አዲስ አበባ፡- የኢፌዴሪ የገቢዎች ሚኒስቴር በስድስት ወራት ውስጥ 600 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ኮንትሮባንድ መያዙንና ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር ፡፡ የኢፌዴሪ የገቢዎች ሚኒስቴር በስድስት ወራት ውስጥ የ600 ሚሊዮን ብር ኮንትሮባንድ መያዙንና ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በኮንትሮባንድ ሰሞኑን የተያዘውን ጨምሮ ወደ 600 ሚሊዮን ብር ደርሷል፤ ይህ ማለት ግን የተበላሹትንና የሚወገዱትን ቁሳቁስና ሌሎች ነገሮችን ሳይጨምር ነው፡፡
«በህዝባችን ላይ ሁሉም ነገር እየመጣ እንዲጫንበት አንፈቅድም» ያሉት ሚኒስትሯ፣ «ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የተበላሹ የህጻናት ወተት፣ ልባሽ ጨርቆች፣ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች፣ ሺሻና የመሳሰሉት የራሳቸው የሆነ የአወጋገድ ሥርዓት ስላላቸው ይወገዳሉ እንጂ ወደ ህዝቡ አይደርሱም» ሲሉ ገልፀዋል፡
በላይ ውዝፍ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡ የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በኮንትሮባንድ ሰሞኑን የተያዘውን ጨምሮ ወደ 600 ሚሊዮን ብር ደርሷል፤ ይህ ማለት ግን የተበላሹትንና የሚወገዱትን ቁሳቁስና ሌሎች ነገሮችን ሳይጨምር ጥሬ ገንዘብ ብቻ ነው፡፡
«በህዝባችን ላይ ሁሉም ነገር እየመጣ እንዲጫንበት አንፈቅድም» ያሉት ሚኒስትሯ፣ «ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የተበላሹ የህጻናት ወተት፣ ልባሽ ጨርቆች፣ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶች፣ ሺሻና የመሳሰሉት የራሳቸው የሆነ የአወጋገድ ሥርዓት ስላላቸው ይወገዳሉ እንጂ ወደ ህዝቡ አይደርሱም» ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የተበላሹ ቁሳቁስን ጨምሮ የጦር መሳሪያ እንደሆነ ያመለከቱት ወይዘሮ አዳነች፣ የተበላሹ ቁሳቁስ በሚያቃጥሉበት ወቅት ግን ህዝቡ ቅር እንደሚለው ጠቅሰዋል፡፡
ይሁንና አገሪቱ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ባለመሆኗ ክብሯን ማስጠበቅ የሚጠበቅባት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት፤ በተቃራኒው ደግሞ ከአገሪቷ ማዕድንና የቁም ከብት የውጭ ምንዛሪ የሚያመጡ ሆነው ሳለ በህገ ወጥ መንገድ ሲወጣ ተስተውሏል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉት የተበላሹና እንደ ጦር መሳሪያዎች ያሉት ምርቶች ህዝቡን እርስ በእርሱ እንዲተላለቅ በነጻ ሁሉ በሚታደልበት ምስራቁ ኢትዮጵያ አካባቢ ተይዘዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ሥራዎቹን ለማቀላጠፍና ግብርን በተገቢው መንገድ ለመሰብሰብ ባደረገው እንቅስቃሴ መጀመሪያ ያየው ውዝፉን እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትሯ፣ ከውዝፍ ብቻ ወደ 9 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰባቸውን ገልፀዋል፡ ፡ ሚኒስቴሩ ይህን ውጤት ማጣት የቻለውም ግብር በትክክል የማይሰበሰበው ለምንድን ነው? ከምንስ ነው መሰብሰብ ያለበት? በምን ያህልስ ጊዜ ውስጥ ነጋዴው አምኖ ነው ገንዘቡ የሚሰበሰበው? የሚለው ጉዳይ በመፈተሹ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ያለውን አቅም በመጠቀም ወደ ገንዘብ ያልተቀየሩ ነገሮች እንዳሉም ጠቅሰዋል፡፡ ወይዘሮ አዳነች እንዳሉት፤ ከኦዲት ጋር ተያይዞ ሁሉንም ኦዲት ማድረግ ትክከል አይደለም፡፡
ኦዲት መደረግ ያለበት የስጋት መሰረት የሆነው ነው ፡፡ በተጋላጭነታቸው በፋይላቸው ውስጥ የተለያዩ ማጭበርበሪያ ደረሰኝ የሚያስገቡ ወይም ደግሞ በሚደረገው ክትትል ንግድ እንቅስቃሴያቸው ውስጥ ደረሰኝ እንደማይቆርጡ ታይተው መሆን ስላለበት ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች፣ ይህንን ተስተውሎ ኦዲት የሚደረጉትን ቅደም ተከተል በማስያዝ በያዙት ገንዘብ ትልቅነትም ጭምር ለአገር ያለውን ጠቀሜታ ቅድሚያ በመስጠት ተሠርቷል ብለዋል፡፡ በዚህም ሥራ መሰረት ከሁለት ሺ400 በላይ ትልልቅ ድርጅቶችን ወይም ደግሞ ፋይሎችን ኦዲት በማድረግ የታክስ መጭበርበሩ የቱ ነው? ግብር ስወራውስ የቱ ነው? የሚለውን መለየት በመቻሉ ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ «ከሁሉ በላይ ግን ለውጥ አመጣን የምንለው ኮንትሮባድ ላይ ነው፡፡ ኮንትሮባንድ ላይ ለውጡን እየገመገምን ያለነው በያዝነው ገንዘብ ልክ ብቻ ሳይሆን ኮንትሮባንድን የሚይዝ አካል እየበዛ በመምጣቱ ነው፡፡ የጉምሩክ ሠራተኞች ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት ተፈጥሯል» ሲሉ ሚኒስትሯ አመልክተዋል፡፡
አዲስ ዘመን የካቲት 8/2011
አስቴር ኤልያስ
Nice post. I learn something totally new and challenging on websites