የሕግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ በትግራይ የተፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ለመቀልበስ መንግሥት መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፤ እያከናወነም ይገኛል። ይህንንም ተከትሎ ብዙዎች እንዳሰቡትና እንደተመኙት ብዙ ሰብአዊ ጥፋት ሳይፈጠር ሁኔታዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
እስከ ቅርብ ጊዜ ባለው ዕውነታ መንግሥት ከ70 ከመቶ የአስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታዎችን በማቅረብ ለትግራይ ሕዝብ ያለውን አጋርነት በተጨባጭ ማሳየት ችሏል። ችግሩን ለዘለቄታው ለመፍታትም የአስተዳደር መዋቅሮችን የማስተካከል አገልግሎቶችን የማስጀመር ከዚያም በላይ የክልሉን የግብርና ሥራ ለማስቀጠል ከፍ ያሉ ድጋፎችን
እያደረገ ይገኛል።
የግብርና ሚኒስቴር ሰሞኑን ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቀው፣ የፌዴራል መንግሥት በ2013 የመኸር እርሻ የትግራይ ክልል ለግብርና ሥራ ያስፈልገኛል ብሎ የቀረበውን የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መቶ በመቶ እንዲሁም ከፍላጎቱ በላይ ምርጥ ዘር እያቀረበ ነው፡፡
ለክልሉ እየቀረበ ያለው የግብርና ግብአቶች ግብርናውን በማስቀጠል ካላቸው ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ባለፈ አርሶ አደሩን ከእርዳታ ጠባቂነት በማላቀቅ የምግብ እህል ፍላጎቱን እንዲያሟላ በማድረግ ወደ ቀድሞ ሕይወቱ እንዲመለስ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል።
መንግሥት በአንድ በኩል የአስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታዎችን በማቅረብ፤ በሌላ በኩል በጁንታው የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት በክልሉ ሕይወት ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመለስ ከዚያም በላይ የትግራይ ሕዝብ የለውጡ ተጠቃሚ እንዲሆን እየሰራ ያለው ሥራ እልህ አስጨራሽና ፈታኝ እንደሆነ በተጨባጭ እየታየ ነው ፡፡
መንግሥት እነዚህን ችግሮች በቁርጠኝነት እየታገለ እያስመዘገበ ያለው ውጤት የሚበረታታና ጥልቅ እውቅና ሊሰጠው የሚገባ ነው። በቅርቡ ደግሞ አብዛኛውን ሰብአዊ ድጋፍ የማቅረብ ሥራ ለእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ሰጥቶ ሙሉ አቅሙን በመልሶ ግንባታው ላይ ለማዋል እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ግብርናውን ለማስቀጠል እያደረገ ያለው ጥረትየዚሁ አካል ነው።
መንግሥት የግብርና ግብአቶችን በወቅቱና በሚፈለገው ልክ በማቅረብ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው፡፡ ለብልህ «አይመክሩም ለአንባሳ አይመትሩም» እንደሚባለው ለአርሶ አደር ብዙ መምከር የሚያስፈልግ ባይሆንም፣ ከሁሉም በፊት የክልሉ አርሶ አደሮች ይህን የመንግሥት ቁርጠኛ እርምጃ በሚገባ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡ የቀረበላቸው ግብአት ትልቅ ሀብት መሆኑንና ብዙውን ችግራቸውን የሚፈታላቸው እንደሚሆን ተረድተው በሚገባ ሊጠቀሙበት ይገባል፡፡
የግብርና ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም አርሶ አደሩን ለመደገፍ በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ የመንግሥት ጥረት ፍሬያማ እንዲሆን በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ ለአርሶ አደሩ የሚያደርጉት ድጋፍ ከተለመደውም በላይ ሆን ይኖርበታል፡፡ አጋጣሚው በክልሉ ግብርና ላይ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ሊሆን እንደሚችል ጭምር
በማሰብ ጠንክረው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡
ግብአቱን አርሶ አደሩ ደጅ ማድረስ ቀጣዩ ትልቁ የቤት ሥራ ከመሆኑ አንጻር የህብረት ሥራ ማህበራት፣ የትራንስፖርት ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሙሉ አቅማቸው ከፍ ባለ ቁርጠኝነት ቀን ተሌት ሊሰሩ ይገባል፡፡
የፌዴራል መንግሥት ለክልሉ የግብር ሥራ ግብአት በማቅረብ እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት በሚገባ መጠቀም የክልሉን ግብርና ከስጋት ከመታደግም በላይ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳደግ መሆኑን በመገንዘብ መስራትም ያስፈልጋል፡፡
በአንዳንድ የዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ሆነ በአንዳንድ አካላት የክልሉ አርሶ አደር ወደ ግብርና ሥራው እንዳይገባ እየተደረገ ነው በሚል የሚናፈሱ አሉባልታዎችን በመቀልበስ ሂደት ውስጥ የመንግሥት እርምጃ ተጨባጭ አቅም ነው፡፡
አሁን የሚያስፈልገው ከአርሶ አደሩ ጎን በመሆን በሚያስፈልገው ሁሉ መርዳት ነው፤ አርሶ አደሩ ለጉዳት ተዳርጓል ብሎ በከንቱ ሙሾ ማውረድና ለቅሶ መቀመጥ አይደለም፡፡ አርሶ አደሩን ምን ይጎድልሃል፤ ምን እናቅርብ ማለት ነው የሚጠቅመው፡፡ ይህ የትብብር መንፈስ ነው አርሶ አደሩን የሚጠቅመውና የሚያሻግረው፡፡ የነገውንም ሕይወት ብሩህ የሚያደርግለት።
የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ መንግሥት ለግብርና ግብአት አቅርቦት በሰጠው ልዩ ትኩረት ለመጠቀም ቁርጠኛ በመሆን አርሶ አደሩን ለመደገፍ ወደቡን ጠበቅ ማድረግ፣ ግብአቶቹ አርሶ አደሩ ጋር እስከሚደርሱ ድረስ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የግብርናውን ሥራ ሊያስተጓጉሉ የሚጥሩ አፍራሽ ኃይሎችን አጀንዳ በማምከን ለፌዴራል መንግሥት እርምጃ ስኬታማነት እንዲሁም ለአርሶ አደሩ ያለውን አጋርነት ማረጋገጥ
ይጠበቅበታል፡፡
የትግራይ ሕዝብ የግብርና ግብአት አቅርቦቱ የታለመለትን እንዲያሳካ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል!