
አሁን ያለንበት ጊዜ ብዙ ውጥንቅጥና ግሳንግስ የበዛበት ነው በዚህ በኩል የኑሮ ውድነት በሌላ በኩል ደግሞ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ብዙዎቻችንን ያስጨንቀናል በርግጥ ሕይወት ትግል የበዛባት ናት ያለ ብርቱ ትግል ህልውናን ማስቀጠል አይቻልም ያለ ውጣውረድ ኑሮን ማሸነፍ የማይታሰብ ነው እንዲህም ሆኖ በሕይወት ውስጥ ጭንቀትና መረበሽ ሊኖር ይችላል ይህም ተፈጥሯዊና ጤናማ ነው
ይሁን እንጂ ከሚፈለገው በላይ መጨነቅና መረበሽ ጤናማ አይደለም ሰዎች አብዝተው ሲጨነቁ ለከፋ የጤና ጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ የሕይወታቸውን መስመር ሊስቱና ያልተገባ ሁኔታ ውስጥ የመግባት እድላቸው በእጅጉ ሊሰፋ ይችላል የሕይወት መመሰቃቀል የሚፈጠረውም እዚህ ጋር ነው ስለዚህ ምንም እንኳን ኑሮ ፈታኝ ቢሆንም ሰዎች የኑሮን ፈተና ተጋፍጠውና ሕይወትን ቀለል አድርገው በማየት ሊኖሩ እንደሚገባ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ይመክራሉ
አብዛኛዎቻችን የምንኖረው ሕይወት ከሚያስፈልገው በላይ እጅግ የተወሳሰበ ነው የምንጨነቅባቸው በርካታ ነገሮች አናጣም እናም በእለት ተእለት ተግባራችን ውስጥ የበዛ ጭንቀትና መረበሽ ያጋጥመናል ይባስ ብሎ ደግሞ አብዛኛዎቻችን በጣም እስኪዘገይ ድረስ እንኳን ይህን ሁኔታ አናስተውለውም በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው አንድን ሰው በአማካይ ከ60 በላይ የሚያስጨንቁት ነገሮች ያሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ብዙ ክብደት የማይሰጣቸው ናቸው
ጭንቀት በሕይወት ላይ አንዳንድ ከባድ የጤና ችግሮች ሊያስከትል ይችላል ስለዚህ ጭንቀትን የሚያስከትሉ ነገሮችን በማስወገድ ሕይወትን እንዴት ማቅለል እንደሚቻል ከታች የተዘረዘሩ አስራ አንድ ጠቃሚ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረጉ አይከፋም
1ኛ. መርዛማ ሰዎችን ከሕይወት ውስጥ ማስወገድ
በርግጥም ሕይወታችንን ለማቅለልና ጭንቀትን ለማስወገድ ፍላጎቱ ካለን በዙሪያችን ያሉ መርዛማና እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ሰዎችን ማስወገድ ያስፈልጋል መርዛማ ሰዎች ሁሌም ቢሆን አሉታዊ አመለካከት ያላቸውና እኛን ዝቅ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው እንዲህ አይነቱ ባህሪይ ያላቸው ሰዎች ፈፅሞ ደስተኛ አይደሉም እነርሱ ደስተኛ የሚሆኑት ሌላውን ሰው ዝቅ በማድረግና በማንቋሸሽ ነው እናም እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ በአሉታዊ መልኩ የሚያወሩት ነገር አያጡም
በሕይወታችን ውስጥ እንደዚህ አይነት ሰዎች ካሉ ከውስጣችን ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው እውነት ከሆነ እንደነዚህ አይነት ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ እንዲገቡ መፍቀድ የለብንም ምክንያቱም ነጋ ጠባ ሕይወታችንን የሚረብሹት እነርሱ በመሆናቸው ነው ስለዚህ ለእንደነዚህ አይነት ሰዎች ቦታ መስጠቱ ተገቢ አይደለም።
2ኛ. በግል ምንም ነገር አንውሰድ
አብዛኛዎቹ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጫና የሚፈጥሩብን አብዛኛዎቹ ነገሮች በፍፁም ግላዊ አይደሉም ከዚህ ይልቅ ብዙውን ጊዜ ዓለምን እንዴት እንደምንመለከት ነፀብራቅ ናቸው ለምሳሌ አንድ ሰው ከፊት ለፊታችን ቢተፋ ወይም ገፍቶን ቢያልፍ ያ በእኛ ላይ የሚደርስ የግል ጥቃት አይደለም የተፋው ወይም ገፍቶ ያለፈው ሰው ጨዋነት የጎደለውና ለሌሎች ሰዎች ደንታ የሌለው ብቻ መሆኑን የሚያመለክት ብቻ ነው ስለዚህ በሕይወታችን እንደነዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ነገሮቹን በግል አንውሰደው፤ ትኩረትም አንስጠው ሕይወታችንንም እንዲረብሽ አንፍቀድ
3ኛ. ያለፈን ነገር መተው
ለብዙዎቻችን የጭንቀት መንስኤ ከሆኑት መካከል አንዱ ያለፈው ጊዚያችን ነው ብዙዎቻችን ከዚህ በፊት ስለተፈፀሙብን ነገሮች ማሰብን በቶሎ ማቆም አንችልም እናም በሀሳብ ዛሬን መኖር ትተን ያለፈውን እንኖራለን ይህ ልማድ ጭንቀተኛ ብሎም ደስተኛ እንዳንሆን ያደርገናል ይህን ለመቋቋም ጥሩው መንገድ ያለፉ ጉዳዮቻችንን መተው ያስፈልጋል ምክንያቱም ያለፈው አልፏልና ከእኛ ጋር የተሸከምናቸው ሁሉንም አሉታዊ ትውስታዎችንና ስቃዮችን መተው ይገባናል ሕይወትን በጥሩ መልኩ ለመቀጠልና እንደ አዲስ ለመጀመር ጊዜው አሁን ነው እናም ያለፈን ነገር ትተን የዛሬውና የወደፊቱ ላይ ብቻ እናተኩር
4ኛ. ሌሎች ሰዎች ምን ይሉኛል ማለትን/ይሉንታን/ ማቆም
የጭንቀትና የመረበሽ መንስኤ ከሆኑት ውስጥ ሌላኛውና ዋነኛው ሌሎች ሰዎች ስለኛ ስለሚያስቡት ነገር መጨነቅ ነው ብዙ ጊዜ አብዛኛውን ጉልበታችንን የምናጠፋው ሰዎች ስለእኛ ምን ሊናገሩ ወይም ሊያስቡ እንደሚችሉ በመጨነቅ ነው ይህ ደግሞ ጭንቀት ይበልጥ እንዲበረታብን ያደርጋል ይህንን ለመቋቋም በጣም ጥሪው መንገድ ሌሎች ሰዎች ስለሚያስቡት ነገር መጨነቅ ማቆም ወይም ቦታ አለመስጠት ነው የሚያስደስተንን ነገር ብቻ እናድርግ ሌላው ሰው ስለሚናገረው አልያም ስለሚያስበው ነገር አንጨነቅ
5ኛ. ውሎን ማሳመር
እስቲ ቢሯችንን ወይም የመኖሪያ ቤታችንን ክፍሎች እንመልከት ምን ያህል የተዝረከረከ ነው? ነገሮችን እየተጠቀምንባቸው ባይሆንም ነገር ግን አሁንም በእነርሱ ላይ ተንጠልጥለናል? መልሳችን ‹‹ብዙ›› ከሆነ ሕይወትን ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው በቢሯችን አልያም በመኖሪያ ቤት ክፍሎቻችን የማያስፈልጉና የማንጠቀምባቸው ነገሮችን እናስወገድ ይህም ሕይወታችንን በጣም ቀላል ያደርገዋል ሁሉም ነገር ንፁህና የተደራጀ ሲሆንና ይህን ስንመለከት በጣም ትንሽ ጭንቀት ይሰማናል ወይም ደግሞ ጭንቀታችን ከነአካቴው ይወገዳል ይህ ሕይወት በቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚያሳይ ምልክት ነው
6ኛ. እምቢ ማለትን እንማር
‹‹አይሆንም›› ወይም ‹‹እምቢ›› ማለትን አብዛኛዎቻችን አንፈልግም ሁልጊዜ መርዳት እንፈልጋለንና ሁልጊዜ አዎ እንጂ እምቢ ማለት አንፈልግም ነገር ግን ይህ ወደ ብዙ ጭንቀት ሊያመራን ይችላል ምክንያቱም ጊዚያችንን በአግባቡ መምራት ስለሚያስቸግረን ነው ይህን ለመቋቋም ከሁሉም የተሻለው መንገድ እምቢ ማለትን መማር ነው በተጣበበ ጊዜ ላይ ሆነን አንድ ሰው እርዳታ ፈልጎ ሲጠይቀን ልንረዳው እንደማንችል በግልፅ እንንገረው ይህ ማለት ግን ማንንም መርዳት የለብንም ማለት አይደለም ከዚህ ይልቅ እኛ ለመርዳት የተስማማንባቸውን ነገሮች የበለጠ መመረጥ ያስፈልገናል እንደማለት ነው
7ኛ. ቀናችንን በአወንታ እንጀምር
በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንደሚጠቁመው ቀናቸውን በአወንታዊ ሃሳቦች የሚጀምሩ ሰዎች በቀን ውስጥ ለጭንቀት የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው ስለዚህ ሕይወታችንን ማቅለል ከፈለግን ቀናችንን በአወንታዊ አስተሳሰብ መጀመር ይገባናል የምናመሰግንባቸውን ነገሮች እናስብና በሕይወታችን መልካም ነገሮች ላይ በማተኮር ጥቂት ደቂቃዎችን እናሳልፍ ይህ በቀሪው ውሏችን ጥሩ ነገር ያስቀምጥልናልና ለጭንቀት የመጋለጥ እድላችንን አነስተኛ ያደርገዋል እንዲሁም በሕይወታችን አወንታዊ ገፅታዎች ላይ የበለጠ ትኩረት እንስጥ ይህም በጥቃቅን ነገሮች ላይ የመጨነቅ እድላችንን ይቀንሳል
8ኛ. ለራስ ጊዜ እንስጥ
ሕይወታችንን ቀላል ለማድረግ ከፈለግን ለራሳችን ጊዜ መስጠት በጣም አስፈላጊ ነው ዘና ለማለትና ራሳችንን በጎ ባህሪያት መሙላት እንድንችል ለራሳችን የተወሰነ ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል ለራሳችን ጊዜ ካልሰጠን ውጥረትና ጭንቀት ውስጥ እንገባለን ስለዚህ በቀን መቁጠሪያችን ውስጥ ለራሳችን የተወሰነ ጊዜ ማቀድ ይኖርብናል ይህ ዘና ለማለትና ጭንቀትን ለማስወገድ የተወሰነ ጊዜ እንዲኖረን ያደርጋል ወደ ሥራ ስንመለስም ይበልጥ ውጤታማ ያደርገናል በእጃችን ላይ ባሉ ተግባራት ላይ እንድናተኩርም ያስችለናል
9ኛ. ሁልጊዜ እውነተኛ እንሁን
ታማኝነት በሕይወታችን ሊኖሩን ከሚገቡ በጣም አስፈላጊ እሴቶች ውስጥ ዋናውና በጣም አስፈላጊው ነው እውነተኛ ስንሆን ዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር ማለትም ከሥራ ባልደረቦቻችን፣ ከጓደኞቻችን፣ ከቤተሰባችንና ከሌሎችም ጋር መተማመን መፍጠር እንችላለን እናም ይህ ሕይወታችንን ይበልጡኑ ቀላል ያደርገዋል ታማኝ መሆን ማለት ግን ከሌሎች ሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ለራሳችን ታማኝ መሆንንም ይጨምራል ታማኝ ስንሆን ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ፍራቻ ፈፅሞ አይሰማንምና ሕይወታችንን ለማቅለል ያግዘናል
10ኛ. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እርዳታ እንጠይቅ
ብዙ ሰዎች አብዛኛውን ነገር በራሳቸው ለማድረግ ይሞክራሉ የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎችንም በራሳቸው ጥረት ብቻ ለመወጣት ይጥራሉ ነገር ግን ሁሉንም በራስ ብቻ መወጣት አይቻልም አንዳንዴ የሰው እገዛ የሚፈልጉና ከእኛ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ሊገጥሙን ይችላሉ አንዳንድ ጊዜ በዙሪያችን ካሉ ሰዎች እርዳታ መጠየቅ አለብን ከመጠን በላይ የመጨነቅ ስሜት ከተሰማን እርዳታ ለመጠየቅ አንፍራ፤ አናመንታ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች እኛን ለመርዳት በጣም ደስተኛ ይሆናሉ ይህ ደካማ እንደሆንን ወይም ነገሮችን በራሳችን አቅም ማስተናገድ እንደማንችል አያሳይም እርዳታ ስንጠይቅ በአካባቢያችን፣ በሥራችን፣ በቤታችን ያሉትን ሰዎች እንደምንተማመንባቸው እያሳየን ነው እነርሱም ይህን ተመሳሳይ ስሜት እንደሚጋሩት ይጠበቃል ይህ በዙሪያችን ላሉ ሰዎች የበለጠ ጠንካራ ግንኙነት ለመፍጠርም ያግዘናል
11ኛ. ጤናችንን መንከባከብ
በሥራና በሌሎች ግዴታዎች ስንጠመድ የጤናችንን ጉዳይ እንዘነጋለን ሆኖም ደስተኛና ቀላል ሕይወት መኖር ከፈለግን የጤናችንን ሁኔታ በየጊዜው መከታተልና እንክብካቤ ማድረግ ያስፈልጋል ጤነኛ ስንሆን የበለጠ ጉልበት እናገኛለንና የምንደሰትባቸውን በርካታ ነገሮችን ማድረግ እንችላለን እንደውም በበሽታ የመያዝ እድላችን አነስተኛ ይሆናል ስለዚህ ጤናማ ምግቦችን መመገብ፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግና በቂ እንቅልፍ በመተኛት ጤናችንን እየተንከባከብን ስለመሆኑ እናረጋግጥ ጤናማ ስንሆን ሕይወታችንን ቀላል ማድረግ እንችላለን
እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩት ሰዎች ራሳቸውን ከሚያስጨንቁ ጉዳዮች በማራቅ ቀለል ያለ ሕይወት ለመኖር የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮች ናቸው እነዚህ ምክሮች በአንዱ ላይ የሚሰሩ በሌላው ሰው ላይ ደግሞ የማይሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ አብዛኛዎቹ ግን ብዙሃኑን የሚጠቅሙ እንጂ የሚጎዱ አይደሉም እናም እርስዎ እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች ተግባራዊ ቢያደርጉ ያተርፋሉ እንጂ አይከስሩም ግድ የለም ይሞክሯቸው!!
አስናቀ ፀጋዬ
አዲስ ዘመን ሐምሌ 22/2015
buy priligy online safe Epub 2002 Jul 18