የቻይና ሩሲያ ወዳጅነት ከምን ጊዜውም በላይ ለምን ጠነከረ?

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይናው አቻቸው ዢ ዢፒንግ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል።

ፑቲን በሰባት ወራት ውስጥ ወደ ቻይና ሲሄዱ ሁለተኛቸው ይሆናል። ከዩክሬን ጦርነት በኋላ ሁለቱ መሪዎች ሲገናኙ ደግሞ አራተኛቸው ይሆናል።

አሜሪካ እና ሌሎችም ሀገራት ሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ለማሸነፍ በሚል ቤጂንግ የሞስኮ ዋነኛ ደጋፊ ሆና ቀጥላለች። ይህ ዘገባ ማዕቀብ የተጣለባት ቻይና እንዴት ነው ሩሲያን በጦር መሣሪያ የምትደግፈው? የሚለውን ይዳስሳል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው “ቻይና ለሩሲያ የምትሰጠው መሣሪያ በዩክሬን ጦርነት ውሏል ወይ የሚለው ነው ነጥቡ” ሲሉ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።

ቻይና ሩሲያ ለመሣሪያነት የምታውለውን ግብዓት በማቅረብ ተከሳለች። ብሊንከን እንዳሉት፣ እነዚህ ግብዓቶች ሩሲያ የበለጠ ወረራ እንድታደርግ የሚያግዙ ታንኮች፣ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ ሚሳኤሎች የሚሠራባቸው ናቸው።

ሩሲያ 70 በመቶ የመሣሪያ እቃዎችና 90 በመቶ ማይክሮ ኤሌክትሪኮች ከቻይና ነው የምታስገባው። አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ ቻይና እና ሆንግ ኮንግ ያሉ 20 ተቋማትን የሚያግድ ነው።

ተቋሞቹ ከሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ምርት ጋር የተያያዘ ወይም ሩሲያ የምዕራባውያንን ማዕቀብ ማለፍ የምትችልባቸው ቴክኖሎጂዎችን ከማምረት ጋር በተያያዘ ነው የታገዱት።

መቀመጫቸውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረጉት ማርያ ሻጊና እንደሚሉት፣ ቻይና ሰሚኮንዳክተር ወደሌሎች ሀገራት በመላክ ግንባር ቀደም ናት።

“አንዳንድ የቻይና ተቋማት የሲቪል ድሮኖችም ያቀርባሉ። ይህም በወታደራዊ አገልግሎትና በሲቪል አገልግሎት መካከል ያለውን መስመር ያለፈ ነው” በማለት ያስረዳሉ።

ቻይና ከሩሲያ ጋር ያላትን የንግድ ትስስር በተመለከተ፣ የጦር መሣሪያን እንደማይጨምር ገልጻለች። “በሕግና ደንብ መሠረት ከአንድ በላይ ጥቅም ያላቸው ቁሳቁሶች እናቀርባለን” ይላል የቻይና መግለጫ።

ቻይና ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአንድ በላይ ጥቅም ያላቸው ቁሳቁሶች ወደተለያዩ ሀገራት ልካለች። ለንግድና ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች በየወሩ ወደ ሩሲያ እንደሚላኩ የቻይና ብሔራዊ መረጃ ያሳያል።

“ቅድሚያ የሚሰጣቸው” በሚል ከተዘረዘሩት መካከል ድሮን እና ታንክ ለመሥራት የሚውሉት ይገኙበታል። ዩኬ የሚገኘው ቲንክ ታንክ ሩሲ እንዳለው፣ የቻይና ሳተላይት ቴክኖሎጂ በዩክሬን መረጃ ለማሰስ ውለዋል።

ቻይና የሩሲያ ቁልፍ የመኪና፣ ልብስ፣ ጥሬ ምርትና ሌሎችም ምርቶች አቅራቢ ናት። ምዕራባውያን ግን ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።

በ2023 በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄደ ንግድ ከምንጊዜውም በላይ ከፍ ብሎ 240 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ይሄ በ2021 ከነበረው 64 በመቶ ጨምሯል።

ሩሲያ ከቻይና ያስገባችው 111 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ዕቃ ሲሆን፣ ቻይና ደግሞ ከሩሲያ 129 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቁሳቁስ አስገብታለች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዊ “የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ በርካታ የቻይና ቤቶችን ያሞቃል። ቻይና ሠር መኪኖች በሩሲያ መንገዶች እየተጓጓዙ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የመስጠትና የመቀበል መሆኑንም አክለዋል። ከ2023 ወዲህ ቻይና የሩሲያ ዋነኛ የንግድ አጋር ሆናለች። የሩሲያ መንግሥት ግማሽ ገቢ የሚገኘው ከነዳጅ ንግድ ነው። ለአሜሪካ፣ ዩኬ እና የአውሮፓ ኅብረት ሀገራትም ይሸጣል።

ከዩክሬን ወረራ በኋላ ግን ማዕቀብ ተጥሏል። ከዚህ በኋላ ወደ እስያ በተለይም ወደ ቻይና እና ሕንድ የሚደረገው ንግድ ጨምሯል።

ሩሲያ ለቻይና ነዳጅ በማቅረብ ከሳዑዲ አረቢያ በልጣለች። ቻይና ለሩሲያ 107 ሚሊዮን ቶን ድፍድፍ ነዳጅ አቅርባለች። እአአ በ2022 ጋር ሲነጻጸር የ24 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

የቡድን 7 አባል ሀገራት ከአውሮፓ ኅብረትና አውስትራሊያ ጋር በመሆን የሩሲያን ገቢ ለመቀነስ ማዕቀቦች ጥለዋል። ሕንድ ግን ለዘመናት የቆየ ግንኙነቷን ከሩሲያ ጋር ቀጥላለች።

ሩሲያ ከሕንድ የምትገዛው ነዳጅ በዚህ ዓመት 44 በመቶ ጨምሯል። አምና ቻይና ከሩሲያ ስምንት ሚሊዮን ፈሳሽ ፔትሮሊየም ያስገባች ሲሆን በ2021 ከነበረው 77 በመቶ ጨምሯል። ሁለቱ ሀገራት የኃይል አቅርቦት ትስስራቸውን ለማጠናከርም አስበዋል።

‘ፓወር ሳይቤሪያ 2’ የተባለ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ትቦ ለመዘርጋት አቅደዋል። ከምዕራብ ሳይቤሪያ ወደ ሰሜን ምሥራቅ ቻይና የተፈጥሮ ጋዝ የሚላክበት ይሆናል።

አሁን ላይ የተፈጥሮ ጋዝ እየተላከ ያለው ‘ሳይቤሪያ ፓይፕላይን’ በተባለውና በ2019 በተዘረጋው ቱቦ ነው።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ማክሰኞ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Recommended For You