
በዩኬ ባለሥልጣናት በስህተት ስማቸው ይፋ የሆኑ አፍጋኒስታናውያን ቤተሰቦች በታሊባን አስተዳደር የአፀፋ ርምጃ ይወሰድብናል በሚል ስጋት እንዳደረባቸው ተናገሩ። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሺህዎች የሚቆጠሩ የአፍጋን ዜጎችን በሚስጥር ወደ ዩኬ የማዘዋወር መረጃ አፈትሎኮ መውጣቱ ይፋ ሆኗል። ይህ መረጃ የልዩ ኃይል እና የዩኬ የስለላ ድርጅት ኤምአይ 6 አባላትን ጨምሮ ከ 100 በላይ የእንግሊዝ መኮንኖች እና በሺህዎች የሚቆጠሩ አፍጋናውያንን ለደህንነት ስጋት የጣለ ነው ተብሏል።
አፈትልኮ የወጣው መረጃ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከ ሐሙስ ድረስ በምስጢር ተይዞ የቆየ ሲሆን፤ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እግዱን ማንሳታቸውን ተከትሎ መገናኛ ብዙኃን ዝርዝሩን እንዲያወጡ ተፈቅዶላቸዋል። ማክሰኞ ዕለት የዩኬ መንግሥት አፈትልኮ የወጣውን መረጃ ያመነ ሲሆን፤ በ20 ዓመታት የእንግሊዝ ቆይታ ከጦሩ ጋር የሠሩ 19 ሺህ የሚሆኑ አፍጋናውያን ወደ ዩኬ ለመዘዋወር ያቀረቡት ማመልከቻ ይፋ ሆኗል። የታሊባን መንግሥት እ.አ.አ በ2021 ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ዩኬ ለመዛወር ጥያቄ ካቀረቡ በሺህዎች የሚቆጠሩ አፍጋኒስታናውያን ውስጥ አማቱ እንደሚገኙ ራሂም (ስሙ የተቀየረ) ተናግሯል።
አምና እና ካቻምን ታሊባን አማቱን ለማግኘት ጥረታቸውን ማጠናከራቸውን የሚናገረው ራሂም አሁን ይህ ለምን እንደሆነ መረዳቱን ይገልፃል። ታሊባን እስኪሳካለት ድረስ የጊዜ ጉዳይ ነው በሚልም ስጋት አድሮበታል። የዩኬ መንግሥት የካቲት እኤአ 2022 መረጃው አፈትልኮ ከወጣ በኋላ በታሊባን ስልታዊ ወይም የበቀል ግድያ ስለመፈፀሙ አነስተኛ ማስረጃ ነው ያለው ይላል።
ነገር ግን ቢቢሲ ያነጋገራቸው አፍጋናውያን መረጃው አፈትሎኮ በመውጣቱ ድንጋጤ እንደተሰማቸው እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የአፃፋ ርምጃ ይወሰዳል በሚል ፍርሃት ላይ ሲሆኑ፤ አፈትልኮ የወጣውን መረጃም “የእንግሊዝ መንግሥት ትልቁ ስህተት” ብለውታል። በዩኬ የሚኖረው ራሂም ስለ ታሊባን ሂሳብ ማወራረድ ጠንቅቆ ያውቃል።ታሊባን ስልጣን ከመያዙ ከሁለት ዓመት በፊት ሁለት የአክስቶቹ ልጆች በቡድኑ ተገድለውበታል።
ከዓመታት በኋላ የእንደዚህ ዓይነቱ የበቀል ዒላማ አሁን ተደብቀው በሚገኙት አማቱ ላይ አነጣጥሯል። 2023 ጀምሮ ለምን ታሊባን ለመያዝ እያደነው እንደሆነ ልናውቅ አልቻልንም ነበር” ይላል። “እርግጠኛ ሆነን መናገር ባንችልም መረጃው አላቸው ብለን እናምናለን”። ራሂም ‘በአፍጋን ማዘዋወር እና እገዛ ፖሊሲ’ መሠረት አማቱ ወደ ዩኬ እንዲዘዋወሩ በማስረጃ አስደግፈው ለመከላከያ ሚኒስቴር ለሦስት ጊዜ ማመልከታቸውን ተናግረዋል።
ከዩኬ መንግሥት ጋር በቀጥታ ባለመሥራታቸውም ማመልከቻው ውድቅ እንደተደረገባቸው ራሂም ተናግሯል። በቅርቡ ግን ከእንግሊዝ ጦር ጋር መሥራታቸውን የሚያሳይ “አሳማኝ ማስረጃ” ማቅረባቸውን ጠቅሷል። እኤአ ከ2023 ጀምሮ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ባቀረቡላቸው ቤቶች ተደብቀው እንደሚገኙ አክሎ ተናግሯል።”አንዳንድ የታሊባን አባላት እስር ቤት ለአስርት ዓመታት ቆይተዋል። ወደ ሥልጣን ሲመጡ በቀል ነው የፈለጉት” ይላል።
መረጃው አፈትሎኮ በመውጣቱ የዜና ትኩረት በማግኘቱ የማዘዋወር ሥራው ተፋጥኖ አማቱ ዩኬ መጥተው ልጃቸውን የራሂም ባለቤት ይገኛናሉ የሚል ተስፋ ሰንቋል። የመረጃው ማፈትለክ እውነተኛ አደጋ መደቀኑን በመጠቆም ታሊባን ርምጃ እንደሚወስድባቸው ያለውን ከባድ ስጋት “የጊዜ ጉዳይ ነው” ይላል። የዩኬ መከላከያ ሚኒስቴር አፈትልኮ በወጣው መረጃ ያደረገው ግምገማ በመረጃው ምክንያት ዒላማ የተደረጉ ሰዎች ስለመኖራቸው የተወሰነ ማስረጃ ነው ያለው ብሏል።
የመከላከያ ሚኒስትር ጆን ሄይሊ ለቢቢሲ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሰዎች በታሊባን ዒላማ የመሆን እድልን መጨመሩ “በጣም የማይመስል” ነው ብለዋል። ለዩኬ ጦር ስለ ታሊባን እንቅስቃሴ መረጃ ሲሰበስቡ የነበሩ አንድ ግለሰብ የመረጃውን ማፈትለክ “የእንግሊዝ መንግሥት የፈፀመው ትልቁ ስህተት ነው” ብለውታል። ግለሰቡ ወደ ዩኬ የተዘዋወሩ ቢሆንም ለቤተሰቦቻቸው ያስገቡት ማመልከቻ ከአፈተለከው መረጃ ውስጥ ሊሆን ይችላል በሚል ስጋት አድሮባቸዋል። ይህን ተከትሎም ወላጆቻቸውን ከካቡል እንዲወጡ እንደነገሯቸው የገለፁት ግለሰቡ፤ “ፈርተው ነበር። የት እንደሚሄዱ አያውቁም። . . .እስካሁን አልደወሉልኝም” ብለዋል።
ሌላ ግለሰብም ባፈተለከው መረጃ የወላጆቻቸው እና የሁለት ታናናሽ ወንዶሞቻቸው መረጃ እንደሚገኝበት እንደተነገራቸው ገልፀው፤ ቤተሰቦቻቻው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር ስለነበራቸው ሥራ እንደ
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም