እንደምን አላችሁ ልጆች፣ ሰላም ናችሁ? ክረምቱ እንዴት አለፈ፣ በጥሩ ሁኔታ ነው ያለፈው? “አዎ” ስትሉኝ ይሰማኛል። በጣም ጥሩ።
ልጆች በሰኔ ወር ትምህርት ቤት ሲዘጋ መስከረም ደርሶ ትምህርት ቤት እስኪከፈት ያለው ጊዜ ሩቅ ይመስል ነበር አይደል? አዎ፣ ቶሎ የሚደርስ አይመስልም ነበር። ግን ይኸው መስከረም ጠብቶ ትምህርት ቤት ተከፈተ። ከጥቅምት 2 ጀምሮ እንግዲህ ሁላችሁም ከጓደኞቻችሁ ጋር ትገናኛላችሁ ማለት ነው።በጣም ደስ ይላል፤ አይደለም እንዴ ልጆች?
ከጥቅምት 2 በኋላ ሁላችሁም በትምህርት ገበታችሁ ላይ ናችሁ። ለዚህ ደግሞ ትምህርት ቤቶቻችሁ ሁሉ ፅድት ብለው፤ መምህራኖቻችሁ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው እየጠበቋችሁ ነው።በዚህም የዘንድሮው የትምህርት ዘመን ከሌሎቹ ሁሉ ደስ የሚል እንደሚሆንላችሁ ያስታውቃል።
ልጆች ይህንን ስነግራችሁ ዝም ብዬ አይደለም። በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ተዘዋውሬ እንደተመለከትኩት ትምህርት ቤቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዘጋጅተው በማየቴ ነው።በተለይ እናንተን ከኮቪድ ለመከላከል የተደረገውን ዝግጅት ተመልክቼ ተደንቄያለሁ። በደንብ ተዘጋጅተዋል። ከእናንተ የሚጠበቀው ትምህርት ቤቶቻችሁ በሚሏችሁና በኮቪድ-19 መከላከያ መመሪያ መሰረት የሚጠበቅባችሁን ማድረግ ብቻ ነው። በቃ፣ ይህንን ካደረጋችሁ እራሱ(ሷ)ን ከኮቪድ የሚጠብቅ/ምትጠብቅ “ጎበዝ ተማሪ”፤ ወይም “ሞዴል ተማሪ” ተብላችሁ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ትሸለማላችሁ ማለት ነው።
በነገራችን ላይ ልጆች “ሞዴል ተማሪ”፤ ማለትም ለሌሎች መልካም አርአያ የሆነ ተማሪ መሆን ትፈልጋላችሁ? በጣም ጥሩ። እንግዲያውስ አንድ “ሞዴል ተማሪ” መሆን የሚፈልግ ተማሪ ምን ምን ተግባራትን መፈፀም እንደሚገባው ሶስቱን ዋና ዋና ተግባራትን ብቻ በማንሳት ልንገራችሁ።
ፈቃደኝነት
ልጆች አንድ ሞዴል ተማሪ በመጀመሪያ ደረጃ ሊያደርግ የሚገባው ተግባር “ፍቃደኛ መሆን” ወይም “ፈቃደኝነት”ን ማሳየት ነው። እናንተም በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታችሁን ለመከታተል ፈቃደኛ መሆን አለባችሁ። ፈቃደኛ ሆናችሁ ትምህርታችሁን ካልተከታተላችሁ ትምህርትን ልትወዱትም ሆነ በአግባቡ ልትከታተሉና ልትረዱት አትችሉም። “ጎበዝ!!!” ተብላችሁም ልትሸለሙና ለሌሎች አርአያ መሆን ይከብዳችኋል። ስለዚህ ማንኛውንም ተግባር ስታከናውኑ በመጀመሪያ ፈቃደኝነቱ ሊኖራችሁ ይገባል።ይህንን አሁኑኑ፣ ገና ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ልትዘጋጁበት ይገባል።ለትምህርታችሁ ፍቅር ሊኖራችሁም ያስፈልጋል።
ተደጋጋሚ ሙከራ
ልጆች ሌላው “ሞዴል ተማሪ” ለመሆን አስፈላጊው ጉዳይ ጥረት ማለትም ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረግ ነው።
ልጆች እንደምታውቁት ምንም ነገር በአንድ ጊዜ መቶ በመቶ የተሳካ አይሆንም። የተሳካ የሚሆነው በተደጋጋሚን ከኮቪድ የሚጠብቅ/ምትጠብቅ “ጎበዝ ተማሪ”፤ ወይም “ሞዴል ተማሪ” ተብላችሁ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ትሸለማላችሁ ማለት ነው።
በነገራችን ላይ ልጆች “ሞዴል ተማሪ”፤ ማለትም ለሌሎች መልካም አርአያ የሆነ ተማሪ መሆን ትፈልጋላችሁ? በጣም ጥሩ። እንግዲያውስ አንድ “ሞዴል ተማሪ” መሆን የሚፈልግ ተማሪ ምን ምን ተግባራትን መፈፀም እንደሚገባው ሶስቱን ዋና ዋና ተግባራትን ብቻ በማንሳት ልንገራችሁ።
ፈቃደኝነት
ልጆች አንድ ሞዴል ተማሪ በመጀመሪያ ደረጃ ሊያደርግ የሚገባው ተግባር “ፍቃደኛ መሆን” ወይም “ፈቃደኝነት”ን ማሳየት ነው። እናንተም በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታችሁን ለመከታተል ፈቃደኛ መሆን አለባችሁ። ፈቃደኛ ሆናችሁ ትምህርታችሁን ካልተከታተላችሁ ትምህርትን ልትወዱትም ሆነ በአግባቡ ልትከታተሉና ልትረዱት አትችሉም። “ጎበዝ!!!” ተብላችሁም ልትሸለሙና ለሌሎች አርአያ መሆን ይከብዳችኋል። ስለዚህ ማንኛውንም ተግባር ስታከናውኑ በመጀመሪያ ፈቃደኝነቱ ሊኖራችሁ ይገባል።ይህንን አሁኑኑ፣ ገና ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ልትዘጋጁበት ይገባል።ለትምህርታችሁ ፍቅር ሊኖራችሁም ያስፈልጋል።
ተደጋጋሚ ሙከራ
ልጆች ሌላው “ሞዴል ተማሪ” ለመሆን አስፈላጊው ጉዳይ ጥረት ማለትም ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረግ ነው።
ልጆች እንደምታውቁት ምንም ነገር በአንድ ጊዜ መቶ በመቶ የተሳካ አይሆንም። የተሳካ የሚሆነው በተደጋጋሚ ሙከራ፣ ያላሰለሰ ጥረት ሲደረግ ነው። በመሆኑም በምትሰሩት በማንኛውም ስራ ተስፋ ሳትቆርጡ ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረግ አለባችሁ።የጀመራችሁትንም ሆነ ያቀዳችሁትን ለማሳካት ጣሩም። ይህ ደግሞ ወደ ሌላ የተሻለ ፈጠራ ይወስዳችኋልና ውደዱት።
እውቀትን ወደ ተግባር መለወጥ ልጆች ሰው በተፈጥሮው የሚያውቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እየተማረ ሲሄድ ደግሞ የበለጠ የሚያውቀው ነገር እየጨመረ ይሄዳል። ያ ማለት እውቀቱ በየጊዜው እያደገና እየሰፋ ይሄዳል ማለት ነው። በመሆኑም ያንን እውቀቱን ወደ ተግባር በመቀየር፤ ተግባር ላይ በማዋል በሚሰራው ስራ ውጤታማ መሆን ይቻለዋል። አንድ ተማሪ ይህንን ማድረግ ከቻለ ጎበዝ የማይሆንበት፤ “Model student” የማይባልበትና ለሌሎች አርአያ በመሆን የማይሸለምበት ምንም ምክንያት የለም።እናንተም ይህንኑ ታደርጋላችሁ ብዬ ማሰብ ብቻ ሳይሆን እመኝላችኋለሁ።
እንዲሁም አርአያ (ሞዴል) ተማሪ ከሌሎች የሚለይባቸው ባህርያት ያሉት ሲሆን፤ ከነዚህ መካከል ተሳታፊነት፤ ማዳመጥ፣ አለመረበሽ፤ ተጫዋች መሆን፤ ትጉህነት፤ ሰውን ማክበር፤ ሀላፊነትን መወጣት፤ ምክንያታዊ መሆን፤ በራሱ መተማመን ወዘተ ናቸው።
ልጆች አንድ ተማሪ በትምህርት ብቻ አይደለም ሞዴል የሚሆነው፤ ከትምህርት ውጪ በሌሎች ተጓዳኝ ተግባራትም ሞዴል መሆን ይቻላል። በመሆኑም በተለያዩ ክበባት ተግባራትም በመሳተፍ ሞዴል ለመሆን ጥረት አድርጉ። በሉ እንግዲህ ልጆች፤ ሳምንት በሌላ ጉዳይ እስክንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑ።
ግርማ መንግሥቴ
አዲስ ዘመን መስከረም 16/2014