በአገራችን የጎመራው ሁሉን አቀፍ ለውጥ አንድ ዓመቱን ደፈነ! ብዙ ደስ የሚሉ፣ ጥቂት የሚያስከፉ፣ባይደገሙ ያልናቸው ነገሮች በተከሰቱበትና ተስ ፋና ስጋት በተደቀኑበት ሁኔታ ነው አንደኛ ዓመቱን ያሰብነው። ማረሚያ ቤቶች ባዶ ሆኑ እስኪያ ስብል ብዙ ታራሚዎች በይቅርታና ምህረት እንዲሁም ክሳቸው ተቋ ርጦ መለቀቃቸው፣ ማረሚያ ቤቶች በሚያስገርም ሁኔታ ድብቅ ገመና ቸው ይፋ ሆኖ ከማሰቃያነት ወደ ማረሚያነት የመሸጋገር ሂደት ላይ መሆናቸው፣ የአገራቸውን መሬት መርገጥ ፈጽሞ አይፈቀድላቸው የነበሩ ብዙ ዳያስፖራዎችና ፖለቲከኞች ለአገራቸው አፈር መብቃታቸው፣ ነፍጥ አንግበው የነበሩ ታጣቂዎች ነፍጣቸውን አስቀምጠው ወደ ሰላማዊ ትግል መቀላቀላቸውና ከኤርትራ ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት ወዘተ አንጀታችንን ቅቤ ያጠጣና አቦ ያዛልቅልን ያልናቸው ፍቱን ተግባራት ነበሩ።
በገዛ አገራቸው ዜጎች መፈናቀ ላቸው፣ጋጠ ወጥነት ጫፍ መድረሱ፣ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ በገዛ ወገኖቹ ተዘቅዝቆ መሰቀሉና እንኳን ለሰው አውሬ እንኳን በማይገባ ሁኔታ የሰው ልጅ ተቀጥቅጦ በላዩ እሳት እስኪነድ ድረስ እንደ አገር አንገት ያስደፉን አስቀያሚ ተግባራትም በዚሁ ዓመት የተስተናገዱ ነበሩ። ዓመቱ እንዲህ ባለ ሁኔታ ሊዘከር በተቃረበበት ወቅት በዕለተ ቅዳሜ ደግሞ እጅግ የማከብራቸው ትሁቱና አስተዋዩ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው ያስደመጡን አንጀት አርስ ንግግር ደግሞ ለእኔ በግሌ የበዓሉ ልዩ ገጸ በረከት ነው ብዬ ወስጀዋለሁ።
ለወሬና አሉባልታ ቦታ ሳይሰጡ በዝምታ ሥራቸውን ሲሠሩ የከረሙት ኦቦ ለማ በመድረኩ ያቀረቡት ገለጻ እኔን ጨምሮ በበርካቶች አዕምሮ ላይ ተመርጎ የነበረውን ብዥታ ያጠፋ ነበረ። አቦ ለማ የመጀመሪያ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በበሬ ወለደ ወሬ አገርን ለማበጣበጥ ለሚ ሠሩ ሰዎች ሲሆን እንኳን ልናገረው ፈጽሞ ላሰበው የማልችለው ነገር ነው በማህበራዊ ሚዲያ ሲናፈስና ሲላመጥ የነበረው በማለት የውሸትን ዕድሜ አሳጥረዋል፡፡
ኦቦ ለማ ህይወቴን ጭምር አስይዤ ለለውጡ የታገልኩት ሰርቄና ዘርፌ አንድን ብሔር ለመጥቀም ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩል የሚታዩባትን አገር እውን ለማድረግ ነው ሲሉ የተናገሩት ንግግርም ለዘላለም ከአዕምሮ የማይፋቅ ነው። “የኦሮሞ ህዝብ ኮንደሚኒየም ሰርቀን እንድንሰጠው አይደለም የሾመን፣ የኦሮሞ ህዝብ መታወቂያ ስረቁልኝ አላለም። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ እንዲህ ያለ ተራ ሌብነት አይደለም። የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በኢትዮጵያ ውስጥ እኩል የመታየት ነው፣ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በጋራ ሠርቶ መለወጥ ነው። የኦሮሞ ህዝብ እኔን ለሌብነት አልሾመኝም። እንዲህ ያለ ተራ ጉዳይ ማራገብ የኦሮሞን ህዝብ መናቅ ነው፡፡”
ሲሉ የተናገሩት ንግግርም የሰውዬውን ክቡር ሰብዕና እጅግ የሚያጎላ ነው፡፡ ክቡር ኦቦ ለማ “ኢትዮጵያዊነትን ማንም በቀብድ አልሰጠኝም ወድጄና ፈቅጄ የተከናነብኩት ክቡር ማንነት ነው” ሲሉም እራሳቸውን ዜግነት ሰጪና ነፋጊ ያደረጉ አካላትን ረብ የለሽ እሳቤ ሜዳ ላይ አስቀርተውታል። ኢትዮጵያዊነት ማንም ሊሰጠንናሊነፍገን የማይችል ክቡር ማንነት ነውና ኦቦ ለማን እንዳመሰግናቸው ተጨማሪ ምክንያት ሆኖኛል። ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያውያን ያስ ተላለፉት “ማንም በነዳን መንገድ መንጎዱ ይቅር ለምን ብለን እንጠየቅ” የሚለው መልዕክትም ቆም ብለን አጽ ንዖት ሊሰጠውና ቆም ብለን ልናስብበት የሚገባ ትልቅ ጉዳይ ይመስለኛል። ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ በፌስቡክ የሚለቀቀውን መረጃ ሳያጠራ ሆ ብሎ የሚነጉድና ለጥፋት መሰለፍ በሰፊው እየተስተዋለ ነውና! በአጠቃላይ ኦቦ ለማ መገርሳ ለሐሰት ወሬ ፈብራኪዎች፣ ለጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች ለወጣቶችና ለመላ ኢትዮጵያውያን ያስተላለፉት እንከን አልባ መልዕክት አገርን ከጥፋት የሚ ያድን ነውና ልብ እንበለው ለማለት እወዳለሁ!
አዲስ ዘመን መጋቢት 28/2011 ዕድል ከአዲሱ ሚካኤል