አዲስ አበባ፡- የአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገድ ግንባታ ከታቀደው ጊዜ በላይ መጓተቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ፡፡
በምክር ቤቱ የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን የመስክ ምልከታ ካደረገባቸው ቦታዎች የአዋሽ አርባ ዱለቻ የመንድ ግንባታ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን በምልከታው ወቅት የመንገዱን መጓ ተት ለማየት ችሏል። የአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገዶች መስፋፋት የአርብቶ አደሩን ጥቅም ለማጉላት ታቅዶ መሥራቱን አድንቆ ሆኖም ግን ፕሮጀክቱ ከታቀደው በላይ ጊዜ መውሰዱን እንደ ድክመት አንስቷል፡፡
የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች በበኩላቸው የግንባ ታው መዘግየት ከግብዓት፣ ከበጀትና ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ የተፈጠረ መሆኑን አስረድ ተዋል፡፡ በተለይ ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ በአካባቢው ካሳ ተከፍሏቸው ከስፍራው ያል ተነሱ አርብቶ አደሮች በመኖራቸው ለሥራው እንቅፋት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊዎቹ አክለው እንደገለፁት በዱለቻ በኩል 10 ኪሎ ሜትር መሬት ረግረጋማ በመሆኑ መንገዱን ለመሥራት ከባድ እና ረዘም ያለም ጊዜ እንዲ ወስድ እንዳደረገው ጠቅሰዋል።
በተያያዘም ቋሚ ኮሚቴው በአፋር ክልል በዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌና አሚባራ ወረዳ ያሉ አርብቶ አደሮችንና በሶማሊያ ክልል ቸረር ዞን ደገሃቡር ወረዳ በአመድሌ የእንስሳት ማቆያ የመስክ ምልከታም አካሂደዋል፡፡
ቋሚ ኮሚቴው በጉብኝቱ ወቅትም በወረዳው ያሉ አርብቶ አደሮችን ሰብሰቦ አነጋግሯል። በውይይቱም ከታቀዱ አራት ዓመታትን ያሳለፉ በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና፣ በውሃ እና በእንስሳት ልማት አርብቶ አደሩን ተሳታፊ ለማድረግ የታቀዱ ሥራዎች እየተሠሩ ቢሆንም በርካታ ሥራዎች እንደሚቀሩም መታዘቡን አስታውቋል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 22/2011
አብርሃም ተወልደ