
ሌላኛው በዚህ ሳምንት ከተከሰቱ አበይት ታሪካዊ ሁቶች ውስጥ አንስተን የምናወሳው በዚህ ሳምንት ሐምሊ 10 ቀን የተወለዱት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላን ታሪክ ነው። በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ትግልና በመጨረሻም የነፃነት ታሪክ ውስጥ የእሳቸው ስም ጎልቶ ይሰማል። ለ27 ዓመታት ለአገራቸው ነፃነት ለህዝባቸው አርነት ሲሉ እስር ላይ ቆይተዋል።
የደቡብ አፍሪካዋ ትራንስኪ የእኚህ ታላቅ የነፃነት ታጋይ የይቅር ባይነት ተምሳሌት የሆነ የዓለማችን ድንቅ ሰው የተወደሉባት ከተማ ነች። እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር ጁላይ 18 ቀን 1918 ማንዴላ ተወለዱ።ማንዴላ የተወለዱበት አካባቢና በጎሳቸው ማዲባ የሚል ስያሜም ነበራቸው።ኔልሰን ማንዴላ ገና በልጅነት እድሜያቸው ነበር አባታቸውን ያጡት። በዚህ ጠንካራና በራስ መቆም ነገሮችን በጥልቀት መመርመርና የበዙ ፈተናና ችግሮችን ማሳለፍ ነበረባቸውና አደረጉት። ዕድሜያቸው ለጋብቻ ሲደርስ በተወለዱበት አካባቢ ባህል መሰረት ማግባት እንዳለባቸው ይነገራቸዋል። ነገር ግን አግብቶ መኖር የማዲባ ፍላጎት አልነበረምና ጋብቻ በመሸሽ የሚፈልጉትን አላማ ለማሳካት ወደ ደቡብ አፍሪካዋ ደማቅ ከተማ ጁሀንስፐርግ አቀኑ።
መማር የሚፈልጉትን ዓላማ ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን የተረዱት ማንዴላ በሄዱበት ጆሀንስፐርግ በመጀመሪያ ፎርትሀሪ ከዚያም በዊክዋተርስ ራንድ በሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ትምህርት በመከታተል በህግ ተመርቀዋል። ከትምህርት ቤት ከወጡ ከሁለት ዓመት በኋላ ትዳር መስርተው አራት ልጆችን ማፍራት ችለዋል።
ከዚህ በኋላ ነው ማንዴላ ፊታቸውን ወደ ፖለቲካ ያዞሩት። በዚያ ዘመን ንቁ ተሳታፊ የነበረውና አሁንም ድረስ ያለው አፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ በሚባለው ፓርቲ ውስጥ በመግባት ንቁ ተሳታፊ በመሆን የፖለቲካ ትግል ጀመሩ። በነበራቸው የተሻለ የፖለቲካ ተሳትፎም እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር በ1952 የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን በወቅቱ ደቡብ አፍሪካን ይጨቁን የነበረውን የአፓርታይድ ስርዓት ለማስወገድ ፊት ለፊት መታገል ጀመሩ።
ከአራት ዓመታት ብርቱ ትግል በኋላ ማንዴላ የሚያደርጉትን ትግልና የነፃነት ተጋድሎ ስጋት ውስጥ የከተተ ክስ የአገር ክህደት ወንጀል በሚል በነጮች ተመሰረተባቸው። የክስ ክርክሩ ለ5 ዓመታት የቆየ ሲሆን ኔልሰን ማንዴላ በክርክሩ አሸንፋ ነፃ ተባሉ። በጊዜው ደቡብ አፍሪካን ይጨቁን የነበረው የአፓርታይድ ስርዓት ከተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች ተቃውሞ ሲደርስበት የከፋ የሃይል እርምጃ በደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታጋዮች ላይ መፈፀም ጀመረ። በዚህም ብዙ ጥቁሮች በግፍ ይገደሉ ጀመር።
ማንዴላም ከባልደረቦቻቸውና የትግል ህይወ ታቸው ካስተዋወቃቸው ወዳጅና የዓላማ አንድነት ካገናኛቸው ጓዶቻቸው ጋር በመሆን ሰላማዊ የትግል ስልት አዋጭ አለመሆኑን ወስነው በትጥቅ ትግል አፓርታይድን ለማስወገድ ተነሱ። ለዚህም በመሰረቱት ተዋጊ ጦር መሪ በመሆን ወደተለያዩ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ ጉዞ ጀመሩ። ወደ ኢትዮጵያም በመምጣት ወታደራዊ ስልጠና ማግኘታቸውን የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በተለያዩ አገራት የሞራልና የትጥቅ ድጋፍ አግኝተው ወደ አገራቸው የተመለሱት ማንዴላ የአፓርታይድ ስርዓት መሪዎች ወጥመድ አዘጋጅተው ጠብቀዋቸው ስለነበር ሲመለሱ ይዘው ለአምስት ዓመታት በእስር ላይ ቆዩ።
የእስር ጊዜአቸውን ጨርሰው ሲወጡ ግን ከትግላቸው ከመታቀብ ይልቅ የአገራቸውን ነፃነት ለማስከበርና ከወራሪው የአፓርታይድ ስርዓት ለማላቀቅ ሌላ ትግል ማድረግ ቀጠሉ። በመጨረሻም በድጋሚ ተያዙና በእድሜ ይፍታህ ወደ እስር ቤት ተወረወሩ።ማንዴላ ግን እንዲሁ በቀላሉ የሚሰበሩና በጠላቶቻቸው አማካኝነት በሚደርስባቸው ጫና እጅ የሚሰጡ አልነበሩም።
እስር ቤት ሆነውም በተለያየ ስልት ትግላቸውን ቀጠሉ። በዚህም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የሚፈጥሩትን ተፅዕኖ በማየት ማንነታቸውን መመርመርና ዓላማቸውን መረዳት፣ ከዚያ ቀስ በቀስ ለእርሳቸውና የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ ለተባለው ድርጅታቸው ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል ጀመረ። ቀስ በቀስም በደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ ስርዓት ላይም ዓለምአቀፍ ጫና በረታ። ስርአቱ እኚህን የነፃነት ታጋይ መፍታት ግድ እየሆነበት መጣ። ፓርቲያቸውም የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲያደርግ ተፈቀደለት። በመጨረሻም ማዴላ ከእስር ተፈተው ፓርቲያቸውን በአዲስ መልክ አጠናክረው መምራት ጀመሩ።
ማንዴላ በዚህ ሰዓት ባደረጉት ትግልና ለሰላም ባሳዩት ቆራጥነት በጊዜው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ዴክላርክ ከነበሩት ጋር አብረው የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ መሆንም ችለው ነበር። በመጨረሻም ደቡብ አፍሪካ እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር በ1994 የመጀመሪያው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አደረገችና እኚህ ብርቱ ታጋይ የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሆኑ።
በ1997 ከፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው ራሳቸውን አነሱ። ቀጥሎም በ2004 ከፖለቲካዊ ተሳትፎ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ። እኚህ የነፃነት ታጋይ ለአገራቸውና ለአፍሪካ ትልቅ አስተዋፅዖን አበርክተው ለሰው ልጆች ይቅር ማለት ምን ያህል ፋይዳ እንዳለው አሳይተው በተወለዱ 95 ዓመት በኋላ እንደ ኤሮፓውያን የዘመን ቀመር ህዳር 26
ተገኝ ብሩ
አዲስ ዘመን ሐምሌ 11/2013