በኃይሉ አበራ
እ.ኤ.አ ከ1970 የሚጀምረው እና ግማሽ ምዕተ ዓመትን የዘለቀው የኢትዮጵያና የቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሁለቱ ሀገራት ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የቀየ ትስስር ከጥንካሬ ወደ ጥንካሬ እያሳደገው ስለመሆኑ ይነገራል።
ለዚህም አያሌ ማሳያዎችን በማንሳት የሚገልጹም አሉ። ከሰሞኑም ሲል ቻይና ዶት ኦርግ ዶት ሲኤን የተባለ የመረጃ ምንጭ ይሄንኑ የሁለቱ አገሮች ትብብር ዘርፈ ብዙ ብቻ ሳይሆን እየጠበቀ ስለመሄዱ ነው የገለጸው።
እንደ ዘገባው፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያና ቻይና ዘላቂ ስትራቴጂካዊ የጋራ ትብብራቸውን በመገንባት ሁለቱም ሀገራት ፖለቲካዊ የጋራ መተማመንን በማጠናክረው በተለያዩ ዘርፎችም ፍሬያማ የጋራ ውጤቶችን አስመዝግበዋል። ከሰሞኑም በወቅታዊ እና በወደፊት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነቶች ዙሪያ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር በቤጂንግ ቻይና-አፍሪካ ውይይት ተካሂዷል።
አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በውይይቱ እንዳሉት፣ ባለፉት 50 ዓመታት ኢትዮጵያ በበርካታ ዘርፎች ሁለቱ ሀገራት ግንኙነቶች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ የሀገራቱ የጋራ ጉዳዮች ተባባሪ ነበረች። ለዚህም አንዱ ማሳያ በፖለቲካ ተሳትፎ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት በጠንካራ ፖለቲካዊ መተማመን እና ከፍተኛ የተሳትፎ ደረጃ የነበራቸው መሆኑ የዚህ መገለጫ ባህሪ ነው።
እ.ኤ.አ በ2017 ጀምሮም ኢትዮጵያና ቻይና የዘርፈብዙ ስትራቴጂካዊ አጋሮች ሆነዋል። እንዲሁም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት፣ የአየር ጸባይ ጉዳዮች፣ ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና በተባበሩት መንግስታት የማሻሻያ ፕሮግራሞች በትብብር ስተሰራ ቆይታለች ብለዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቻይና በኢትዮጵያ የሰው ሀብት እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገች መሆኑን ያስታወሱት አምባሳደር ተሾመ፤ በቻይና ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን በመጥቀስ አሁንም ይህ ቁጥር እየጨመረና እያደገ እንደሚመጣ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት በትራንስፖርትና ቴክኖሎጂ የጋራ ትብብር እያደረጉ መሆኑን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በሀገሪቷ ታሪክ የመጀመሪያዋን
ወዳጆቼ አባት ልጁን ያማ ጀመር እንዴ እንዳትሉኝ እንጂ ልጄ የሰራችልኝን ሥራ ላወጋችሁ ብቅ ብያለሁ። በደኅና ቀን ፈጣሪ የሰጠኝ በቆዳዋ ውብ የሆነች ልጅ አለችኝ። እናም ቆንጆ በመሆኗ ከሰው ሁሉ ለማስበለጥ ያላደረግኩት ጥረት አልነበረም።
ምን አለፋችሁ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ብሎ እርምጃ ሲወስድ ከነበረው ልፋት በላይ ደክሜያለሁ። ልጄን በአካል ማቆንጀት ብቻ ሳይሆን አእምሮዋንም ለማስከበር በ”ቦጠሊቃ” ቋንቋ እርምጃ ወስጃለሁ።
በዘመድ አዝማድ አፈላልጌ በአፋልጉኝ ጭንቅ ጥብብ ብዬ ትብለጥ፣ በለጠች፣ በለጡ የሚል ስም ከዶክትሬት ዲግሪ ባልተናነሰ መልኩ አንስቼ ድፍት አደረግኩባት። ታዲያ ኃላፊ አግዳሚው፤ እውነትም በለጡ! እያሉ ሲያሞጋግሷት እኔ የእሷ አባት በመሆኔ ኩራቴ ገደብ አልነበረውም። ጎረቤቶቼ እንኳን በስሜ ሲጠሩኝ ኸረ ምን በወጣኝ የበለጡ አባት እያላችሁ ጥሩኝ እንጂ እያልኩኝ እነዘንዛቸው ጀመር።
የሆነ ቀን ነው፤ በለጡ “ክሬዚ ዴይ” የሚባል በአል /በአል ነው ብላለች/ለማክበር ከጓደኞቿ ጋር ራቅ ወዳለ ቦታ በጠዋት ተነስታ ሄዳለች። አይ የኛ ነገር አሁን እንደው ካልጠፋ ቀን እንዴት ክሬዚ ዴይ ተብሎ የእብዶች ቀን ይከበራል? በእርግጥ በዚህ ዘመን ሁሉም ሰው አብዷል።
ከቀኑ 7 ሰዓት ሲሆን ገመድ አልባው የቤታችን ስልክ ጭርር አለ። አንስቼው ሃሎ ማን ልበል? አልኩ፤“ቡቹ እባላለሁ” እሺ ልጅ ቡችላ ማነው፤ ቡቺ ማለቴ ቡቹ ምን ልታዘዝ? “ኪኪን ፈልጌ ነው!” ደግሞ የማናት ኪኪ…? ተሳስተሃል ልጄ ኪኪ የምትባል ልጅም እቃም የለንም አልኩትና አሰናብቼ መጽሐፍ ቢጤ ላነብ ስል አሁንም ስልኳ ጠራች።
አሁንም ስልኩን አንስቼ ሃሎ! አልኩ፤ ደሞ ሌላ ሰው። ማን ልበል? አልኩ፤ “ሃይ ፒስ ነው፤ ጆቢራው እባላለሁ፤ ቲቲን ፈልጌ ነበር።” የሚል ጥያቄ ቀረበልኝ፤ ልጄ ቲቲ የምትባል የጎረቤት ውሻ እንጂ ልጅስ እዚህ ቤት የለችም አልኩና ንዴት ቢጤ ተሰምቶኝ ስልኩን ዘግቼ “ የሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች” እንዲሉ የኔው ጉድ መሆኑን አላወቅኩ።
ምነው የዘመኑ ስም አወጣጥ ግራ ገባውሳ አልኩ ለራሴ። በእርግጥ በኛም ጊዜ እኮ ስም አወጣጡ ለየቅል ነው። የማውቀው አንዱ ወዳጄ ስሙ ለታ ሲሆን፤ ልጆቹን በቀናት ሰይሟል። የመጀመሪያ ልጁ ስም ሰኞ (ሰኞ ለታ)፣ ቀጣዩ ማክሰኞ (ማክሰኞ ለታ)…እያለ ልጆቹ ከቀኖቹ ቁጥር ሲበልጡ ስምንተኛውን በቀደም አለው /በቀደም ለታ/ መሆኑ ነው እንግዲህ።
ይገርመል! ስም አወጣጥን ማን እንደኛ። አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት አንዳንድ ስሞች ግን ሲወጡ ያስገርማሉ። ለምሳሌ ደኅና አድርገህ በለው የሚል ስም ስትሰሙ ምን ትሉ ይሆን? አለ ደግሞ ስሙ አሸብር ሆኖ የልጆቹን ስም ሙሉ ቀን፣ ዘላላም እያለ የሚያወጣ። (ሙሉ ቀን አሸብር… ዘላለም አሸብር) በዚህ ጉዳይ ስብሰለሰል ቆይቼ ለሦስተኛ ጊዜ አሁንም ስልኩ ጠራ።
ዛሬስ ስልካችን ቴሌ ሆነሳ አልኩ፤ ሃሎ ከማለት ተቆጥቤም ማድመጥ ጀመረኩ። የአሁኑስ ባይወራ ይሻል ነበር። ጀምሬዋለሁና ላውጋችሁ። ደዋዩ ማን እንዳነሳ ሳያረጋግጥ “ የኔ ቆንጆ፣ የኔ ፍቅር፣ የኔ ማር፣ የኔ ስኳር፤ የኔ ጣፋጭ …ይላል። ”እንዴት እንደናፈቅሽኝ፣ ንፍቅፍቅ እንጂ ይሄንንና እዚህ የማልጠቅሳቸውን ቃላት እንደ ወራጅ ውሃ አፈሰሳቸው።
እኔ ስለ እርሱ በድንጋጤ እንደ ስልክ እንጨት ለአስር ደቂቃ ድርቅ ብዬ ቀረሁ፤“ እሱ ግን ቱቱዬ ምነው መልስ ስጪኝ እንጂ፤ ዝም አትበይ የኔ ቆንጆ! ናፍቀሽኛል እኮ” እያለ መቀባጠሩን ቀጠለ።
እኔ ከድንጋጤዬ እንደመንቃት ብዬ “ አንተ እንደ አባይ ወንዝ መገደብ ያስፈልግሃል፤ በል ስልኩን ዝጋውና ቱቱን ካለችበት ፈልጋት” ብዬ በጆሮው ላይ ዘጋሁበት፤ በሁኔታው እየተብሰለሰልኩ ሳለም ልጄ ክሬዚ ዴይ ቋ፣ ቀጭ…እያለች ተመለሰች።
ክሬዚ ዴይን ለማክበር የተቀባችው ቻፒስቲክ የሚበለው ነገር የጾም በየዓይነት የተበላበት ትሪ አስመስሏታል። እኔ ደግሞ በሁኔታዎች ተናድጄ ነበርና ፊት ነሰኋት። “ምነው አባዬ ሠላም አይደል እንዴ?” ስትል ጠየቀችኝ።
ኸረ ልጄ….ምን ሰላም አለ? የገዛ ስልካችን ጉድ ሲያሰማኝ ዋለ እኮ። አንዱ ቡቺ ነኝ ኪኪን ፈልጌ ነው፤ አንዱ ጆቢራው እባላለሁ ቲቲን ፈልጌ ነው፤ አንዱም እንዲሁ ቱቱ መስላኝ ነው፤ ኸረ የሱስ እንደው ጭራሽ ባይወራ ቢቀር ይሻላል።
ብቻ ምን ልበልሽ ሲያደክሙኝ ዋሉ እንጂ ብዬ የአፌን ሳልጨርሰው “ወይኔ በዳዲ ሞት ምን አይነት ቀን ነው? ሞባይሌ ቻርጅ ባይዘጋ ኖሮ ይሄ ሁሉ ችግር ባልተፈጠረ ነበር፤ ቲሽ ሲደብር” አለች። እንዴ ልጄ ምን በወጣሽ ያንቺ ሞባይል ቻርጅ ማለቅና የእነርሱ ስልክ መደወል ምን አገናኘው? ስላት “ አገናኝቶትማ ነው፤ ጓደኞቼ እኮ ናቸው። ሞባይሌ ስለተዘጋባቸው በቤት ስልክ የደወሉት።” አለችኝ።
ቆይ ቆይ ቆይ…. ልጄ! ጓደኞቼ ስትዪ አልገባኝም። ምን አይነት ጓደኛ? የሥራ ባልደረባ ማለትሽ ነው? ደግሞስ ኪኪ. ቲቲ፣ ቱቱ፣…ብሎ ስም ማን አወጣልሽና? እኔ አባትሽ በደኅና ቀን ከሰው ሁሉ ያስበለጥኩሽ መስሎኝ በለጡ ብዬ አይደል እንዴ ያወጣሁልሽ? ታዲያ አሁን ምነው ስመ ብዙ ሆንሽሳ ብዬ ብጠይቃት ምንም ሳታፍርና ሳትፈራ “ይኸውልህ ዳዲ የዘመኑ ወንዶች በፍቅር እንደ ቻይና እቃ አይበረክቱም፤ ስለዚህ በየጊዜው ከአዳዲስ ወንዶች ጋር ስለምተዋወቅ ትክክለኛ ስሜን አልነግራቸውም። ለዚህ ነው ስመ ብዙ የሆንኩት። ደግሞ ቲቲ፣ ሊሊ፣ ፊፊ…ብዬ ካልተናገርኩ በለጡ የፋራ ስም ነው ይሉኛል” ብላ ቅስሜን ስብር አደረገችው።
ለሦስት ሰዓት ስልኳ ቢዘጋ ሦስት ወንዶች በቤታችን ስልክ ከደወሉ ለአስራ አንድ ሰዓት ስልኳ ቢዘጋማ አስራ አንድ ሰዎች ስልክ መደወል ብቻ ሳይሆን ቤታችን ድረስ መጥተው አስራ አንድ ቦታ እንደሚቆራርጡኝ አሰብኩት። ይገርማል፣ ያሳዝናል፣ ያሳፍራል! አንቺን ብሎ በለጡ! ይልቅ ስምሽን ከምትቀያይሪ ምናለበት ምግባርሽን ብትቀይሪ? የሚገርመው ነገር ራሳችን ታምነን ሳይሆን ሰዎች እንዲታመኑ መፈለጋችን ነው።
እኔምለው እኛ በአንዱ ሳንበረክት እንዴት ሌላው እኛ ላይ ሊበረክት ይችላል? እኛ ሳንታመን እንዴት ታማኝ ልናገኝ እንችላለን? እኛ ተፈቃሪ ሳንሆን እንዴት አፍቃሪ ልናገኝ እንችላለን? ጎበዝ ወንድ የራሱን ሄዋን ሊያገኝ የሚችለው፣ ሴቷም የራሷን አዳም ልታገኝ የምትችለው ላጤዎች በሚለው የፌስ ቡክ ግሩፕ ላይ አይደለም።
ብዙ ወዳጅ ስላፈራን ከብዙ ሰዎች ጋር ስለተዋወቅን፣ ብዙ ሰዎች ስለቀረቡን እኛም ስለቀረብን አይደለም የኛን ፍቅር ልናገኝ የምንችለው። ፍቅር አንድ እንጂ ሁለት አይደለም። ከአስሩ ጋር ስንቅበዘበዝ ወይ ለሥጋችን ወይ ለነፍሳችን ሳንሆን በሞት ተጠርተን እንሄዳለን።
ሳተላይት ያመጠቀችው በተጨባጭም በቻይና የስፔስ አካዳሚ ድጋፍ ነው ብለዋል።እንዲሁም የኢትዮጵያና የቻይና ጠንካራ የአቪዬሽን ትብብር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁንም በሳምንት 40 ያህል በረራዎችን ከቻይና ከተሞች ወደ አፍሪካ በማካሄድ በአገናኝነት እየሰራ የሚገኝ የአፍሪካ ዋነኛ አየር መንገድ ነው።
ይህም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የቻይና ቱሪስቶችን ቁጥር እንደሚያሳድገው ይጠበቃል። ወደ ፊትም በቻይና ድጋፍ ላይ የተመረቱ ውጤቶች በኢትዮጵያ እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል።
አምባሳደር ተሾመ፣ በኢትዮጵያ ያለው የቻይና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል። ይኸውም የኢትዮጵያን የኤክስፖርት እና የውጭ ምንዛሪ አሳድጓል፤ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እገዛ አድርጓል፤ በመሆኑም ከቻይና ጋር በጥምረት መስራቱ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ስለሚያግዝ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ኢትዮጵያም በቀጣይ አስር ዓመታት ቴክኖሎጂ በሚፈልጉ ኤሌክትሮኒክስ ንግድ (ኢ-ኮሜርስ) እና ኦንላይን ንግዶች ከቻይና ጋር በትብብር ለመስራት ትፈልጋለች። እንዲሁም ከቻይና ጋር የሚደረጉ የንግድ ግንኙነቶችን በማሳደግ እና በንግድ ዘርፍ ያሉ ልዩነቶችን ለማሻሻል ይሰራል። ቡና እና በመሳሰሉት የኢትዮጵያ ምርቶች እሴት በማከል በከፊል እና በሙሉ የተዘጋጁ ምርቶችን ለቻይና ደንበኞች የማቅረብ ፍላጎት መኖሩንም ጠቁመዋል።
አምባሳደር ተሾመ እንዳብራሩት፤ ቻይና አንድ ሺህ 590 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ አሏት፤ ይህም ለበርካቶች የስራ እድል ፈጥሯል። በዚህ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክትም 300 ሺህ ያህል ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚ ሆነዋል። ይህም ቀጥተኛ ጠቀሜታ ነው።
በቻይና የተገነቡ መንገድ እና ባቡር የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶች በየዕለቱ አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድሎችን ፈጥረዋል፤ ይህም የወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች እንዲጨምሩ በማድረግ እገዛ እያደረገ ነው፤ ይህ በመሆኑ ደግሞ ኢኮኖሚያችንን የሚያግዝ ቀጥተኛ የውጭ ምንዛሪ አሳድጓል ብለዋል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ቻይና እና የአፍሪካ አገራት በችግር ጊዜ እርስ በእርሳቸው ተደጋግፈዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በወረርሽኙ ወቅት ከቻይና ባለሥልጣናት ጋር ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል። አየር መንገዱ ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለአውሮፓ እና ለላቲን አሜሪካ አገራት የህክምና መሳሪያዎች ዋና አቅራቢ ነበር ብለዋል።
ይህ ከንግድ ስራ በላይ የድርጅታዊ ማህበራዊ ሃላፊነትን የሚያሳይ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስትን የኢትዮጵያ አየር መንገድን እና ሰራተኞችን ማመስገን አለብን። እኛም እነዚህን ስራዎች እንዲቆሙ ትችት ደርሶብን ነበር፤ ነገር ግን ከቻይና ህዝብ እና መንግስት ጋር በአንድነት ቆመን ነበር ብለዋል።
እንዲሁም በዩሃን 300 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እንደነበሩና ሁሉም እዚያው አስፈላጊው ጥበቃ እንደተደረገላቸውና ማንም በበሽታው እንዳልተያዘም አስታውሰው፤ ወዳጅ ሀገሮች ሁል ጊዜ በደስታ ጊዜ እና በችግር ጊዜ አብረው ይቆማሉ። እኛ ያደረግነው ይህንን ነው ብለዋል።
በምላሹም የቻይና መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እና የመንግስት ዘርፍ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የህክምና መሳሪያዎች እና አቅርቦቶች ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ በማቅረብ ረገድ መሪ ነበሩ። ከቻይና የህክምና ባለሙያዎችን ኮቪድ-19 ድጋፍ ከተቀበሉ የመጀመሪያዎቹ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ እንደነበረችም አስታውሰዋል።
በመጨረሻም ከኮቪድ-19 በኋላ ከቻይና ጋር ያለው የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ እንደሚቀጥል ተስፋችን ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የንግድ ልውውጧን በማሳደግ የበለጠ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ትፈልጋለች። ተጨማሪ ምርቶችንም ወደ ቻይና ለመላክ ፍላጎት መኖሩን ጠቁመዋል። የቻይና የግል ዘርፍም በኢትዮጵያ የበለጠ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20/2013
አዲስ ዘመን ታኅሣሥ 20/2013