አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ ያለውን የኔትዎርክ መሰረተ ልማት ለማሟላት ሆነ ከሳይበር ደህንነት ጋር ተያይዞ እንደ አገር የሚከናወኑ ሥራዎችን በእውቀት ላይ ተመስርቶ ማገዝ የሚችል ህብ ረተሰብ ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን የጅማ ዩኒቨ ርሲቲ ገለጸ።
በዩኒቨርሲቲው የሲስኮ ኔትዎርኪንግ አካዳሚ በዘርፉ መምህራን አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ የሁለት ቀን የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክተር እና የሲስኮ ኔትዎርኪንግ አካዳሚ ተጠሪ ዶክተር ግሩም ከተማ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ በርካታ የኔትዎርክ ባለሙያ ቢኖርም ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ይዘው የሚወጡት እውቀትና ኢንዱስትሪው የሚፈልገው ክህሎት እምብዛም የተጣጣመ ባለመሆኑ ተጨ ማሪ ሥልጠናዎችን እንዲወስዱ ይደረጋሉ።
በዚህ ረገድ ተቋሙ የዘርፉ ባለሙያዎች በእውቀት ላይ ተመስርተው በአገሪቱ የኔትዎርክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲያከናውኑ እና በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሳይበር ጥቃት መከላከል መፍትሔ እንዲሰጡ ለማስቻል የሚያግዙ ተግባራት እያከና ወነ ይገኛል።
ዶክተር ግሩም እንደሚሉት፤ ዩኒቨርሲቲው ሥራውን ከአሜሪካው የአይ.ቲ ሃርድ ዌርና ሶፍት ዌር አምራች ሲስኮ ጋር በመተባበር የሚያከናውን ሲሆን፤ አካዳሚውና ማስተባበሪያውም በኢትዮ ጵያ ውስጥ ያሉ አካዳሚዎች የዘርፉን የሰው ኃይል በጥራትም ሆነ በብዛት ማሰልጠን እንዲችሉ እየደገፈ ይገኛል። የእለቱ መድረክም በዘርፉ ባሉ መልካም ተግባራትና ችግሮች ላይ በመምከር
በቀጣይ የተሻለ ሥራ ለመሥራት የሚያስችሉ መፍትሔዎችን ማፈላለግና የእርምት ርምጃዎችን ለመውሰድና ከዘመኑ ጋር ለመራመድ የሚያግዙ፤ ለአዳዲስ ችግሮች አዳዲስ መፍትሔዎች የሚፈል ቅባቸው ውይይቶች የሚከናወኑበት ነው።
እንደ ዶክተር ሳሙኤል ገለጻ፤ በመከላከያ ሪፎርምም የሳይበር ደህንነት ትኩረት የተሰጠው ዓለም አቀፋዊ የሳይበር ጥቃት በቀላል የሚ ሰነዘሩ መሆኑን ተከትሎ የሚመጡ ችግሮችን ለመከላከልና የአገርን ደህንነት ለመጠበቅ ነው።
ከዚህ አኳያ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚ በአገሪቱ የኔትዎርክ መሰረተ ልማትና የሳይበር ደህንነት ላይ የሚከናወነውን ተግባር የሚያግዝ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ህብረተሰብ ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል። ከመከላከያ ጋር ላለው ሥራ ውጤታማነትም የደብረ ዘይትን የመከላከያ ኢን ጂነሪንግ ኮሌጅ በመምረጥ ከመከላከያ አባላት፣ ከኢንጂነሪንግ ኮሌጁና ከኢንሳ ለተውጣጡ ባለ ሙያዎች የመጀመሪያ ዙር የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጥቷል።
ዩኒቨርሲቲው በተለይም በ2011 በጀት ዓመት በዚሁ በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ሲሆን፤ ባለሙያዎችም ስለ ሳይበር ሴኩሪቲ አጠቃላይ እውቀት እንዲኖራቸው ሥልጠና እየሰጠ ነው።
አካዳሚው በ1998 በኢትዮጵያ ሲጀምር ከተመረጡ 10 አካዳሚዎች አንዱ የሆነው ጅማ ዩኒቨርሲቲም፤ ከማስተባበር ሥራው በተጓዳኝ በእስካሁን ጉዞው በዩኒቨርሲቲው አካዳሚ ብቻ ከ13ሺ በላይ ባለሙያዎችን አሠልጥኗል። በቀጣይም ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር ማንኛውም መሥሪያ ቤት ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ ሊያውቃቸው በሚገቡ ነገሮች ላይ ሥልጠና ይሰጣል።
የዩኒቨርሲቲው የማስተባበር ሂደት ኢት ዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሶማሊያና ጅቡቲን የሚ ጨምር ሲሆን፤ በሶማሊያ አራት አካዳሚዎች አሉት። በኤርትራም ለመክፈት እቅድ አለው። አሠልጣኞችም በዩኒቨርሲቲው ሥልጠና እየወ ሰዱ ሲሆን፤ ይሄን ዓይነት ትብብር መኖሩም ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በእነዚህ አገራትም በዘርፉ የሠለጠነ የሰው ኃይል እንዲኖር በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሥራ እንዲለመድ የድርሻውን እያበረከተ ይገኛል። ይሄም የኔትዎርክ መሰረተ ልማቶችንም ሆነ የሳይበር ጥቃትን የመከላከል ሥራዎች አንድም በእውቀት ላይ ተመስርተው እንዲከናወኑ ያግዛል፤ ሁለተኛም ለሚፈጠሩ ችግሮችም በእውቀት ላይ የተመሰረተ መፍትሔ ለመስጠት ያስችላል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 25/2011
በወንድወሰን ሽመልስ