እ.ኤ.አ በ2012 በኬኒያ የተገኘው ጥቂት የነዳጅ ድፍድፍ ክምችት ማጣሪያውን ለመገንባት የሚያስችል ተስፋ ሰጪ ውጤት እንደሌለው የኬኒያ ነዳጅ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ፡፡
በኬኒያ ሎክቸር በሚባለው ሸለቋማ አካባቢ እ.ኤ.አ 2012 ተገኝቶ ለገበያ ይቀርባል የተባለለት ድፍድፍ ነዳጅ አምስት መቶ ስልሳ ሚሊዮን በርሜል ምርት እንደሚሰጥ ቱሎ የተሰኘው ኩባንያ የነዳጅ ዘይት ግምቱን አስቀምጦ ነበር፡፡
ቱሎ እንደገለጸው ከሆነ በየቀኑ አጠቃላይ መጠኑ ከ60 ሺህ እስከ 100 ሺህ በርሜል ከአጠቃላይ ምርት ይይዛል ብሎ ነበር፡፡ ዓለም ያረጋገጠው ሀቅ የሚያሳየው የነዳጅ ማጣሪያዎች የሚገነቡት ገንዘብ ለማግኘት ሲባል ብቻ ነው፡፡ ዝቅተኛው የማጣራት አቅም ደግሞ 400 ሺህ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በቀን የመስጠት አቅም ብቻ እንዳለው የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር ዋና ጸሃፊ አንድሪው ካሙ ለሪፖርተሮች አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹አሁን ላይ እኛ በቀን 80 ሺህ በርሜል አለን፡፡ ሥለዚህ የቱ ላይ ነው ገንዘብ ልናገኝበት(ሊያመጣ) የሚችለው? እንዲህ ከሆነ ከሕንድ በርካሽ ብናስገባ የተሻለ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡
ኬኒያ ከበፊትም በዋና ከተማዋ ሞምባሳ አካባቢ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ገንብታ የነበረች ቢሆንም ወደ ውጪ ምንም አይነት ነዳጅ ልካ አታውቅም፡፡ ይሁን እንጂ እ.ኤ.አ. በ2013 የ1 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እቅድ ማስፋፊያ ጋር ተያይዞ ሥራው ቆሟል፡፡ አማካሪውም በምጣኔ ሀብቱ ላይ የሚጨምረው ምንም አይነት እሴት እንደሌለ መግለጹ ተዘግቧል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2016 የአገሪቱ መንግሥት የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታውን ከነጠቀ በኋላ እንዲቀየር በማድረግ ለመጋዘንነት አገልግሎት እንዲውል አድርጎታል ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል በጥቁር ድፍድፍ ነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማሩት ድርጅቶች አፍሪካ ዘይት ኮርፖሬሽን እና ቶታል ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት ቱሎ እንደገለጸው ንግድን ያማከለ የመግባቢያ የሥምምነት ሰነድ ከኬንያ መንግሥት ጋር መፈራረም ችሏል፡፡ በሥምምነት ፊርማው በተመላከተው አቅጣጫ መሰረት ለመጀመሪያው ዙር የነዳጅ ድፍድፍ ማምረቻና ማስተላለፊያ ዝርጋታ መገንቢያ የሚሆን 800 ሄክታር የመሬት ርክክብ ተደርጓል፡፡
የኬኒያ መንግሥት በይፋዊ መግለጫው ባሳወቀው መሰረት የኬኒያ ብሄራዊ የነዳጅ ዘይት ኮርፖሬሽን በዝቅተኛ ደረጃ ለአገር ውስጥ የሚሆን የኬኒያ ብሔራዊ ዘይት ኮርፖሬሽን እ.ኤ.አ. ከሕዳር 2017 ጀምሮ 1 ቢሊዮን እጥፍ የአሜሪካን ዶላር እድገት በናይሮቢ ከበርቴዎችና በለንደን ሽያጭ ዝውውሮች መካከል እስከ 1920 መድረሱ ይታወቃል፡፡
በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የመጨረሻ ውሳኔ ስምምነት መሰረት የገለጹ ቢሆንም ቱሎ በዚህ ዓመት መጨረሻ ይጠናቀቃል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡ ኬኒያ ከምታካሂደው ድፍድፍ ነዳጅ ፍለጋ ጋር ተያይዞ በሶማሌ ድንበር አካባቢ በባህር ይገባኛል ውዝግብ እየተካረረ መምጣቱን ተከትሎ ኬኒያ አምባሳደሯን ከኬኒያ መጥራቷ ይታወሳል፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 14/2011
ሙሀመድ ሁሴን