ልጆች እንዴ ናችሁ? ሁሉ ሰላም ነው? የክረምቱ ወራት አልቆ አዲስ ዓመት እየመጣ እንደሆነ አወቃችሁ አይደል ልጆቼ አዲሱን ዓመት በድስታ ለመቀበል ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው? ውዶቼ ለቀጣይ የትምህርት ዓመት በርትታችሁ ተዘጋጁ እሺ? ልጆቼ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋልና አንባቢ ሁኑ እሺ… ለዛሬም የኢትዮጵያ እናቶችና አባቶች ለትውልድ ይተላለፍልን ብለው ካዘጋጁት ተረት መካከል በእማማ ዘሪቱ ከበደ የተፃፈውን እንዲህ አዘጋጅተነዋል፤ መልካም ንባብ።
በአንድ ወቅት አንድ የወደፊቱን መናገር የሚችል ሽማግሌ አማካሪ የነበረው ንጉስ ነበር።ታዲያ አዛውንቱ ሰው ሲሞት ንጉሱ ወደ ልጁ ልኮበት ስለ ወደፊቱ እንዲተነብይ ጠየቀው።ልጁ ግን ምንም ማድረግ ስለማይችል በጣም አዘነ፡፡
ሆኖም ልጁ ወደ ንጉሱ ቤተ መንግስት እየሄደ ሳለ አንድ ቀበሮ አገኘ።ቀበሮውም ልጁን “ሃምሳ በጎች ከሰጠኸኝ ስለወደፊቱ ልነግርህ እችላለሁ፡፡” አለው፡፡
ልጁም በዚህ
ከተስማማ
በኋላ
ቀበሮው
“የሚቀጥሉት
ጥቂት
ዓመታት
የእሳትና
የቃጠሎ
እንደሚሆኑ
ለንጉሱ
ንገረው፡፡”
አለው፡፡
ልጁም ወደ ንጉሱ ሄዶ ይህንኑ ነገረው።ነገር ግን ቃል የገባውን በጎች ከማምጣት ይልቅ እሳት ይዞ መጥቶ ቀበሮውን ሊያቃጥለው ሞከረ፡፡
ከሶስት ዓመታት በኋላ ንጉሱ አሁንም ወደ ልጁ መልዕክት ሲልክ ልጁ ቀበሮውን እስኪያገኘው ድረስ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው።ነገር ግን ቀበሮው አሁንም “ሃምሳ በጎች ካመጣህልኝ ስለወደፊቱ እነግርሃለሁ፡፡” አለው፡፡
ልጁም እንደገና ቃል ገብቶ ቀበሮው የሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የጦርነት ጊዜ እንደሚሆኑ ነገረው፡፡
በዚህም ጊዜ ለቀበሮው በጎች ከማምጣት ይልቅ ጦር ይዞ መጥቶ ቀበሮውን ሊገድለው ሞከረ፡፡
ከሶስት ዓመታት በኋላ ንጉሱ አሁንም ወደ ልጁ ሲልክበት ቀበሮው መንገድ ላይ አግኝቶት መጪው ጊዜ የሰላም እንደሚሆን ነገረው፡፡
በዚህ ጊዜ ልጁ ሄዶ ሃምሳ በጎችን ለቀበሮው አምጥቶለት ዘመኑም የሰላም ሆኖ ሰዎችና እንስሳት እንዲሁም ልጁና ቀበሮው ታርቀው በሰላም አብረው መኖር ጀመሩ ይባላል።
አስመረት ብስራት
አዲስ ዘመን ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም