ስለ ኢ.ፕ.ድ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ1933 ዓ.ም የተመሠረተ ቀዳሚ የኅትመት መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ነው። ድርጅቱ በአማርኛ “አዲስ ዘመን” የተባለውን ዕለታዊ ጋዜጣ የሚያሳትም ሲሆን፤ በተመሳሳይም በሳምንት ለስድስት ቀናት በእንግሊዝኛ “ዘ ኢትዮጵያን ሔራልድ” የተሰኘውን ጋዜጣ ያሳትማል። በተጨማሪም በአፋን ኦሮሞ “በሪሳ”፣ በአረብኛ “አል-ዓለም”፣ በትግርኛ “ወጋህታ”  እና በሲዳምኛ “ባካልቾ” የተባሉ ሳምንታዊ ጋዜጦችን ያሳትማል። በየወሩ የሚዘጋጀው ዘመን መጽሄትም የድርጅቱ ሰባተኛ የኅትመት ውጤት ነው። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከ300 በላይ ሠራተኞች ያሉት እና ሕዝባዊ አገልግሎት የሚሰጥ ተጠሪነቱ ለኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነ መንግሥታዊ  ተቋም ነው።

ራዕይ
በ2017 የህትመት ውጤቶቹ ተነባቢነትንና ተደራሽነትን በእጥፍ ያሳደገ፣ በአገር ውስጥና በአፍሪካ ቀንድ ተወዳዳሪና ተመራጭ የህትመት ሚዲያ ሆኖ ማየት፤

ተልዕኮ
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትክክለኛና ሚዛናዊ ዘገባዎችን በማሰናዳት፣ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያሰራጭ ተዓማኒ ሚዲያ በመገንባት በልማት፣ በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ኅብረተበሰቡ የተጋ ተሳትፎ እንዲያደርግ የሚያግዝ ተመራጭ የህትመት ሚዲያ መሆን፤
ተቋማዊ ዕሴቶች

• ተቋማዊ መማማር
• የአገልጋይነት ስሜት
• የአዳዲስ ሃሳቦች ምንጭ
• ማህበራዊ ሃላፊነት
• ቀዳሚ የህትመት ሚዲያ
• ጠንካራ ውስጣዊ ተግባቦት
• ህዝባዊ ወገንተኝነት