አዲስ አበባ፡- ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ታሳቢ በማድረግ የህጻናት ጉዳይን በተመለከተ አምስት ሴት ዳኞች የሚሰየሙበት ችሎት ለመጀ መሪያ ጊዜ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚካሄድ ተገለጸ። በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን እጅጉ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ከሴቶች የበለጠ ለህጻናት የቀረበ አካል የለም። ስለሆነም የሴቶች ቀንን አስመልክቶ የህፃናት ጉዳይ በሴቶች ብቻ የሚታይ ይሆናል።
ጉዳዮቹ የተለያዩ ደረጃዎችን አልፈው የመጡ ሲሆን፣ በዘርፉም የረጅም ዓመት አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አምስትሴት ዳኞች ተሰይመው ውሳኔ የሚሰጡ ይሆናል። ችሎቱ በሴቶች የሚሰየምበት ምክንያት ከ80 በላይ የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በችሎቱ ከተሰየሙት አንጋፋ ዳኞች ልምድ እንዲቀስሙ ለማድረግ መሆኑን ጠቅሰው በተመሳሳይ ከ80 በላይ የከፍተኛ ተቋማት የህግ ተማሪዎችም እንዲሁ አርአያ የሚሆኗቸውን ሴት ዳኞች እንዲመለከቱ ዕድል የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል።
በወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ሌሎች ተሳ ታፊ ሴቶች እንደሚኖሩ የጠቆሙት አቶ ሰለሞን፤ ‹‹ችሎቱ የማስተማሪያም መድረክ ጭምር ይሆናል›› ብለዋል። በተለይ ሴት የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች በትምህርታቸው ምን ምን ነገሮችን ማካተት እንዳለባቸው ልምድ የሚቀስሙበትም እንደሆነ ተናግረዋል።
‹‹ጉዳዩ እንደማንኛውም ጊዜችሎት ቢሆንም ለየት የሚያደርገው በሴት ዳኞች መከናወኑና በእነርሱ ስም ችሎቱ መሰየሙ መሆኑ ነው።›› ብለዋል። እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ ማህበረሰቡ ለእን ግልት እንዳይዳረግ ጎን ለጎን ሌሎች ችሎቶችም የሚካሄዱ ሲሆን አንዱ ችሎት ብቻ በሴቶች የሚሰየም ይሆናል።
ከፌዴራል ውጪ ያሉ ሴት ዳኞች ሌሎች ጉዳዮችን የሚያዩበትም ዕድል ተመቻችቷል። በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚሰሩ ሴት ዳኞች ውስጥ አምስቱ የተመረጡበት ምክንያት ቀጠሮውም ሆነ የያዙት ጉዳይ ለዚህ ቀን ተስማሚ በመሆኑ ነው። በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስምንት ሴት ዳኞች ያሉ ሲሆን፤ 108 ሴት ዳኞች ደግሞ በከፍተኛና በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚሰሩ መሆናቸው ታውቋል።
አዲስ ዘመን የካቲት 29/2011
በጽጌረዳ ጫንያለው
Symptomatic luteal phase dosing, or your non urgent health newsletter priligy united states