ወላጆች ለልጆቻቸው ፍቅር ለግሰው፣ በሥነ ምግባር ኮትኩተውና አስተምረው ማሳደግ አለባቸው። ልጆች ለተለያዩ ሱሶች እንዳይዳረጉ መከታተልና ጉዳቱን ማሳየት እንዲሁም ወላጆችም ሱሰኛ ባለመሆን አርአያ መሆን ይጠበቅባቸዋል። በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችም የሚመክሩት ይሄንኑ ነው።
የሱስና ሱሰኝነት ተጋላጭነት ቅነሳ ህክምናና መልሶ ማገገም ስልጠና ባለሙያ አቶ ኤሊያስ ካላዩ እንደሚሉት ማንኛውም ወላጅ በሥነ ምግባርና ከሱስ ነፃ የሆኑ ልጆችን ወልዶ ለማሳደግ በምንም አይነት መልኩ ወላጆች የሱስ ተጋላጭ መሆን የለባቸውም። ሱስ ተጋላጭ ከሆነ ቤተሰብ ውስጥ የሚወለዱ ልጆች ከፅንስ ጀምሮ ተጎጅዎች ናቸው። ወላጆች ከልጆቻቸው ተደብቀው የሚጠቀሙ
ቢሆንም እንኳን ጉዳቱ አይቀርም። ልጆች በሚያዩት ነገር በቀላሉ ስለሚሳቡ የወላጆቻውን ተግባር በመከተል የሱስ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላል።
አቶ ኤልያስ እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለመደ የመጣው ህፃናት ባሉበት ቦታ መጠጣትና ማጨስ ነው። እፅ ተጠቃሚ ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ ልጆች ደግሞ ሱሰኛ የመሆን ዕድላቸው ከ50 እስከ 60 በመቶ ነው። ይህ ደግሞ ልጆችን የሱስ ተጋላጭ ከማድረግም በላይ ሕግ መጣስን እያስተማሯቸው ነው። ወላጆች ከእንዲህ አይነት ድርጊት መቆጠብ ካልቻሉ በልጆች አስተዳደግሞ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።
ልጆች ከምንናገረው በላይ ከተግባራችን ስለሚማረኩ ልጆች እንዳያደርጓቸው የምንፈልጋ ቸውን ነገሮች አለመተግበር ጥሩ ነው። ሕግን እያከበሩ በተግባር ማስተማር፤ ቤት ውስጥ እፆችን መጠቀም ሕገወጥ
መሆኑን ማስተማር፤ አስገዳጅ ነገር ካለ በመጠኑና በአግባቡ ከቤት እርቆ በመሄድ መጠቀምና ሲመለሱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። የአፋቸውና የልብሳቸው ጠረን የቆዩበትን የሚገልፅ አለመሆኑን እርግጠኛ መሆን አለባቸው። ካልሆነ ግን አደጋው ከፍተኛ ነው።
የተለያየ ነገር ሱስ በቤተሰብ ውስጥ የትዳር ግጭትና የኢኮኖሚ ማነስ ይፈጠራል። ይህ ደግሞ ልጆች ከቤት መውጣትና ባላሰቡት መንገድ የሱስ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ትምህርታቸውን ይቀንሳሉ፤ ወደ እርካታ የሚውስዳቸውን መንገድ በመፈለግ ለአደንዛዥ እፅ ይጋለጣሉ።
ወላጆች ልጆቻቸውን ከነዚህ ሁሉ ተፅዕኖዎች ነፃ አድርገው ማሳደግ ካልቻሉ አለመውድ፤ ከወለዱ ደግሞ ትልቅ ሀገራዊ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተገንዝበው በተገቢው መንገድ ማሳደግ እንዳለባቸው አቶ ኤልያስ ይመክራል። ልጆች የፈጣሪ ፀጋ ከመሆናቸውም በላይ ለሀገር ጠቃሚ አድርጎ ማሳደግ የወላጆች ትልቅ ሃላፊነት ነው። እፅ ተጠቃሚ የሆኑ ወላጆች የልጆቻቸውን የሱስ

ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ እንዲችሉ ከአሁን ጀምረው የህክምና ድጋፍ ማግኘት አለባቸው ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ።
አዲስ ዘመን ሰኔ 21/2012
ሞገስ ፀጋዬ