
ዜና ሐተታ
ክረምት አልፎ ብርሃን ሲወጣ በወርሐ መስከረም ዓለም ሁሉ ሊያየው የሚጓጓለት ሠርግ በኢትዮጵያውያን እየተደገሰ ነው። ይኸ ሠርግ ከዚህ በፊት ዓለም የሚያውቀውን ሠርግ ዓይነት አይደለም። ልዩ የሚያደርገውም ደጋሹ ግለሰብ ሳይሆን ኢትዮጵያ የምትባል ትልቅ እና ታሪካዊ ሀገር፤ ሙሽራውም ሰው ሳይሆን ትሩፋቱ ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ታላቅ ግድብ መሆኑ ነው።
ኢትዮጵያ ይህንን ታላቅ ሠርግ ስታሰናዳም ለግብዣው የጎረቤት እና የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትን በተለይም ግብፅና ሱዳንን በፍጹም አልዘነጋችም። ይልቁኑ በሀገሪቱ መሪ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኩል በዚሁ ታላቅ ድግስ እንዲታደሙ የአክብሮት ግብዣ አቅርባለች።
የመስከረሙ ሙሽራ ኢትዮጵያውያን ያለምንም የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የፆታ እና የዕድሜ ልዩነት በጋራ የቆሙለት እና በማህፀን ካለ ጽንስ እና በመቃብር ካለ አስከሬን በስተቀር ሁሉም የአቅሙን ያህል ከተረፈው ሳይሆን ከጉድለቱ አስተዋፅዖ ያደረገበት ታላቁ የዓባይ ግድብ ነው። አዎን ይህን ታላቅ ግድብ ያለምንም የውጭ ኃይሎች ድጋፍ ኢትዮጵያውያን ለ14 ዓመታት ተንከባክበው፤ የውስጥ እና የውጭ ተግዳሮቶችንም እመቤት ሽር ጉድ እያሉ ነው። ክረምቱ አልፎ ጨለማው ሲገፍ እና ብርሃን ሲወጣ ታላቁ የዓባይ ግድብም ለዓለም ሁሉ ብርሃን ሆኖና ተሞሽሮ ይገለጣል።
በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ማብራሪያ “የህዳሴ ግድብ አልቋል እናስመርቀዋለን፤ ከመመረቁ በፊት ብንረብሽ ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ፤ ነገር ግን ክረምቱ ሲያልቅ እናስመርቀዋለን። ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ያለኝ መልዕክት ለግብፅና ለሱዳን ህዳሴ በረከት ነው ያሉት።
የሚመጣው ልማትና ኢነርጂ ለሁሉም ሀገራት የሚተርፍም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በህዳሴ ግድብ ምክንያት የግብፅ አስዋን ግድብ አንድ ሊትር ውሃ
በፍቃዱ ከተማ
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም