የሰኔ 2010 ዓ.ም ትውስታዎች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ 365 ቀናት ሆኗቸዋል። በእነዚህ ጊዚያትም የተለያዩ ተግባራትን አከናው ነዋል። በ2010 ዓ.ም ሰኔ ወር ብቻ በተለያዩ ዘርፎች ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ተግባራት እንደሚከተለው ለማጠናቀር ተሞክሯል።
•ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጽና ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ጋር ባደረጉት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከፕሬ ዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር የተለያዩ ስምምነቶች አድርገዋል። በስምምነታቸው መሰ ረት ከተፈጸሙት ተግባራት በግብጽ ሀገር በእስር ላይ የነበሩ 32 ኢትዮጵያዊያን ከእስር
ተፈተው ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሁለቱን ሀገራት የመልማት ፍላጎት ባከበረ መልኩ በአዲስ መንፈስ በጋራ ለመሥራት መስማማታቸው፣ በፖለቲካና ኢኮኖሚ መስኮች ያላቸውን ትብብር በሚያጠናክሩባቸው ሁኔታዎች ላይ ያደረጉት ምክክር ይጠቀሳል።
በተመሳሳይ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መካከል ሰባት ስምምነቶች ተፈርመዋል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አልጋ ወራሽ ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል። በሁለቱ ሀገራት ከተፈጸመው ስምምነት የቱሪዝም ልማት ይጠቀሳል። ሶስት ቢሊየን ዶላር የሚገመት ኢንቨስትመንትም ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊየን ዶላር በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ካዝና በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
•ኢትዮጵያ የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብላ ለመተግበር በወሰነችው መሰረት የኤርትራ ፕሬዚዳንት የኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪና የፖቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ የማነ ገብረአብ እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኡስማን ሳለህ በአዲስ አበባ ከተማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በስፋት ተወያይተዋል።
•ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች በነቂስ የወጡት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ነበር። በወቅ ቱም ለድጋፍ የወጣው ህዝብ ለጥቅላይ ሚኒስትሩ ደስታውን እየገለጸ ያልተጠበቀው የቦንብ ፍንዳታ ደርሶ ዜጎችን ለጉዳት ዳርጓል። ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ይህ ቀን ኢትዮጵያዊያን ተደምረው በፍቅር፣ በደስታ፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ፍቅር እንዲዘንብ ያደረጉበት እለት ቢሆንም ይህን የማይፈልጉ ሀይሎች በተጠና ፣በታቀደና በሙያ ታግዘው ይህን ደማቅ ሥነ ስርዓት ለማደፍረስ፣ ለማበላሸት፣ የሰው ህይወት ለመቅጠፍ፣ ደም ለማፍሰስ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። ነገር ግን ‹‹ፍቅርና ይቅርታ ያሸንፋል፣ መግደል መሸነፍና መዋረድ ነው›› ማለታቸው ይታወሳል። በፍንዳታው የሁለት ዜጎች ህይወት አልፏል። ከመቶ በላይ የሚሆኑ ቆስለዋል።
• በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የድፍድፍ ነዳጅ የሙከራ ምርት እንደሚጀምር በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይፋ ሆኗል። በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ የሚመረተው ድፍድፍ ነዳጅ በቀን 450 በርሜል እንደሚያመርት ተገልጧል።
•ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ኣብይ አህመድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በማንኛውም ሀገራዊ፣ ፖቲካዊና ማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ አጋዥ ሀሳቦችን ለማመንጨት አቅም ያላቸው መሆናቸውን በጋራ ማድረጉ ላይ ተናግረዋል። የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የሀገሪቱን አንድነትና መደመርን የሚሰብኩ ሥራዎችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ፤ ሀገሪቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የበኩላቸውን እንዲወጡ የቤት ሥራ የተሰጠበትም ነበር።
•የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2003 ዓ.ም በአሸባሪነት የፈረጃቸውን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/፣የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር /ኦብነግ/ እና ግንቦት ሰባት ከሽብርተኝነት ስያሜ እንዲሰረዙ ውሳኔ አሳልፏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የበጀት ዓመቱን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የመን ግስት ትላልቅ ኩባንያዎች ወደግል የማዞሩ ሥራ በጥንቃቄ እንደሚከናወን ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ባካሄደው 30ኛ መደበኛ ስብሰባም የ2011 ዓ.ም በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊን ብር አጽድቋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 19/2011
በጋዜጣው ሪፖርተር