የትርጉም ስራችን ወዴት እያመራ ነው?

መጽሐፍ ፡- የኢትዮጵያ ታሪክ ከሰሎሞን ሥርወ መንግሥት እስከ አብዮቱ ውድቀት ( 2ኛ ዕትም ) ( የእንግሊዝኛው ርዕስ A History of Ethiopia ከማለቱ በስተቀር በትርጉሙ ላይ በንዑስ ርዕስነት የተጨመረው “ ከሰሎሞን ሥርወ መንግሥት እስከ አብዮቱ ውድቀት” የሚለው እ. ኤ. አቆጣጠር በ 1994 በታተመው የእንግሊዝኛ ዕትም ላይ የለም፡፡)

ደራሲ፡- ማርቆስ ሓሮልድ

ትርጉም፡- በሽፋን ገጽ ላይ ቴዎድሮስ ጸጋዬ ሲል በውስጥ ገጽ ላይ ደግሞ ዓለም ገረመው ይላል፡፡

 ስለትርጉም ስራ መጀመሪያ የሰማሁትና ትርጉም የሚለውን ቃል ስሰማ ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው ከመቅድመ ተዓምረ ማርያም “ ወመጽሐፈ ሥርዓቶሙሰ ተተርጎመት እምነገረ ዐረቢ ለግዕዝ ብሔረ ኢትዮጵያ በመዋዕለ ጳጳሳቲነ አባ ሚካኤል ወአባ ገብርኤል ወኤጲስ ቆጶስነ አባ ዮሐንስ እምአመ ወጽኡ ውስተ ብሔረ ኢትዮጵያ በ፫ ዓመት .“ አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል በሚባሉ ጳጳሳት ዘመን አባ ዮሐንስም ኤጲስ ቆጶስነት በተሾመ ወራት ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ በወጡ በ፫ ዓመት ፣ የሥራታቸውም መጽሐፍ ከዐረብ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ሰዎች በግዕዝ ቋንቋ ተተረጎመች” ( መቅድመ ተአምረ ማርያም) የሚለው ነው።[1]

በኢትዮጵያ የመጻሕፍት ትርጉም ሥራ እጅግ የሚደነቅ የእውቀት ምንጭ ሆኖ የኖረና የተከበረ ሙያ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ይመስለኛል ። እኔን በተመለከተ ግን በልጅነት ዘመኔ ስመ ጥር የነበሩትን አቶ ማሞ ውድነህን ፣ አቶ ተክለጻድቅ መኲሪያን ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌንና በየጊዜው ብቅ እያሉ እጅግ ጠቃሚ አበርክቶ ያደረጉትን ወጣት ተርጓሚዎች ሳስብ ከነሱም ስራ የተጠቀምኩትንና ያተረፍኩትን በረከት መለስ ብዬ ስቃኝ ዛሬም ለትርጉምስራና ለተርጓሚዎች ትልቅ አክብሮት አለኝ። አሁን ግን ይህ የተከበረ የትርጉም ስራ ደረጃው ወድቆና ተንገላትቶ የሚገኝበት ደረጃ ላይ የደረሰ ስለመሰለኝ በፍርሐትና የወደፊቱንም ሳስብ በስጋት ተሞልቻለሁ። በዚህም ምክንያት ዝም ማለት አልቻልኩም።

ለዚህ አባባሌ መነሻ የሆነኝ አዲስ አበባ ከተማ ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓመተ ምሕረት ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በተያያዘ ለማዘጋጀት ላሰብኩት ስራ ማመሳከሪያ ሊሆኑ ይችላሉ ካልኳቸው መጻሕፍት ውስጥ A History of Ethiopia by Marcus Harold, በሚል ርዕስ በማርቆስ ሓሮልድ የተጻፈውን መጽሐፍ የአማርኛ ትርጉም አዲስ አበባ ከብሔራዊ ትያትር ጀርባ ከሚገኙት የመጻሕፍት መሸጫዎች ከአንዱ ገዝቼ ወደ ቤቴ ከገባሁ በኋላ በጉጉት ለማንበብ ስዘጋጅ ያጋጠመኝ ነገር አሳዛኝ ሆኖ ስላገኘሁት ነው።

ለጊዜው አዲስ አበባ የምገኝ ሲሆን ያለሁትም በአጭር የእረፍት ጊዜና በተደራራቢ የስራ ጫና ውስጥ ቢሆንም ሁኔታው አሳዛኝ ሆኖ ስላገኘሁት ብቻ አለፍ አለፍ ብዬ ያገኘሁትን ከዚህ በታች በጥቂቱ በምሳሌነት ሳቀርብ እኔ በጭራሽ ስላልገባኝና እናንተ ምን ያህል ይገባችኋል ? የሚለውን ለአንባቢው ውሳኔ በመተው ነው።

 በመቀጠል በመጽሐፉ የውስጥ ይዘት ውስጥ የሚከተሉት ከተራ ቁጥር 1 እስከ 30 ለምሳሌነት ያቀረብኳቸው ለኔ ያልገቡኝና ምንም ትርጉም ሊሰጡኝ ያልቻሉ ሲሆን በኔ ዕምነት መጽሐፉ በጎግል ተተርጉሞ እንደወረደ ለመታተም የበቃ ነው የሚል ግምት ስላደረብኝ ለአንባቢ ፍርድ ይረዳ ዘንድ ለአብነት ከመጽሐፉ የሚከተሉተን ቀንጨብ አድርጌ አቅርቤያለሁና ተመልከቱት ።

1. የእነሱ ዋና ትብብር ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነው ፣ እናም በመንደሮች የተደራጁ ናቸው ቀሳውስት እና ተጓዥ ቅዱስ ቅዱሳን የክርስትናን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው በመመልከት በስነ ምግባር እና በሃይማኖታዊ የበላይት እንዲታመኑ ያደርጉላቸዋል (ገጽ 5)

እንግሊዝኛው

Their primary affiliation is to the Orthodox Church. And they are loosely organized into parishes. Priests and itinerant holy men keep the banner of Christianity high and drill their auditors to believe in their moral and religious superiority.( Page xi)

2. በኢትዮጵያ የደቡባዊ ክልሎች ውስጥ የተለያዩ ሕዝቦች ይኖራሉ። ከእነዚህም ወስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ሴሚካዊ ተናጋሪ ጉራጌ እና ኩሽቲክ ተናጋሪ የሆኑት ኮንሶና ሲዳማ ናቸው። (ገጽ 5)

3. ጉራጌዎች በአብዛኛው ሙስሊሞች ቢሆኑም በመካከላቸው አንዳንድ ክርስቲያኖችን ይመድባሉ (ገጽ 5)

4. በተጨማሪም እጅግ አስፈላጊ የሆኑት የሱዳን ሕዝቦች በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ዳርቻ ይኖራሉ። (ገጽ 5) የኔ ጥያቄ (የማያስፈልግ ሕዝብ አለ)

5. መንግስቱ ኃይለማርያም 1974-1991) … ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ስብጥርም ፍላጎት ነበረው። (ገጽ 5)

6. አቢሊስ….. እናም በጥሩ በተስተካከለ ሰረገላ እና ከአራት እጥፍ በላይ የሆነ አካል ነበረው። (ገጽ 13)

7. ንግድ ክብር እና ጠብ መንጃን የሚወስዱ ልሂቃንን እንዲጨምር የሚፈቅድ ሀብት አምጥቷል። በአረመኔያዊ ጦርነቶች የተፈጠሩ ምኞት እና ስግብግብነት ፣ ዕድልና ችሎታ ማጠናከሪያን አመጣ። እናም ስኬት ወደከፍተኛ

 ሃብት ፣ ብዙ ተከታዮች እና ተጨማሪ ማስመሰል አመራ።(ገጽ 17)

8. የአክሱም ግዛት በአንደኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ማብቂያ ላይ ወደ ሰፊው የተታመ ብርሃን ሲመጣ ፣ በጥሩ ሁኔታ ካልተቀናጀ የተዋሃደ የንግድ ልውውጥ ነው (ገጽ 17)

9. በየመን የተሳካ ውጤት ጠላቶቻቸውን ያዳክማል ፣ ምናልባትም ተጋላጭነትን አያበሳጭም (ገጽ 26)

10. የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን አንዲመራ የተመረጠችው የግብጽ ቅድመ ቅኝ ግዛት አገሪቷን ፖለቲካዋን ፣ ቋንቋዋን፣ ወይም ባሕሏን በደንብ አልገባችም ዜግዊስ ወደ ግብጽ ባለስልጣናት ለመዞር የፈለጉትን ወደ ሞንፊሽያ ፓትርያርክ ወደነበረበት ተንኮል ነገር ግን ኢትዮጵያን ወደ ጦር መሪዎች ትኲረት እንዲስብ እና በተዛባ እና በፍቅር መንገድ ወደ ምዕራቡ ዓለም እንዲመጣ በማድረግ ግብጽ ግዛት ለማምለጥ ፈለጉ። (ገጽ 30)

11. መላው የፖለቲከ ምጣኔ ሀብት የተመሰረተው የእሳተ ገሞራ አፈር ውስጥ ረዘም ላለ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ለመዝራት እና ገበሬዎች በሚጠቀሙበት ገበሬ ላይ ነበር።አዝመራው ከጥቅምት – ህዳር ወር በኋላ አዝመራው እህልና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለአካባቢያዊው ጌታ ግብር ሰጠው፣ እሱ ግን እጅግ በጣም ትልቅ ከሆነው ቤትና ከቀጠለ በስተቀር ፣እንደ ተገዢዎቹ በጣም የሚለምደው በአብዛኛው በአገር ውስጥ በተሠሩ መሳሪያዎች ፣ በጨርቅ ነው።ተንቀሳቃሽው ፍርድ ቤት በቀላሉ የሚንቀሳቀስ ነበር። (ገጽ 31)

12. ባለፉት ምዕተ አመታት የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተማ በመሆኗ ከመላው ግዛቶች የመጡ መምህራንን እና አጋቾችን ሳብ። ዘረዓ ያዕቆብ እንኳ በብዙ ሃይማኖታዊ በራሪ ወረቀቶች ውስጥ ስሙን በማንሳት በሀብታም ባሕላዊ ሕይወት ውስጥ ተሳትፏል ።አዲሱ ካፒታል የውጪውን ዓለም ፍላጎት እንኳ ቀልብሷል። ውጤቱም ንጉሠ ነገሥቱን ያስደስተዋል። (ገጽ 45)

13. አካባቢው ንጉሠ ነገስቱ እስር ቤት እንዲገባ በጣም ሰፊ ነበር፣ እና ደጋማ አካባቢዎች በሞቃታማ እና ደረቅ በሆነ ሀገር ውስጥ በሙስሊሞች መካከል መኖርን ይጠሉ ነበር (ገጽ 47)

 14. በመሃል ላይ ያለው በየጊዜው መከፋፈል በሰለስቲካዊ የፖለቲካ ኃይል ፍሰት ላይ በሴንትራልገጣ ሃይሎች ተደምስሷል።በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ የቋንቋና ሃይማኖታዊ ትስስር ያላቸው ሰዎች በሰሜናዊ- ማዕከላዊ ከፍታ ቦታዎች ላይ ያተኮረ የበተችና የተዋሃደች አገር ነች። ዋናው ቦታው በቅርብ ጊዜ በተያዙት አውራጃዎች ደውሎ ነበር። ነዋሪዎቻቸው ቢያንስ እጅግ የላቁ ክርስቲያኖች እና አስተዳደራዊውም በባሕላዊ ግዛቶች ውስጥ የመንግስት መስሏል። (ገጽ 48)

15. በባህል ፣ በሃይማኖታዊ እና በኢኮኖሚያዊነቱ እና በአካባቢዎች ይለምዳሉ። ችግር በሚኖርበት ጊዜ ወይም በእውነቱ የንጉሳዊ አለመረጋጋት ፣ ሞት ወይም የተተካው መንግስት ኮንትራት ጀመረ። (ገጽ 49)

16. አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሃገር ውስጥ ማሰብን ቀጠሉ፣ እናም ለእነሱ መንግስት በግብር ፍላጎት ላይ ብቻ ራሱን የሚያንጸባርቅ ጨለማ አካል ነው።(ገጽ 49)

17. እሷ ለየት ያለ ብልህ ሰው ነች፣የፖለቲካ ተሰጥኦዋ ከዛራ ያቢብ መሪነት በባዳ ማርያም የግዛት ዘመን (1468-1478)ፍርድ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ላይ የወሰደችው መጀመሪያ ላይ ከሃዲያ ፣ ስሜቷ ለኢትዮጵያ ከሚያስችላቸው ሃብቶች ጋር ተጣምሮ ነበር፣ እናም የትምክሕት ምርጡ የንጉሠ ነገስቱ አነስተኛ ንጉሠ ነገስታዊ መንግስት እንደሆነች ያምናሉ። (ገጽ 49)

18. በዳ ማሪያም ግብር ለማዕከላዊ ቦታ እንዲሰጥ ከመከልከል ይልቅ መንገዱን ለመፈለግ ወደ መንገድ ሄደች (ገጽ 50)

19. ግን እንደ ቀድሞው ሁኔታ ያለመከሰስ ጉዳይ ምንም እንኳን የዘገው የኦሮሞና የቤተ እስራኤል አስፈላጊ ሕዝቦች ቢኖሩም አብዛኛዎቹ ክርስቲያናዊ ሴማዊ ተናጋሪ ሕዝቦችን ያካተተ በቀላሉ ሊወገድ የሚችል ማሕበራዊ ትብብራዊ ቡድን ነበር። በተረቂቶች በስተቀር ሰዎቹ የሰለሞናዊው መንግስት የፖለቲካ ምጣኔ ሃብት ውስጥ የሚኖሩት አርሶ አደሩ ገበሬ ነበር።ክርስቲያኖቻቸው በአንድ ወቅት ገዢዎቻቸው እጅግ በታም ትልቅ በሆነ ግዛት ሲይዙ እንደነበር ሁሉ መቼም አልረሱም፡እናም ኢትዮጵያዊነት በሰሎሞን ነገድ ስርወ መንግስት ስርወት ስራዎች ሕጋዊነት እንዲጨምር በማድረግ የፖለቲካ መሪን ወደ አለቃውና የገበሬው ጭንቅላት ውስጥ የገባ የፖለቲካ ሀሳብ ነበር (ገጽ 63)

20. የተሃድሶና የተሻሻለ ወታደራዊ በአዲሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ግልጽ የሆነ ወሳኝ ሚና ነበረው። ሳራ ዴንጋ ብዙ ወታደሮችን በመመልመል አክሊል ቀጥታ ትዕዛዝ ስር ተጨማሪ ክፍሎችን አቋቋመ። (ገጽ 63)

21. መንትዮቹ የኦሮሞ-ሙስሊም ቀውሶች የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ውጤታማነት በተመለከተ ጥያቄዎችን አስነስቷል።ክርስቲያኖች ቀሳውስትን ንብረታቸውንን ክልላቸውን ለሙስሊሞች ትተው ለኦሮሞ መስጠታቸውን ስለሚቀጥሉ የቤተክርስቲያኒቱ ርዕዮተ ዓለም ጉድለት ነበረው።የገዢው መደብ ክፍሎችለመዋጋት የገበሬን ውሳኔ ያዳከመው ወይም ከኦሮሞ መስፋፋት በስተጀርባ ያለውን ጫና የሚረዱ የግጭት አፈጻጸም አድናቆት የላቸውም ።እራሳቸውን እንከን የለሽ አድርገው የሚቆጥሯቸው በሆነ ምክንያት ፣የፍርድ ቤት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጦር አዳዲስ ዘዴዎችን፣ እና ድጋፎችን የመፈለግ ፣የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መታደስ ያስፈልጋታል ሲሉ አስረድተዋል። (ገጽ 65)

22. ሃሳቦቻቸው የሚያነቃቃ ተጽዕኖ ባላቸው ፖረቹጋሊዎች በፍርድ ቤት ተቀባይነት ያላቸው ቄሶች ይመጣሉ።አጼ ገላውዴዎስ (እ ኤ. አቆጣጠር 1540-1559) በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተምሕሮዎች ላይ እምነት መታለን የሚያረጋግጥ ዝነኛ አምነት መግለጫን በመጻፍ ምላሽ ሰጡ። ከአምሳ አመት በኋላ እና ብዙ የኦሮሞ መስፋፋት ግዛቶች በኋላ ንጉሠ ነገሥት ዘ ዴንደር ከ (1603-1604)ቅድመ ተተኪው ቤተክርስቲያን ትምሕርት ውስጥ ያላቸውን እምነት ማካፈል አልቻሉም።እናም በተስፋና በምስጢር ወደ ሮማ ካቶሊክነት ተለወጡ። ከደረሰ በኋላ ወዲያውኑ በአሰቃቂ የክልል ንጉሶች ተወግዶ .. (ገጽ 65-66)

23. የፔዝ ትዕግስት የሌለው ተተካ፣አፈኒሶ ማዴን የተባለ ሌላ የስፔናዊው ኢዚት የኢትዮጵያ ካቶሊክ ኢትሆፍ ቆጶስ ሆኖ ከ 1625 በኋላ እንዲህ አይነት ለውጥ ተደረገ-፤፤የቅዱስ እናት የበታች ኢትዮጵያውያንን ነፍሳት ለማዳን አንድ ቀን መጠበቅ እንደማይችል ወሰነ። (ገጽ 67)

24. ጨካኝ ፖለቲከኛ ፣ዋና ከተማቸውን በኦሮሞ ወታደሮች፣ በአስተዳዳሪዎች እና በፍርድ ቤቶች ሲሞላ የተመለከቱትን የአቢሲኒያ ወግ አጥባቂዎች ተፈጥሯዊ ጭንቀቶችን ተጠቅሟል። ባሕላዊ እንደመሆናቸው፣ የሰሎሞናዊው መንግሥት በፍጥነት ወደ እስልምና አዝጋሚ ተንሸራታች እየቀነሰ እንደነበረ ያምናሉ፣ ዮአስ ታዋቂውን ሰው ከክርስቲያን አማላጅነት ወደ ምዕራብ በመዘዋወር ብቸኛው ጎል ያስቆጠረ ነው። (ገጽ 75)

25. አስገዳጅ የቤተክርስቲያን ጋብቻ አለመኖሩን እና በ 1820 አካባቢ ደጃዝማች አዲስ መመሪያ መርጣለች እና አጼ ወንድ ልጅዋን ወደ ጎንደር ወሰዳት፣ ኃይለኛ መንስሔ የሆነውን ኮሶ በመሸጥ ኑሯቸውን ትመራለች። ለልጇ በበቂ ሁኔታ ማቅረብ ባለመቻሏ ደጃ በሚሆንበት ጊዜ ወደ ኪዋራ መልሷታል።(ገጽ 94)

26. ሆኖም በአጪር ጊዜ ውስጥ አውሮፓውያን ከምጽዋ አርባ አምስት ማይል ብቻ የሚሆኑ ደስ የሚሉ እና ጨዋ በሆኑት የቦጎስ ተራሮች ሳቢዎችን ይስባሉ። (ገጽ 130)

27. በሃዘን ወደ ቤት ሲዘዋወር ተበታትነው ነበር። ራሰዝ አላውላ እና ሚካይል የተባሉት አነስተኛ ሀይሎች ብቻ ይዘው የሚቆዩ ናቸው።ሆኖም ምኒልክ በላስታ ፣ቤጁ፣ ጎጃም ፣ ወሎ ውስጥ ያሉ የአካባቢ ባለሥልጣናትን በማስረከቡ ሰሜኑን በኃይል በፍጥነት ተጓዘ። (ገጽ 137)

28. እ.ኤ.አ ማርች 1 ቀን ከምሽቱ 4 ሰዓት ምኒልክ ለህዝባቸው የክተት አዋጅ አስነገሩ። ይህ የምግብ ሁኔታ ንጉሠ ነገሥቱ መጋቢት 2 ቀን በጦር ሰፈሩ እንዲመታ ያዘዘው ስለሆነ ኣሳዛኝ ጊዜ ነበር። በርከት ያሉ መልዕክተኞችና ሯጮች ጠላት እየገሰገሰ መሆኑን ለመዘገብ በተጣደፉ ጊዜ የእፎታው ከፍተኛ መሆን አለበት። ( ገጽ 153)

29. ቀደም ሲል ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ ወንድሞቻቸው ድንቁርናን እና ውርደትን ያካፈሉበት ፣ ግን በድንገት ጉልበታቸው ፣ የእውቀት ብርሃን እና እድገታቸው ፣ ነባር ቀሳውስት ንቅናቄ እና ብልሹ ሥነ-ምግባርን በመጎበኘት የሚነቀፈው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አሁን እንደ መንፈስ ቅዱስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መንፈስ እውነተኛ ተሽከርካሪ ሆና ታየች።(ገጽ 155)

30. እንደ ጃፓኖች የኢትዮጵያውያን ህዝብ በጥሩ ስነ ስርዓት አልተስተካከለም። ግዛቱ አዲስ የተቋቋመ ሲሆን አስተዳደሩም አሁንም ሥርዓተ – ሥርዓቱ ነበር። (ገጽ 165)

እንግሊዝኛው

The Ethiopian People were not so well disciplined as the Japanese, the empire was newly established and its administration still rudimentary. (Page 106)

በአጠቃላይ በዚህ ወደ አማርኛ በተተረጎመው መጽሐፍ ላይ ዕጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ምንም ትርጉም የማይሰጡ የቃላት ክምችቶች መጽሐፍ ተብለው የቀረቡበት ሁኔታ መስሎ ስላገኘሁት ይህን የማንቂያ ጽሑፍ ለማዘጋጀት ተገድጃለሁ። የጽሑፉ ዋና ዓላማም የሚከተለው ነው

1ኛ) መጽሐፉ ከአንድ ጊዜ በላይ መታታሙን እኔ የገዛሁት 2ኛ ዕትም ስለሚል በዚህ ማረጋገጥ ይቻላል። በዚህ መጽሐፍ ተርጓሚነት ስማቸው የተጠቀሰው ቴዎድሮስ ጸጋዬ / ዓለም ገረመው ወይም ማንኛውም ግለሰብ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 25 ለጠቀስኩት ጥቅስ ማብራሪያ እንዲሰጡኝ እጠብቃለሁ። እኔ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከሩብ ምዕተ አመት በላይ በውጪ አገር የኖርኩ በመሆኔ ምናልባትም በነዚህ 30 አመታት የአማርኛ ቋንቋ ለውጥ አሳይቶና ያልተረዳሁት ነገር ካለ ለመማርም ፈቃደኛ መሆኔን እገልጻለሁ፡

2ኛ) ጉዳዩን በባለቤትነት በመውሰድ መልስ የሚሰጥ ከጠፋ ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ የደራስያን ማሕበር፣ የትምሕርት ሚኒስቴር፣ የታሪክና የቅርስ ጉዳይ የሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ወዘተ.. እንደዚህ አይነት በተለይም የአገርን ታሪክ በዚህ መንገድ ጽፎ፣ አሳትሞ በገበያ ላይ የሚያውል ማንኛውም አካልም ሆነ ግለሰብ በሕግ አግባብ የሚጠየቅበት፣ የሚታረምበት፣ ገበያ ላይ እየተሸጠ ያለውም ደረጃውን ያልጠበቀና ትክክለኛውን የደራሲውን መልዕክት የማያስተላልፍ ሆኖ ከተገኘ ተገቢው እርምጃ የሚወሰድበት መንገድ ካለ ለማሳሰብና የግሌን አስተያየት ለመስጠት ነው።

 በዮሐንስ ተፈራ /ኦስሎ ኖርዌይ/

ዘመን መፅሄት ኅዳር 2014 ዓ.ም

Recommended For You