አገራችን አንድ ዓመት ባስቆጠረ የለውጥ ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ የለውጥ ወቅት በርካታ መሠረታዊ ጉዳዮች የተከናወኑ ቢሆንም በፖለቲካው መስክ ያለው የፖለቲካ ምህዳር መስፋት ጉዳይ ቁልፍ መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ መንበረ ሥልጣኑ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ከፖለቲካ ምህዳሩ ጋር ተያይዞ ለሃሳብ ብዝሀነት እና ስለ ሃሳብ አሸናፊነት በማንሳት ቀልብ የሳበ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ከንግግራቸው ባለፈም በተግባር የሚታይ ለውጥ በማምጣት የለውጥ መሪነታቸውን አሳይተዋል፤ አስመስከረውማል፡፡
ከእነዚህ ተጠቃሽ ተግባራት ውስጥ ከቀድሞው በተሻለ መልኩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመስኩ በሙሉ አቅማቸው በመሳተፍ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው ላይ ሚናቸውን እንዲያበረክቱ በሩን ክፍት አድርገዋል፡፡ በዚህም ዓላማና ግባቸውን ለሕዝቡ በማድረስ በኩል የተሰጠው ነፃነት መንግሥትን የሚያስመሰግነው ብቻ ሳይሆን አንዱ የለውጥ ጉዞው ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡
የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ሌላው ማሳያ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የነበሩ ፅንፍ የወጣ አቋም የነበራቸው ኃይሎች ሳይቀሩ በዚህ ምህዳር አብይ ተዋናይ ለመሆን አገር ውስጥ ገብተዋል፤ እነዚህም ቢሆኑ ያለማንም ከልካይ ከሕዝቡ ጋር በመገናኘት ‹‹አለን›› ያሉትን ሃሳብ በማራመድና አማራጮቻቸውን በማሳየት የዕድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ይህ አካሄድ በመሠረቱ ሃሳብ በሚፈለገው ልክ እንዲሸራሸርና የሃሳብ ብዝሀነት እንዲኖር ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡
መንግሥት የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት አለበት በተባለበት ልክ ለማስፋትና በሩን ክፍት ለማድረግ አሉ የተባሉ ማነቆዎችን በማስወገድ ረገድ እየሰራቸው ያሉ ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በመሆኑም የተለያዩ የሕግ መሠረቶችን ከማሻሻልና ከማሟላት ባለፈ የዴሞክራሲ ተቋማቱን በአዲስ መልክ ማደራጀት እና አስፈላጊውን ሁሉ በማሟላት ተቋማቱ በተገቢው ሰው እንዲመሩ ተደርጓል፡፡
የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ረገድ በመንግሥት በኩል ያለው ቁርጠኝነት የተሻለ ተግባር ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዓመት ዕድሜ ውስጥ ዴሞክራሲውን በተለይ ደግሞ የፖለቲካ ምህዳሩን የሚጋፉ አንዳንድ ተግባራት ብቅ ማለታቸው የሚደበቅ አይደለም፡፡ መንግሥት በሩን ክፍት በማድረጉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓላማና ሃሳባቸውን ለሕዝብ የማሳወቅ እንቅስቃሴ በአንዳንድ ሥርዓት አልበኛ ግለሰቦችና ቡድኖች እየተገደበ ይገኛል፡፡ ይህን ሁኔታ ደግሞ ፓርቲዎቹ ሳይቀሩ የሚገልጹት ሆኗል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ‹‹ያልተፈጠረ፤ ተፈጠረ›› የተፈጠረውን ደግሞ በማጋነን እና ከብሔር ጋር በማስተሳሰር ዜጎች ችግር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ የመጣውን ለውጥ በመጠቀም ሥርዓተ አልበኛ ከሆኑት ውስጥ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ያሉት ‹‹አክቲቪስት›› ነን ባዮች ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ አካላት አዋጊ ጄነራል በመሆን ጭምር የፖለቲካ ምህዳሩን በተለይ ደግሞ ሃሳብን ከመግለፅ መብት ባለፈ ለውጡን በማደናቀፍ በነውጥ መሪነት ሥራ ተጠምደዋል፤ ዘምተዋልም፡፡
ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ከዚህ ቀደም ‹‹ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እንዳንሰበሰብ አድርጎናል፤ አዳራሽ ኪራይ ተከልክለናል ወዘተ… ›› የሚል እና የሃሳብ ብዝሀነትን የሚገታ ተግባር ይፈፀምባቸው እንደነበር ቢገልፁም፤ አሁን ደግሞ መንግሥት ምቹ ሁኔታ ቢፈጥርላቸውም ፓርቲዎቹ በፈለጉት ክልል እና አካባቢ ካሉ ዜጎች ጋር ተገናኝተው ምህዳሩን የመጠቀምና ያለመጠቀም ሁኔታ ‹‹ሰጪና ነሺው›› የተደበላለቀበት ሆኖ ይታያል፡፡ በዚህም አንዳንድ ፓርቲዎች ‹‹እንቅስቃሴያችን ሥርዓት ባጡ የተደራጁ አላካት እየተገደበ ነው›› ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ በዚህ ሂደት የአክቲቪስት ነን ባዮቹ ሚና ከልማት ይልቅ ወደ ጥፋት የተሸጋገረ ሆኖ ተስተውሏል፡፡
በአጠቃላይ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ሁሉንም ባልተገደበ መልኩ ሃሳብንም ሆነ እንቅስቃሴን መፍቀዱ ለአንዳንዶች የተሰጠውን መብት ያለ ቅጥ ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የሌሎችን የመንቀሳቀስ መብት ሳይቀር እስከ መንፈግ ተደርሷል፡፡ ይህ ተግባር በጥቅሉ የመጣውን የፖለቲካ ምህዳር ከማጥበብ ባለፈ አንዳንዶችን ሥርዓት አልበኛ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡
በመሆኑም ይህን በቅርበት የሚያስተውሉት የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌዴራል መንግሥት ሕግና ሥርዓትን ያልተከተሉ ተግባራትን ማስቆም ሕገ መንግሥታዊ ግዴታቸው ነው፡፡ በዚህች አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የመጡትን ለውጦ ሕግና ሥርዓቱ በሚፈቅደው መንገድ መጠቀም ካልቻለ ከዚህ ቀደም ወደነበርንበት አዙሪት ብቻ ሳይሆን ወደ ባሰ ሁኔታ የሚያስገባን በመሆኑ፤ ሁሉም አካል የምህዳሩን ገደብ ማለፍ አይገባውም፡፡ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን የመጣልንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ፈንታ ወደ ችግር ገብተን ያገኘነውን ዕድል እንዳናጣ ራሳችን ሕግ አክባሪና አስከባሪ መሆን እንደሚገባን ወቅቱ ያስገድደናል፡፡
አዲስ ዘመን መጋቢት 19/2011
PVC Pipes in Iraq Elite Pipe Factory in Iraq is a leading name in the production of high-quality PVC pipes, providing durable and reliable solutions for a range of applications. Our PVC pipes are designed to meet rigorous standards, ensuring longevity and performance even in the most demanding environments. With a commitment to excellence, Elite Pipe Factory stands out as one of the best and most reliable manufacturers in Iraq, offering products that deliver both strength and flexibility. For more information on our PVC pipes and other offerings, visit our website at elitepipeiraq.com.
What topics would you like to see covered in future posts? Let us know in the comments.
Your positivity and optimism are contagious It’s evident that you genuinely care about your readers and their well-being
I am so grateful for the community that this blog has created It’s a place where I feel encouraged and supported