተሰብ መፈናቀሉን፣ የተፈናቀለውም ህዝብ የምግብ አቅርቦት ስለሌለው የሚላስ የሚቀመስ ነገር ፊላጎ ጥልቅ ውሃ ውስጥ ሲዋኝ ማየቱን አልጀዚራ ያትታል። በአከባቢው ወባና የተቅማጥ ወረርሽኝ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነም ገልጸዋል።
በጎርፉ ምክንያት ቤታቸው የወደመና ከቀዬአቸው ተፈናቅለው አንድ የአካባቢው የመጀሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ የዘጠኝ ልጆች እናት የሆኑት ኛኮል ፕኒ ለአልጀዚራ በሰጡት አስተያየት፣ አሁን በተጠለሉበት አካባቢ ምግብ እንደሌለ፣ ምግብ አልፎ አልፎ የሚያገኙት ከሰብዓዊ ህርዳታ ድርጅቶች ብቻ ነው።
ያም በቂ ስላልሆነ ማገዶ ለቅመው በመሸጥም የዕለት ጎሮሮ ለማግኘትም ይገደዳሉ።ንጹ የመጠጥ ውሃ በአካባቢው ባመኖሩ ልጆቻቸው የደፈረሰ የጎርፍ ውሃ በመጠጣት ለበሸታ ተዳርገዋል። ለመታከም እንኳ በአከባቢው ጤና ጣቢያ ወይም ጤና ኬላ እንደሌለ አልጀዚራ በዘገባው ይገልጻል።
ዘገባው፣ ናንኩን ዳሆል የተባሉት እናት በህዳር ወር በአስቸገሪ ሁኔታ ውስጥ 7ኛው ልጃቸውን በሰላም መገላገላቸውን ጠቁሞ፣እኚህ እናት በአሁኑ ወቅት በጣም ከስተውና ጠወልገው እንዳሉ፣ አንዱ ጡታቸው በማበጡና በምግብ እጦት ምክንያት የተወለደው ህጻን በሞትና በህይወት መካከል እንዳለ ያትታል።
አከባቢው በጎርፍ በመጎዳቱ ምክንያት ሰዎች ውሃም ሆነ ምግብ ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ ጭቃው እንቅስቃሴያቸውን ከባድ ያደርገዋል። በአጠቃላይ በአከባቢው ያለው ኑሮ እጅግ የተመሰቃቀለና በዘርፈ ብዙ ችግሮች የተወሳሰበ በመሆኑ ሞትና ህይወት ገና ያልተለዩ ጉዳዮች ሆነዋል።
በዘገባው መሰረት፣ ህዝቡ በአንድ አካባቢ በብዛት ተጠልለው ስላሉ መታመማቸውን እንጂ በየትኛው በሽታ እንደተያዙ በቅጡ አያውቁም። ስለ ኮሮና ወረርሽኝም ግንዛቤ የላቸውም። ከበሽታው ይልቅ የጎርፉ አሁንም በድንገት ተከስቶ ልጆቻቸውን ወስዶ እንዳይሄድ ስጋት አላቸው። እንደሚረዱአቸው ተስፋ ያደረጉት የአገሪቱ መንግስትም፣ ተስፋ እንዳደረጉት አልሆነላቸውም።
በአደጋ ጊዜ እየደረሱለት አይደለም፣ የምግብና የመድሃኒት ጉዳይም ረስተዋል። ሰዎቹ በህይወት ለመቆየት ያላቸውን ሁሉ እንደተጠቀሙ፣ ከጎርፍ የተረፉት ከብቶቻቸውንም ሽጠው ጨርሰዋል። አሁንም ግን ጎርፉ አሳሳቢ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል።
አዲስ ዘመን ታህሳስ 25/2013